ኦርቶዶክስ ተዋህዶ️


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ይህ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ትምህርቶች መዝሙራት ቅዱሳት ሥዕላትን እንዲሁም ሌሎችን ምናጋራበት መንፈሳዊ ቻናል ነው።
👉"የአባቶቼን ርስት አልሰጥም"👈
ለማንኛውም አስተያየት @jermi123
ይጠቀሙ

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብ ልጆች የሚቆመው ታላቅ አለቃ __ይነሣል::


'https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk' rel='nofollow'>🫃👉መንታ ወንድና ሴት ቢወለዱ ክርስትና እንዴት  ይነሳሉ⁉️
👉ሴት በወር አበባ ጊዜስ⁉️
👉 ወንድ ህልመ ሌሊት ቢያጋጥመው ለስንት ቀን ይረክሳል ⁉️
👉 ሰባቱ አጽዋማት እነማን ናቸው⁉️
👉 አምስቱ አዕማደ ምስጢራት ማን ናቸው⁉️
👉 ከአስርቱ ትዕዛዛት ውጪ ያለው ትዕዛዝ ምነው⁉️

⛪️ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አንፃር መልሱን ይመልከቱ⛪️
                    👇👇👇👇


'https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk' rel='nofollow'>👳‍♂አባቶች ይህንን ይመክሩናል
            እኛ የአባቶቻችን ልጆች ነን
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

ለኦርቶዶኮስ አማኞች ብቻ የተከፈተ ቻናል ።
    ✝ክርስትናችን እንዳንኖረው የሚያደርጉን ምክንያቶች በእውኑ ታውቋቸዋላችሁ⁉️
ለዚህ ችግር አባቶች ምን አሉ⁉️
የምትፈልጉትን ለማግኘት ወደ ቻናላችን ተቀላቀሉ

'https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk' rel='nofollow'>ይህ ምክረ አበው ነው ሁላችሁም ተቀላቀሉ ትጠቀሙበታላችሁ open የሚለውን በመንካት ይቀላቀሉን👇👇👇👇👇👇👇
    ⬜️◻️◽️▫️ⓄⓅⒺⓃ⬛️⬛️⬛️⬛️
    ⬜️◻️◽️▫️ⓄⓅⒺⓃ▪️◾️◼️⬛️
    ⬜️⬜️⬜️⬜️ⓄⓅⒺⓃ▪️◾️◼️⬛️


የ99 ነገድ አመታዊ ክብረ በዓል መቼ ነው?
Poll
  •   ጥቅምት 1
  •   መስከረም 10
  •   ህዳር 13
  •   ህዳር 2
11 votes


በትሕትናው ልዕልናን ላገኘ፣ ለፍጥረታት ባለው ርኅራኄ የአምላክ እናትን ለሚመስል፣ የተቸገሩትን ፈጥኖ መርዳት ልማዱ ላደረገው፣ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ፣ ደግ እና ሰውን ወዳጅ ለሆነው መልአክ ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል እንኳን በሰላም አደረሰን።

ቅዱሳን መላእክት በአንድ ኃጢአተኛ ወደ እግዚአብሔር መመለስ የሚደሰቱትን ያህል፣ ባልተመለሰው ኃጢአተኛ ደግሞ እንዲሁ ያዝናሉ። በአንዱ ኃጢአተኛ መመለስ የተሰማቸውን ደስታ ፈጣሪያቸውን በማመስገን እንደሚገልጹ፣ ባልተመለሰው ኃጥእ የተሰማቸውን ኃዘን ደግሞ አምላካቸውን "ማረው፣ ይቅር በለው" ብለው በመለመን ያሳያሉ። (ያዕ 5፥13) ቅዱስ ሚካኤል አሁን እንዴት እንደ ሆንን አይቶ ይዘንልን፣ አዝኖም ይለምንልን፣ ለምኖም ያስምረን!!!


ሚካኤል ማለት ምን ማለት ነው
Poll
  •   እግዚእ ወገብር
  •   መኑ ከመ አምላክ
  •   እግዚአብሔር ፈዋሽ ነው
  •   መልስ የለም
31 votes


4ኛ ዙር የሥዕል ስልጠና


ስልጠናው ሰኞረቡዕአርብ በሁለት ፈረቃ
ከ 3:00 - 8:00 ሰዓት እና ከ 8:00 - 11:00
ለ4 ወር ይሰጣል።


ምዝገባ ፦ ከህዳር 9 - 12
አድራሻ ፦ ፒያሳ አሮጌው ፖስታ ቤት ግቢ ውስጥ
ለበለጠ መረጃ ፦ 0909389444
                         0944240000


=>አምላከ ብጽዕት ሐና በምልጃዋ ከዘለዓለም እሳት ያድነን:: ጸጋ በረከቷንም ይክፈለን::=>ኅዳር 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት ሐና ቡርክት
2.ቅዱስ አርኬላዎስ ሰማዕት
3.አባ ኤልሳዕ አበ ምኔት
4.አባ ዻኩሚስ መነኮስ
5.ቅዱስ ሚናስ ሰማዕት
6.ቅድስት አውራንያ (የሰማዕቱ እናት)

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ያሬድ ካህን
2.ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት
3.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
4.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ

=>+"+ መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው::
ከያዕቆብ ድንኩዋኖች ይልቅ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳቸዋል::
የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ በአንቺ የተደረገው ነገር ድንቅ ነው . . . ሰው እናታችን ጽዮን ይላል:: በውስጥዋም ሰው ተወለደ:: እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት:: +"+ (መዝ. 86:1)
   
  
https://t.me/enabib


=>+"+ እንኩዋን "ለቅድስት ወብጽዕት ሐና" (እመ ማርያም) ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+

+*" ብጽዕት ሐና "*+

=>"ሐና" ማለት በእብራይስጥኛው "የእግዚአብሔር ስጦታ" እንደ ማለት ነው:: "ሐና: ዮሐና: ሐናንያ" የሚሉ የዕብራይስጥ ስሞች ትርጉማቸው ተወራራሽ ነው:: የዚህችን ቅድስት እናት ክብሯን መናገር የሚችል የለም:: እርሷ ሰማይና ምድርን ለፈጠረ ለእግዚአብሔር ወልድ በሥጋ አያቱ ተብላለችና::

+አንድም ለሰማይና ለምድር ንግስት ለድንግል ማርያም ወላጅ እናቷ ናትና:: ከዓለም ሴቶች ሁሉ የቅድስት ሐና ማሕጸን እንደ ምን ይከብር! በፍጥረት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥንተ አብሶ (የአዳም በደል) መተላለፍ የቀረው በማሕጸነ ሐና ውስጥ ነውና:: (ለዚህ አንክሮ ይገባል!!!)

+ይስሐቅን የተሸከመ የሣራ ማሕጸን ቡሩክ ከተባለ የቅድስት ሐናማ እንደምን አይባል! ከፍጥረታት ሁሉ እግዚአብሔር ድንግል ማርያምን እንደ መረጠ ሁሉ ቅድስት ሐናንም ለአያትነት መርጧታል::

=>ለመሆኑ ቅድስት ሐና ማን ናት? ለዚህ ክብርስ ያበቃት ምሥጢረ ቅድስናዋ ምንድን ነው?

+ቅድስት ሐና ትውልዷ: ነገዷ ከላይ ከቅዱስ አብርሃም: ከታች ደግሞ ከነገደ ካህናት ነው:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

*አብርሃም ይስሐቅን: ይስሐቅ ያዕቆብን: ያያዕቆብ ደግሞ ሌዊንና 11 ወንድሞቹን ይወልዳል::

*ሌዊ ቀዓትን: ቀዓት እንበረምን: እንበረም አሮን ካህኑን ይወልዳሉ::

*ቅዱስ አሮን አልዓዛርን: አልዓዛር ፊንሐስን እያለ ትውልዱ እስከ ቴክታና በጥሪቃ ይወርዳል:: ቴክታና በጥሪቃም ልጅ በማጣት ኖረው: የእንቦሳዎች: የፀሐይና: የጨረቃን ምሥጢር ተመልክተው ሄኤሜንን ይወልዳሉ::

*ሄኤሜን ዴርዴን: ዴርዴ ቶናሕን: ቶናሕ ሲካርን: ሲካርም ሔርሜላን ይወልዳሉ::
*ሔርሜላም ከክርስቶስ ልደት 90 ዓመታት በፊት ማጣት ("ጣ" ጠብቆ ይነበብ) የሚባል ደግ ሰው ከካህናት ወገን አግብታ በስርዓተ ኦሪት ትኖር ነበር:: እግዚአብሔር ለዚህች ደግ ሴት የተባረኩ 3 ሴቶች ልጆችን ሰጣት::

+የመጀመሪያዋን "ማርያም" አለቻት:: ይህቺውም የአረጋዊው ዮሴፍ ሚስትና የቅድስት ሰሎሜ ቡርክት እናት ናት:: ሁለተኛዋን "ሶፍያ" አለቻት:: እርሷም ቅድስት ኤልሳቤጥን (የመጥምቁን እናት) ወልዳለች::

+በመጨረሻ የወለዷትን ግን "ሐና" አሏት:: ይህቺውም የፈጣሪ የሥጋ አያቱ: የድንግል ማርያምም እናቷ ትሆን ዘንድ የተመረጠችውና ስም አጠራሯ የከበረው: ዛሬ የምናከብራት እናት ናት::

+መጽሐፈ ስንክሳርን ስመለከት እንዲህ የሚል ዓረፍተ ነገር አየሁ:: "ለዛቲ ቅድስት ኢያዕመርነ ገድላቲሃ ዘትገብሮን በኅቡዕ ከመ ንዝክሮን" ይላል:: ትርጉሙም "የዚህቺን ቅድስት ገድሏንና ትሩፋቷን እንዳንዘረዝር አላወቅነውም" እንደ ማለት ነው::

+የሚገርመው አበው እንዲህ ያሉት ክብሯን መግለጹን አልጠግብ ብለው ነው:: እኛም በመጠናችን የብጽዕት ሐናን ሕይወት በአጭሩ ቀጥለን እንመልከት::

+ብጽዕት ሐና ወላጆቿ (ማጣትና ሔርሜላ) ከካህናት ወገን በመሆናቸው ልጆቻቸውን በጥንቃቄ: በሥርዓተ ኦሪት እንዳሳደጉ ይታመናል:: ቅድስት ሐናንም ለአቅመ ሔዋን እስክትደርስ ድረስ በሕጉ: በሥርዓቱ አሳድገዋታል::

+በወቅቱ በፈቃደ እግዚአብሔር ትውልዱ ከነገደ ይሁዳ የሚሆን አንድ ደግ ሰው አጩላት:: ይህ ሰው "ኢያቄም" ይባላል:: አንዳንዴም "ሳዶቅ" ወይም "ዮናኪር" እየተባለ ይጠራል:: ቅዱስ ኢያቄም ማለት ክፉ ከአንደበቱ የማይወጣው: ምጽዋትን የሚወድ: አምላከ እሥራኤልን በንጹሕ ልቡ የሚያመልክ ሰው ነበረ::

+እንደ ኦሪቱ ሥርዓት 2ቱ (ኢያቄም ወሐና) ከተጋቡ በሁዋላ ቶሎ መውለድ አልቻሉም:: ይሕ ደግሞ የወቅቱ ከባድ ፈተና ነው:: በዘመድ የከበሩ: በጠባያቸው የተመሰገኑ: መልካምንም የሚሠሩ ሰዎች ልጅ ስለሌላቸው ብቻ "ኅጡአነ በረከት" እየተባሉ ከቤተ እግዚአብሔር ይገፉ: በአደባባይም ይነቀፉ ነበር::

+ምክንያቱም በብሉይ ኪዳን ልጅ አለመውለድ እንደ ኃጢአተኛ ያስቆጥር ነበር:: ደግነቱ የወቅቱ ሊቀ ካህናት ቅዱስ ዘካርያስ (የመጥምቁ አባት) እንደ እነሱ ልጅ ያጣ በመሆኑ አብረው ይጽናኑ ነበር::

+የሆነው ሆኖ እኒህ ቡሩካን ሰዎች አምላከ እሥራኤልን ከመለመንና ከማመስገን በቀር ሌላ ትርፍ አልተገኘባቸውም:: ምንም የሞላቸውና የደላቸው ባይሆኑም ደሃን ሳያጐርሱ አይበሉም ነበር::

+ቅድስት ሐናን ግን "ቢወልዷት እንጂ አትወልድ: ድንጋይ: በቅሎ" እያሉ ጐረቤቶቿ ይሳለቁባት ነበር:: ከማልቀስ በቀር ደግሞ መልስ አልነበራትም::

+አንድ ቀን ግን ርግቦች ከልጆቻቸው ጋር ሲጫወቱ ተመልክታ "ፈጣሪ ሆይ! የእንስሳትን ማሕጸን የምትከፍት: ዕፀዋትንም ከባሕርያቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ:: እውነትም ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ስትል አለቀሰች::

+ቅዱስ ኢያቄምም ወደ ተራራ ወጥቶ ለ40 ቀናት አለቀሰ: ተማለለ:: ይህ ሲሆን 2ቱም አርጅተው ነበር:: ሐምሌ 30 ቀን ግን ነጭ ርግብ 7ቱን ሰማያት ሰንጥቃ በማሕጸነ ሐና ስታድር አዩ:: ደስ ብሏቸው ለ7 ቀናት ሱባኤ ይዘው ቅድስት ሐና እመቤታችንን ነሐሴ 7 ቀን ጸነሰቻት::

+ይሕም ለእነርሱም: ለወገኖቻቸውም ታላቅ ተድላ ሆነ:: ብጽዕት ሐና ግን ፈጣሪዋን ታከብረው ዘንድ በጐነትንና ንጽሕናን አበዛች:: ጸንሳ ሳለም ዕውራንን አበራች: ድውያንን ፈወሰች::

+የጦሊቅ ልጅ በሞተ ጊዜም እያለቀሰች ስትዞረው ጥላዋ ቢያርፍበት አፈፍ ብሎ ተነስቶ:- "ሰላም ለኪ እሙ ለፀሐየ ጽድቅ" ብሎ ድንግል ማርያምን::
"ወሰላም ለኪ እምሔውቱ ለዘገብረ ሰማየ ወምድረ" ብሎ ቅድስት ሐናን አመስግኗል:: ትርጉሙም ድንግልን "የፀሐየ ጽድቅ እናቱ": ሐናን "ሰማይና ምድርን ለፈጠረ አያቱ" ማለት ነው::

+ይህንን ያዩ አይሁድ ቅድስት ሐናን ሊገድሉ ብዙ ጊዜ ሞክረዋል:: ግን መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል አልፈቀደላቸውም:: ግንቦት 1 ቀንም የሰማይና የምድር ንግስትን ሊባኖስ ተራራ ላይ ወልዳ ሽሙጥን ከሁላችንም አራቀች::

+ስሟን "ማርያም-የአምላክ ስጦታ" ብለው ሰይመው ለ3 ዓመታት አሳድገዋታል:: የሚገርመው በ3ቱ ዓመታት ውስጥ ቅድስት ሐና ድንግል ማርያምን ከክንዷ አውርዳት አታውቅም ነበር:: አንድ ጊዜም መላእክት ወስደውባት ፍጹም አልቅሳለች:: ሁዋላ ግን መልሰውላታል::

+ሌላኛው የሚደንቀው እግዚአብሔር የዓለም ውዱን ስጦታ እመ ብርሃንን ሰጣቸው:: እነርሱም ይሕችን ውድ ስጦታ ሳይሰስቱ ለፈጣሪ መለሱለት::
"እምቅድሜክሙ አልቦ::
ወእምድኅሬክሙ አልቦ::
ከመዝ መስዋዕት ለእግዚአብሔር ዘወሃቦ::" እንዲል::

+ቅድስት ሐና ድንግል ወደ ቤተ መቅደስ ከገባች በሁዋላ የእናትነት ፍቅሯ እያገበራት ለ5 ዓመታት እየተመላለሰች ትጐበኛት: ትስማት ነበር:: እመቤታችን 8 ዓመት በሞላት ጊዜ ግን የእግዚአብሔር ጥሪ ወደ ቅድስት ሐና ደረሰ::

+ከክርስቶስ ልደት 8 ዓመታት አስቀድማ ብጽዕት እናት ሐና በዚህች ቀን ዐረፈች:: ትንሽ ቆይቶም ባለቤቷ ቅዱስ ኢያቄም ተከተላት እኛም ልጆቿ "ብጽዕት ሐና ብጽዓን ይገባሻል!" እያልን እናመስግናት::

+ሊቃውንቱ ለእርሷ እንዲህ ብለዋልና:-
"ሰላም ለኪ ለጸሎተ ኩሉ ምዕራጋ::
ከመ አስካለ ወይን ዲበ ሐረጋ::
ሐና ብጽዕት ተፈስሒ እንበለ ንትጋ::
እስመ ረከብኪ ሞገሰ ወአድማዕኪ ጸጋ::
እምሔውተ አምላክ ትኩኒ በሥጋ::" (አርኬ)


+" ባሕረ ሐሳብ "+

+ዳግመኛ በዚህ ቀን: በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ባሕረ ሐሳብ በዓለማቀፍ ደረጃ ተቀባይነትን አግኝቷል:: ሊቁ ቅዱስ ድሜጥሮስ (የግብጽ 12ኛ ፓትርያርክ) መንፈስ ቅዱስ ቀመረ ባሕረ ሐሳብን ገልጾለት በዓለም ላሉ ሊቃነ ዻዻሳት ልኮላቸው በዚህች ዕለት በሮም ከተማ ተሰበሰቡ::

+ሊቃውንትም ሐዋርያት ካስተማሩት ጋር ተመሳሳይ ሆኖ ቢያገኙት በደስታ ተቀብለውታል:: እነሆ እስከ ዛሬ ድረስ ለ1,700 ዓመታት ቤተ ክርስቲያን እየተገለገለችበት ይገኛል::
https://t.me/enabib


መስቀል ኃይልነ፤
መስቀል ጽንእነ፤
መስቀል ቤዛነ፤
መስቀል መድኃኒተ ነፍስነ።
አይሁድ ክህዱ ንህነሰ አመነ፤
ወእለ አመነ በኃይለ መስቀሉ ድኅነ።


††† እንኳን ለአበው ቅዱሳን "318ቱ ሊቃውንት" ዓመታዊ የጉባኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ጉባኤ ኒቅያ †††

††† በዚህች ዕለት (ኅዳር 9 ቀን) በሃገረ ኒቅያ በእመቤታችን እና በአምላክ ልጇ የሚያምኑ 318ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት ተሰብስበዋል::

የሊብያው ሰው አርዮስ ጌትነት ገንዘቡ የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ክዶ ሊያስክድ ሲሯሯጥ በፈቃደ እግዚአብሔር: በጻድቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ጥሪ: 2348 ምሑራን ከመላው ዓለም ተሰበሰቡ::

ጥሪው የተላለፈው በወርኀ ሚያዝያ ሲሆን በመንገድ ችግር ሁሉም ተጠቃለው ኒቅያ የገቡት መስከረም 21 ቀን ነበር:: ከተሰበሰበው ብዙ ሰው መካከል የአበውን ደቀ መዛሙርት ሳንቆጥር ሃይማኖታቸው የቀና: ምግባራቸው የጸና 318ቱ አበው ሊቃውንት ተገኙ::

እነዚህ አባቶች "ሊቃውንት" ሲባሉ እንዲሁ በእውቀት ብቻ የበሰሉ እንዳይመስሉን:: 318ቱ አበው እኩሎቹ በዘመነ ሰማዕታት እጅና እግራቸውን የተቆረጡና ለሃይማኖታቸው ብዙ ዋጋ የከፈሉ ናቸው::

እኩሎቹ ደግሞ በገዳማዊ ሕይወት ያጌጡ: ፍቅረ ክርስቶስ በውስጣቸው የሚነድ: የመንፈስ ቅዱስ ቤት ናቸው:: እስኪ እናውቃቸው ዘንድ የጥቂቶችን ማንነት በስምና በመገለጫ እንመልከት:-
1.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ (በዘመነ ሰማዕታት ለ22 ዓመት ሲቆራርጡት ኖረው በጉባኤው ላይ የተገኘው ያለ እጅ: እግር: ጀሮ: ከንፈር: ቅንድብ ነው)
2.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ (ስለ ቀናች እምነት ለ50 ዓመታት የተጋደለና ለ15 ዓመታት በስደት የኖረ ነው)
3.ቅዱስ እለእስክንድሮስ ሊቅ (ከሰማይ ብርሃን ይወርድለት የነበረ አባት ነው)
4.ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ (በጸሎቱ አጋንንትን ያንቀጠቀጠ: ነፍሳትን ከሲዖል የቀማና ከከዊነ እሳት የደረሰ አባት ነው)
5.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘአርማንያ (ስለ ቀናች እምነት መጸዳጃ ጉድጓድ ውስጥ ለ15 ዓመታት ተጥሎ የኖረ ሰማዕት ነው)
6.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሜራ (ከሕጻንነቱ የተቀደሰ: በበርሃ የተጋደለ: በዘመነ ሰማዕታት ብዙ መከራን የተቀበለ አባት ነው)
7.ቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን (በደግነቱ ሙታንን ያስነሳ: ወንዝን በጸሎቱ ያቆመ: በንጽሕና የተጋደለ አባት ነው)
8.ቅዱስ ሶል ጴጥሮስ (ቅዱሱን ንጉሥ ያጠመቀ:
ቁስጥንጥንያን በወንጌል ያበራ ሊቅ ነው)
9.ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ (ስለ ቀናች እምነቱ ብዙ ግፍ የደረሰበትና በስደት ያረፈ አባት ነው)

ለአብነት እንዲሆኑን እነዚህን አነሳን እንጂ 318ቱም ሊቃውንት ስለ ቤተ ክርስቲያን ተግተው የተጋደሉ: ብዙ ዋጋም የከፈሉ አባቶች ናቸው::

በወቅቱ ታዲያ ቤተ ክርስቲያንን የበጠበጡ ብዙ መናፍቃን ቢኖሩም የአርዮስ ግን ከመጠኑ አለፈ:: የእርሱ ኑፋቄ (ፈጣሪያችንን ፍጡር ነው ማለቱ) መነሻው ከእርሱ በፊት ነው:: መናፍቃን ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ ቤተ ክርስቲያንን ሲያውኩ መኖራቸው ግልጽ ነው::

በተለይ ደግሞ ቢጽ ሐሳውያንና ግኖስቲኮች የወለዷቸው እሾሆች አባቶቻችንን እንቅልፍ ነስተው ነበር:: የሚገርመኝ በዘመኑ እንደ ነበሩ መናፍቃን ኃይለኝነት የእኞቹ ከዋክብት ሊቃውንት ባይኖሩ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ያሳስብ ነበር::

ግን እግዚአብሔር ለሁሉ እንደሚገባ ያዘጋጃልና አበው ብርቱ መናፍቃንን በብርቱ መንፈሳዊ ክንድ እያደቀቁ ከጐዳና አስወገዷቸው:: የዛሬውን ደካማ ትውልድ ደግሞ የአርዮስ ልጆች 2 (3) ጥቅስ ይዘው ሲያደናብሩት ይውላሉ::

ሐረገ መናፍቃን በርጉም ሳምሳጢ ጳውሎስ: በመርቅያንና በማኒ ይጀምራል:: በእርግጥ አርጌንስ እና የግብጹ ቀሌምንጦስም ተቀላቅለዋቸዋል:: ርጉም ሳምሳጢ ድያድርስን በኑፋቄ ወልዶታል:: ድያድርስ ሉቅያኖስን: ሉቅያኖስ ደግሞ አርዮስን ወልደዋል::

ይህ አርዮስ እጅግ ተንኮለኛ በመሆኑ ልክ እንደ ዘመኑ መሰሎቹ ግጥምና ዜማ እየጻፈ በየመንገዱ እያደለ: በየቤቱ እየሰበከ ብዙዎችን በኑፋቄው በከለ:: በመጀመሪያ ተፍጻሜተ ሰማዕት
ቅዱስ ጴጥሮስ (አስተማሪው) መከረው:: ባይሰማው ከአንዴም ሁለት ጊዜ አወገዘው::

ቆይቶ ሰነፉ ጳጳስ አኪላስ ቢፈታውም ሊቁ ቅዱስ
እለእስክንድሮስ እንደ ገና አወገዘው:: እንደ አርዮስ ሐሳብ መድኃኒታችን ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ አይደለም (ሎቱ ስብሐት!) ማለት ክርስትናን ከሥሩ ፈንቅሎ መጣል ነው::

ስለ ክርስቶስ እግዚአብሔርነት ብሉይም ሐዲስም እየመሰከሩ (ኢሳ. 9:6, መዝ. 46:5, 77:65, ዘካ. 14:4, ዮሐ. 1:1, 10:30, ራዕይ. 1:8, ሮሜ. 9:5) አርዮስና የዛሬ መሰሎቹ አንዲት ጥቅስ ይዘው ክርስትናን ከመሠረቱ ለመናድ መሞከራቸው በእርግጥም ከሰይጣን መላካቸውን ያሳያል::

በወቅቱም በመወገዙ "ተበደልኩ" ብሎ የጮኸው አርዮስ ከ2ቱ አውሳብዮሶች ባልንጀሮቹ (ዘቂሣርያና ዘኒቆምድያ) ጋር ሆኖ ወደ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ሔዶ ከሰሰ:: ቅዱሱ ንጉሥም የጉዳዩን ክብደት ተመልክቶ የዓለም ሊቃውነት ይሰበሰቡ ዘንድ አዘዘ::

ከሚያዝያ 21 እስከ መስከረም 21 ተጠቃለው ገቡ:: በ325 ዓ/ም (በእኛው በ318 ዓ/ም) ለ40 ቀናት የሚቆይ ሱባኤን ያዙ:: ሱባኤውን ሲጨርሱም በ4ቱ ፓትርያርኮች (እለእስክንድሮስ: ሶል ጴጥሮስ: ዮናክንዲኖስና ኤዎስጣቴዎስ) መሪነት: በእለእስክንድሮስ ሊቀ መንበርነት: በአትናቴዎስ ጸሐፊነት ጉባኤው ተጀመረ::

በጉባኤው ሙሉ ስልጣን በሰማይ ከፈጣሪ: በምድር ከንጉሡ የተሰጣቸው አበው አርዮስን ተከራክረው ከነ ጀሌዎቹ ምላሽ አሳጡት:: ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ: ሥግው ቃል: ራሱም እግዚአብሔር መሆኑን አስረዱት:: በጉባኤው መጨረሻም:-
1.አልመለስም በማለቱ አርዮስን አወገዙ::
2.ጸሎተ ሃይማኖትን "ለመንግስቱም ፍጻሜ የለውም" እስከሚለው ድረስ ተናገሩ::
3.ፍትሐ ነገሥትን ሥጋዊና መንፈሳዊ ብለው አዘጋጁ::
4.ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እንደሚገባ አደራጁ::
5.በስማቸው የሚጠራ አንድ ቅዳሴን ደረሱ::

ይህ ሁሉ ሲሆን መድኃኒታችን ክርስቶስ 319ኛ ሆኖና ገሊላዊ ጳጳስን መስሎ ሁሉን አከናውኖላቸዋል:: አባቶችም ሥራቸውን
ከጨረሱ በኋላ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስን ባርከው ወደየ ሃገረ ስብከታቸው ተመልሰዋል::

††† በየዘመኑም ዐርፈው ለክብረ መንግስተ ሰማያት በቅተዋል:: እኛም እነሆ "አባቶቻችን:
መምሕሮቻችን:
መሠረቶቻችን:
ብርሃኖቻችን:
ምሰሶዎቻችን" እያልን እናከብራቸዋለን::

††† አምላከ ቅዱሳን ሊቃውንት በጸሎታቸው እኛንም: ቤተ ክርስቲያናችንንም ከክፉ ጠላት ይጠብቅልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

††† ኅዳር 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱሳን 318ቱ ሊቃውንት
2.ቅዱስ እለእስክንድሮስ ሊቅ
3.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
4.አባ ይስሐቅ ሊቀ ጳጳሳት
5.ሊቁ አካለ ወልድ

††† ወርሐዊ በዓላት
1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ሁሉ አባት)
2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ
3.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን
4.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ
5.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ

††† "እውነት እላቹሃለሁ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል:: በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል:: ደግሞ እላቹሃለሁ ከእናንተ ሁለቱ በምድር በማናቸውም በሚለምኑት ነገር ሁሉ ቢስማሙ በሰማያት ካለው ከአባቴ ዘንድ ይደረግላቸዋል:: ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና::" †††
(ማቴ. ፲፰፥፲፰)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††https://t.me/enabib


ሊቁ አካለ ወልድ በረከታቸው ይደርብን


በነገው እለት የሚታሰቡትን ሰለስቱ ምዕትን እና ሊቁ አካለ ወልድን እናስባቸው


🌻🌻🌻🌻🌻

      ምጽዋት

የማትፈልገውን ሳይሆን ለአንተ ምርጥ የምትለውን መስጠት ልመድ፡፡ የአገልግሎት ዘመኑን የጨረሰ ልብስ፣ ለመመገብ አስቸጋሪ የሆነ፣ የሻገተ ወይንም የደረቀ ምግብ መስጠት የተለመደ በሆነበት ዘመን ላይ ስላለህ የምታደርገውን ሁሉ ተጠንቅቀህ አድርግ፡፡ አንተ የማትለብሰው ስለማይለበስልህ ነው፡፡ የማትበላው በጤናህ ላይ ችግር ስለሚያስከትልብህ ነው፡፡ ታድያ ወንድምህስ? የምትሰጠው ለሕመም የሚዳርገውን ነው? መሆን የለበትም፡፡ ማስቀመጫ እንዳጣ መጣያ አታርገው ይልቁንም ለወንድምህ ከምትበላው አካፍለው፡፡ ከምትለብሳቸው ሁለት ልብሶች አንዱን ስጠው፡፡ የሚጎዳውን ብዙ ነገር ከምትሰጠው የሚጠቅም ትንሽ ነገር ስጠው፡፡ ለአንተ የምትመኘውን ጥራት ለወንድምህም አድርግ፡፡ “ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው” ያለውን የእግዚአብሔር ቃል መለስ ብለህ አስብና፣ የምትሰጠውን ጎጂ ነገር ለክርስቶስ እንደምትሰጠው ተረዳ፡፡ ከዚሁ ጋር አቤልና ቃየል ለእግዚአብሔር ያቀረቡት መሥዋዕት እንዴት እንደነበረ አስብ፡፡ “አቤልም ደግሞ ከበጎቹ በኩራትን ከስቡ አቀረበ፡፡ እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ፡፡” (ዘፍ 4፣4) ለምን መረጠለት? ብትል ፣ ካለው ሁሉ መርጦ የተሻለውን ስላቀረበ ነው፡፡ በሐዋርያት ሥራ 4፣34-35 ላይ ሠፍሮ የሚገኘውን የሐዋርያቱ ሕይወት ምን
ይመስል እንደነበረ የሚናገረውን ቃል አስተውለህ አንብበውና የአንተ ምጽዋት የአንተ ሥጦታ የትኛው ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ራስህን ጠይቅ፡፡ ክብርን ለመፈለግ አትስጥ በአንደበትህም ይሁን በልብህ፣ በስሜትህም ይሁን በሃሳብህ የራስህ ነገር ኖሮህ እንደሰጠህ አስበህ አትኩራራ፡፡ ለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ የተናገረውን እንደ ትልቅ ማስረጃ ተጠቀም፡፡ “አንተ እድትበልጥ ማን አድርጎሃል? ያልተቀበልኸውስ ምን አለህ? የተቀበልክ ከሆነ ግን እንዳልተቀበልክ የምትመካ ስለምንድር ነው?” (1 ቆሮ 4፣7) ስለዚህ ስጦታ ሁሉ ከእግዚአብሔር ተቀብለን የምንሠጠው እንጂ የራሳችን እንደሆነ በከንቱ የምንመካበት አይደለም፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
+++


✝እንኳን አደረሰነ!

✞በዓለ ቅዱሳን፦

✿፬ቱ እንስሳ ኪሩቤል
✿አፍኒን ሊቀ መላእክት
✿ቆስጠንጢኖስ ጻድቅ
✿ኪሮስ ገዳማዊ (ቅዳሴ ቤቱ)
✿ቅፍሮንያ ወልደ መኮንን
✿እግዚእ ክብራ ኢትዮጵያዊት
✿ዮሐንስ ሊቀ ጳጳሳት
✿ወመስቀል ዕጸ ሕይወት

ኅዳር ፰፦

✝ሰላም ለክሙ ፬ቱ እንስሳ ኪሩቤል፤
እለ ትጸውሩ ሰማየ መንበሮ ለልዑል፤
እንበለ አርምሞ ትጸርሑ ወትባርኩ በቃል፤
ምስለ እህትክሙ ማርያም ወላዲተ አምላክ ድንግል፤
አፍራሠ እሳት ንዑ ለምሕረት ወሣሕል!

✝ሰአሉ ለነ ቅዱሳን አርባዕቱ እንስሳ፤
ገጸ ሰብእ ወገጸ እንስሳ ገጸ ንሥር ወገጸ አንበሳ፤
ወኪሮስ ጻድቅ እንተ አልብከ አበሳ፤
አፍኒን ዘትቄድስ ለመንበረ መንግሥት በከርሣ፤
ቅፍሮንያ ወቆስጠንጢኖስ ፍቁረ መስቀል ወከኒሳ!

(አርኬ - ዝክረ ቅዱሳን ርቱዓነ ሃይማኖት)

https://t.me/enabib


+የግብጽ አረማውያን ገዢዎች እንደ ትልቅ ሥራ የሚያዩት አድባራትን ማቃጠል: ገዳማትን መመዝበር ነውና እርሱም ለዚሁ ሥራ ተነሳ:: ሠራዊትን አስከትቶ በሠረገላው ተጭኖ ወደ አንድ ገዳም ደረሰ:: ልክ የገዳሙን መሬት ሲረግጥ ግን በአንዴ ልቡናው ተሰበረ::+ሠራዊቱን ወደ ከተማ አሰናብቶ እርሱ ብቻውንወደ ገዳሙ ዘለቀ:: ወደ አበ ምኔቱም ቀርቦ ሰገደላቸውና እንዲያጠምቁት ተማጸናቸው:: እርሳቸውም አስተምረው አጠመቁት:: በዚያውም መንኖ መነኮሰ::

+ለዘመናትም በጠባቡ መንገድ ተጋድሎ ከጸጋ (ከብቃት) ደረሰ:: በአካባቢው ሰውና እንስሳትን የፈጀውን ዘንዶም ባሪያ አድርጐ ለ10 ዓመታት ገዝቶታል:: ከብዙ ተጋድሎ በሁዋላም በዚህ ቀን ዐርፏል::

=>አምላከ ቅዱሳን መላእክት እነርሱን ለረድኤት ይላክልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

=>ኅዳር 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱሳን 4ቱ እንስሳ (ኪሩቤል)
2.ቅዱስ አፍኒን ሊቀ መላእክት
3.አባ ቅፍሮንያ ጻድቅ
4.ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ንጉሥ (ዘምስለ ቅዱስ መስቀል)
5.ቅድስት እግዚእ ክብራ

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
2.አባ ብሶይ (ቢሾይ)
3.አቡነ ኪሮስ
4.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
5.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)

=>+"+ በዙፋኑም መካከል: በዙፋኑም ዙሪያ በፊትና በሁዋላ ዓይኖች የሞሏቸው አራት እንስሶች ነበሩ:: ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል:: ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል:: ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው:: አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል:: አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሏቸው:: +"+ (ራዕይ. 4:6)

   >https://t.me/enabib


✝✞✝ እንኩዋን ለቅዱሳን ኪሩቤል (ዐርባዕቱ እንስሳ): ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ወአባ ቅፍሮንያ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✞✝

+"+ ዐርባዕቱ እንስሳ +"+

=>እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን ሲፈጥራቸው በነገድ መቶ (100): በክፍለ ነገድ አሥር (10) አድርጉዋቸዋል:: አቀማመጣቸውንም በ3 ሰማያትና በ10 ከተሞች (ዓለማት) አድርጉዋል::

+መላእክት ያሉባቸው ከተሞች ከታች ወደ ላይ 'ኤረር: ራማና ኢዮር' ይባላሉ:: አሥሩ ክፍለ ነገድ ደግሞ ከነ አለቆቻቸው ይህንን ይመስላሉ:-

1.አጋእዝት (የቀድሞ አለቃቸው ሳጥናኤል: አህን የተረፉት በቅዱስ ሚካኤል ሥር ናቸው)
2.ኪሩቤል (አለቃቸው ኪሩብ)
3.ሱራፌል (አለቃቸው ሱራፊ)
4.ኃይላት (አለቃቸው ሚካኤል)
5.አርባብ (አለቃቸው ገብርኤል)

6.መናብርት (አለቃቸው ሩፋኤል)
7.ስልጣናት (አለቃቸው ሱርያል)
8.መኩዋንንት (አለቃቸው ሰዳካኤል)
9.ሊቃናት (አለቃቸው ሰላታኤል)
10.መላእክት (አለቃቸው አናንኤል) ናቸው::

+ከእነዚህም *አጋእዝት: *ኪሩቤል *ሱራፌልና *ኃይላት መኖሪያቸው በኢዮር (በ3ኛው ሰማይ) ነው:: *አርባብ: *መናብርትና *ስልጣናት ቤታቸው ራማ (2ኛው ሰማይ) ነው:: *መኩዋንንት: *ሊቃናትና *መላእክት ደግሞ የሚኖሩት በኤረር (በ1ኛው) ሰማይ ነው::

+መላእክት ተፈጥሯቸው እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ ነው:: አይራቡም: አይጠሙም: አይዋለዱም: አይሞቱም:: ተፈጥሯቸውም ረቂቅ ነው:: ተግባራቸው ዘወትር "ቅዱስ: ቅዱስ: ቅዱስ" እያሉ ፈጣሪያቸውን ማመስገን ነው:: ምግባቸውም ይሔው ነው::

+ዕረፍት ብሎ ነገርን አያውቁም:: "አኮቴቶሙ ዕረፍቶሙ: ወዕረፍቶሙ አኮቴቶሙ" እንዲል:: በተጨማሪም መልአክ ማለት ተላላኪ (አገልጋይ) ነውና ከፈጣሪ ወደ ሰው ልጆች ለምሕረትም: ለመዓትም ይላካሉ::

+ምሕረትን ያወርዳሉ:: ልመናን ያሳርጋሉ:: ቅጡ ሲባሉም ይቀጣሉ:: ስነ ፍጥረት (አራቱ ወቅቶች) እንዳይዛቡ ይጠብቃሉ::

*ዘወትርም ስለ ሰው ልጆች ያማልዳሉ (ዘካ. 1:12)
*ምሥጢርን ይገልጣሉ (ዳን. 9:21)
*ይረዳሉ (ኢያ. 5:13)
*እንዳንሰናከል ይጠብቃሉ (መዝ. 90:11)
*ያድናሉ (መዝ. 33:7)
*ስግደት ይገባቸዋል (መሳ. 13:20, ኢያ. 5:13, ራዕ. 22:8)
*በፍርድ ቀንም ኃጥአንን ከጻድቃን ይለያሉ (ማቴ. 25:31)
*በአጠቃላይ ለሰው ልጆች ሕይወትና ድኅነት ሲባል ከፈጣሪያቸው የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ሲጠብቁና ፈቃዱን ሲፈጽሙ ይኖራሉ::

+ከእነዚህ ቅዱሳን መላእክት መካከል ደግሞ ትልቁን ሥፍራ ዛሬ የምናከብራቸው ነገደ ኪሩቤል (ዐርባዕቱ እንስሳ) ይይዛሉ:: መንፈሳውያን ከመሆናቸው በላይ መንበረ ጸባኦትን እንዲሸከሙ ስላደላቸው ክብራቸው ታላቅ ነው:: ከመላእክት ወገንም ቅሩባን እነርሱ ናቸው::

+ዘወትርም ስለ ፍጥረታት (ሰዎች: እንስሳት: አራዊትና አዕዋፍ) ምሕረትን ይለምናሉ:: ለዚህም ነው በ4 እንስሳት (በሰው: በንስር: በላምና በአንበሳ) መልክ የተሳሉት:: ቅዱስ መጽሐፍም ስለ እነርሱ ብዙ ይላል:: (ሕዝ. 1:5, ራዕ. 4:6, ኢሳ. 6:1)

+በተለይ ግርማቸው እንደሚያስፈራ ተጽፏል:: "ምሉዓነ ዐዕይንት - ዐይንን የተሞሉ" ይላቸዋል:: ይህንንም መተርጉማን "ምሥጢር አዋቂነታቸውንና ግርማቸውን ያጠይቃል" ሲሉ ተርጉመውታል::

+ዐርባዕቱ እንስሳን 4 ሆነው በስዕል ብናያቸውም "ከመ ርዕየተ እለ ቄጥሩ" እንዲል እያንዳንዱ ከወገብ በላይ አራት በመሆናቸው ተሸካሚዎቹ 16 መልክ አላቸው:: በ2 ክንፋቸው ፊታቸውን: በ2ቱ እግራቸውን ሸፍነው በ2 ክንፋቸው ይበራሉ:: ይህም ብዙ ምሥጢር ሲኖረው ዋናው ግን አርአያ ትእምርተ መስቀል ነው::

+"4ቱ" እንስሳ (ኪሩቤል) በሐዲስ ኪዳንም ልዩ ክብር አላቸው:: 4ቱ ወንጌል ሲጻፍ እየተራዱ ስላጻፉ በስማቸው ተሰይሟል:: ቅዱስ ማቴዎስን ገጸ ሰብእ: ቅዱስ ማርቆስን ገጸ አንበሳ: ቅዱስ ሉቃስን ገጸ ላህም: ቅዱስ ዮሐንስን ገጸ ንስር እየተራዱ ስላጻፏቸው እነሆ እስከ ዛሬ ድረስ "ዘብእሲ ማቴዎስ": "ዘአንበሳ ማርቆስ": "ዘላሕም ሉቃስ" እና "ዘንስር ዮሐንስ" እየተባሉ ይጠራሉ::

+እነዚህ ቅዱሳን መላእክት የሰው ልጆችን ስለ መራዳታቸውም በብዙ ገድላትና ድርሳናት ላይ ተጽፏል:: የራሳቸውን "ድርሳነ ዐርባዕቱ እንስሳን" ጨምሮ በገድለ አባ መቃርስና በገድለ አባ ብስንድዮስ ላይ በስፋት ግብራቸው ተጽፏል::

+እኛም ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ክብራቸውን: ረድኤታቸውንና ምልጃቸውን አምነን ዘወትር እናከብራቸዋለን:: አባቶቻችን እንዲህ እያሉ እንደ ጸለዩ:-

"ሰላም ለክሙ ኪሩባውያን አፍራሱ:
ለመሐይምን ወጻድቅ እንተ ወርቅ አክሊለ ርዕሱ:
ኀበ ዝ አምላክ ለእለ ትጸውርዎ በአትሮንሱ:
ለእለ ጌገዩ ወለእለሂ አበሱ:
ሰአሉ መድኃኒተ ወምሕረተ ኅሡ::" (አርኬ)

+" ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ "+

=>ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ለቤተ ክርስቲያን የፈፀመውን መልካም ተግባር ያሕል መሥራት የቻለ ንጉሥ በሐዲስ ኪዳን የለም:: ጻድቁ ንጉሥ ከቅድስት እናቱ እሌኒና ከአረማዊ አባቱ ቁንስጣ በበራንጥያ ተወለደ::

+ዘመኑ ዘመነ ዐጸባ /የመከራ ጊዜ/ ወይም የሰማዕታት ዘመን በመሆኑ ክርስቲያኖች በግፍ የሚጨፈጨፉበት ወቅት ነበር:: ክርስቲያኖችን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት በተደረገው የ40 ዓመታት ዘመቻ አብያተ-መቃድስና መጻሕፍት ተቃጠሉ::
ብዙዎቹ በየበርሃው ተሰደዱ:: ሚሊየኖች በግፍ አለቁ::

+የዚሕን ዘመን መከራ በውል ያልተረዳ ሰው ቅዱስ ቆንጠንጢኖስን ሊያከብር አይችልም:: ምክንያቱም ይህን የመከራ ዘመን በፈቃደ እግዚአብሔር አስቁሞ: ቀርነ-ሃይማኖት የቆመው: ብዙ ሥርዓት የተሠራው: ቤተ ክርስቲያንም ያበራችው በዘመኑ ነውና::

+ቅዱሱ ንጉሥ ለሁሉም ነቢያት: ሐዋርያትና ሰማዕታት አብያተ ክርስቲያናትን ራሱ በመሠረታት በቁስጥንጥንያ አንጿል:: በዘመኑ ቤተ ክርስቲያን በሰላም ኖራለት: በኃይለ መስቀሉ ጠላት ጠፍቶለት ኑሮ በዚህች ቀን አርፏል::

+ይህቺ ቀን ታላቁ ንጉሥ በፈለገ ኮቦር ቅዱስ መስቀልን የተመለከተባት ናት:: መክስምያኖስን ሊወጋ ወደ ሮም በተጉዋዘ ጊዜ በሰማይ ላይ መድኅን መስቀል ተዘርግቶ በላዩ ላይ "ኒኮስጣጣን" የሚል በዮናኒ ልሳን ተጽፎበት ተመልክቷል::

+ይህንንም "በዚህ ጠላትህን ድል ታደርጋለህ" ማለት ነው ብለው ተርጉመውለታል:: እርሱም በጋሻው: በጦሩ: በሰይፉ: በፈረሱ ላይ የመስቀል ምልክትን አድርጐ ማሕደረ ሰይጣን መክስምያኖስን ድል ነስቶታል:: እኛንም በሞገሰ መስቀሉ ይጠብቀን::

+"+ አባ ቅፍሮንያ ጻድቅ +"+

=>ይህ ቅዱስ ሰው በቀደመ ሕይወቱ አረማዊ ነበር:: ነገር ግን በውስጡ ቅንነት ተገኝቶበታልና እግዚአብሔር በቸር አጠራሩ ወደ ቤቱ አመጣው:: አባቱ አረማዊ: በዚያውም ላይ አገረ ገዢ ነበርና ለቅፍሮንያ ይህንኑ እያስተማረ አሳድጐታል::

+አንድ ቀን ግን ፈጣሪ ጥሪውን ላከለት:: ይኸውም ገና ወጣት ሳለ የገዳም አበው ያዩትና ትንቢት ይናገሩለታል:: "ይህ ሰው በጐ ክርስቲያን: ምርጥ ዕቃም ይሆናል" ሲሉት እንኩዋን ሌሎቹ ለእርሱ ለራሱም ምንም አልመሰለውም ነበር:: በዚህ መንገድ (በአረማዊነቱ) ዓመታት አልፈው ቅፍሮንያ የከተማው መኮንን (አገረ ገዢ) ሆነ::


✝እንኳን አደረሰነ!

✞በዓለ አበው ቅዱሳን፦

✿ጊዮርጊስ ልዳዊ
✿ጊዮርጊስ እስክንድርያዊ
✿ሚናስ ዘተመይ
✿ናኅርው ዘፍዩም
✿ገብረ እንድርያስ ዘወለቃ
✿ዳንኤል ዘኀረይክዋ
✿መርቆሬዎስ ወዮሐንስ
✿ዘኖቢስ ወዘኖብያ

ኅዳር ፯፦

✝ሰላም ለጊዮርጊስ ኮከበ ፋርስ ወልዳ፤
ርዕሰ አዕዋፍ ኅሩያን ወንስረ ሃይማኖት ጸዐዳ፤
ዘተመትርዎ ወቀሰፍዎ በይቡስ አነዳ፤
በዛቲ ዕለት ዘምስለ አምሀ ወጋዳ፤
እሰግድ ለንግሡ ዘምስለ አቢብ ወበብኑዳ!

✝መክብበ ሰማዕታት ክቡራን ጊዮርጊስ ልዳዊ፤
ወሰማዕት ሐዲስ ጊዮርጊስ እስክንድርያዊ፤
ሚናስ ወናሕርው ወዳንኤል መርዓዊ፤
ዘኖቢስ ወዘኖብያ መርቆሬዎስ ጻማዊ፤
ዮሐንስ ሰንቃዊ ወገብረ እንድርያስ ሰግላዊ!

(አርኬ - ዝክረ ቅዱሳን ርቱዓነ ሃይማኖት)

✝እንኳን አደረሰነ!

✞በዓለ አበው ቅዱሳን፦

✿ጊዮርጊስ ልዳዊ
✿ጊዮርጊስ እስክንድርያዊ
✿ሚናስ ዘተመይ
✿ናኅርው ዘፍዩም
✿ገብረ እንድርያስ ዘወለቃ
✿ዳንኤል ዘኀረይክዋ
✿መርቆሬዎስ ወዮሐንስ
✿ዘኖቢስ ወዘኖብያ

ኅዳር ፯፦

✝ሰላም ለጊዮርጊስ ኮከበ ፋርስ ወልዳ፤
ርዕሰ አዕዋፍ ኅሩያን ወንስረ ሃይማኖት ጸዐዳ፤
ዘተመትርዎ ወቀሰፍዎ በይቡስ አነዳ፤
በዛቲ ዕለት ዘምስለ አምሀ ወጋዳ፤
እሰግድ ለንግሡ ዘምስለ አቢብ ወበብኑዳ!

✝መክብበ ሰማዕታት ክቡራን ጊዮርጊስ ልዳዊ፤
ወሰማዕት ሐዲስ ጊዮርጊስ እስክንድርያዊ፤
ሚናስ ወናሕርው ወዳንኤል መርዓዊ፤
ዘኖቢስ ወዘኖብያ መርቆሬዎስ ጻማዊ፤
ዮሐንስ ሰንቃዊ ወገብረ እንድርያስ ሰግላዊ!

(አርኬ - ዝክረ ቅዱሳን ርቱዓነ ሃይማኖት)
https://t.me/zikirekdusn


💠"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"
/(ማቴ ፫:፫/)

✝እንኳን አደረሰን!!

ለ ፳፻፲፯ የቤት ሥራ የሚሆኑ ፭ መልእክቶች

፩.ለጸሎት ተነሱ
፪.ክርስትናን መኖርን እንጀምር
፫.የእውነት ንስሐ ያስፈልገናል
፬.ካቆሸሸን ማኅበራዊ ሚዲያ ጥቂት እንራቅ
፭.ትልቁ መከራ እንዳያገኘን

ነቢያት ወሐዋርያት፥ ጻድቃን ወሰማዕት፥ ደናግል ወመነኮሳት፥ አዕሩግ ወሕጻናት፥ ገዳማውያን ወሊቃውንት፥ ሰአሉ ለነ ኩልክሙ ቅድመ መንበሩ ለጸባኦት።

✝ዝክረ ቅዱሳን ላልደረሳቸው  እናድርስ እናስፋ ስለ ሃገራችን እንጸልይ ንስሃ እንግባ!!

✝ 5 ነገሮችን በደንብ ያዙ።
    1, 🛑አላማ

    2 ,🛑እምነት

    3,🛑ጥረት

    4 🛑ጥንቃቄ

     5🛑ጽናት
=>እነዚህን ያዟቸው ተጠቀሙባቸዉ ኑሯቸው።

✝9ኙ የቅድስና መንገዶች

፩👉ሃይማኖት
፪👉ጾም
፫👉ጸሎት
፬👉ስግደት
፭👉ምጽዋት
፮👉ፍቅር
፯👉ትህትና
፰👉ትዕግስት
፱👉የዋህነት


ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት)

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::
       አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
https://t.me/enabib

20 last posts shown.