✟እንዘምር✟


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


✟✟✟በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን✟✟✟
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ስርአቱን የጠበቀየመዝሙር ግጥምናዜማውን ማግኘት ከፈለጉ ቻናላችንን ይጎብኙት✟
"ድምፁ መልካም በሆነ
ፀናፅል አመስግኑት
እልልታ ባለዉ
ፀናፅል አመስግኑት።"ሀሌሉያ
መዝ150÷5
ዮቲዩብ ቻነል ይቀላቀሉhttps://www.youtube.com/@enzmrbellta

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


'https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk' rel='nofollow'>♥️🌹ጋብቻ ምን ማለት ነው⁉️🌹
ጋብቻ እና የዘር ሐረግ ምን ያገናኛቸዋል⁉️
ጋብቻ የሚፈቀደው ከስንት ዓመት ጀምሮ ነው⁉️
ሴት ሙሽራ ከወንድ ሙሽራ ቀኝ ለምን ትሆናለች⁉️
🌹ሙሽሮች በጫጉላ ጊዜያቸው ለምን አይጾሙም⁉️
ያገባሁት ሰው ካልተመቸኝ ብፈታው ምን ችግር አለው⁉️
እንደምንጋባ እርግጠኛ ከሆንን ግብረስጋ ግንኙነት ብንፈጽም ምን ችግር አለው⁉️




ምን አለ ያጎደልክብኝ

ሊቀ መዘምራን ዲያቆን ቴውድሮስ ዮሴፍ

እ_ን_ዘ_ም____ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbell
ta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
እ_ን_ዘ_ም____


ምን አለ ያጎደልክብኝ

ምን አለ ያጎደልክብኝ
ሳትነፍገኝ ሁሉን ሰጠኸኝ
ሁነኸኝ እናት እና አባት
አለፈ ብዙ ዘመናት

        
አኖርከኝ ዛሬም በጤና
ወጥቸ ገባሁ በደና
መንገዴን ሰጥቸሀለው
ስትመራኝ እከተላለው
        
አዝ_

ወረት አታውቅም ጌታየ
መች ቀረ ፈሶ እንባየ
ህይወቴ በመድሀፍህ ነው
መፍራቴ ከቶ ለምን ነው
          
አዝ_

አውቀኸኝ ሳሰራኝ ገና
ሞልተኸኝ ቅኔ ምስጋና
ካንተ ነው የተቀበልኩት
በመዝሙር የሰለጠንሁት
           
አዝ_

መዛሌ በውሀ ጥም
በባእድ ሀገር መድከም
በብዙ ስጋት ተጉዤ
ቁሜአለው ስምህን ይዤ
           
አዝ_

በትዳር በልጅ ባርከኸኝ
የልቤን ደስታ ሰጠኸኝ
ስለያዝኩ ጌታ ያንተን እጅ
ተባልኩኝ የንጉሱ ልጅ
       
ሊቀ መዘምራን ዲያቆን ቴውድሮስ ዮሴፍ

እ_ን_ዘ_ም____ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbe
llta ~ @enzmrbellta
@enzmrb
ellta ~ @enzmrbellta
እ_ን_
ዘ_ም____ር


የአርምሞ እናት

ዘማሪ ዲያቆን ዘለዓለም ታከለ (ዘጎላ)

እንዘ_ም____ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbel
lta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
እንዘ_ም____ር


የአርምሞ እናት

የአንደበት የብዕሯን ኃይል በጸጋዋ ብንመዝነው
የእርሷን ስብከት የእሷን ጦማር የሚችል ስፍራ የቱ ነው
'የአምላክ እናት የአርምሞ እናት ዝምታዋ ግን ድንቅ ነው/2/


ከ22ቱ ፍጥረት ሰባቱን በአርምሞ
የፈጠረ ልጇ በቀራንዮ ደግሞ
በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል ጠቦት
በአርምሞ አዳናን በሞቱ ገድሎ ሞት

አዝ______

ግብሯም እንደ ልጇ መልኳም እንደአምላኳ
ሁሉኑም በልቧ መጠበቅ ታሪኳ
በሚልቅ ዝምታ ከአርሳኒ ከአጋቶን
ቃልን ከለከለች የቃል እናት ስትሆን

አዝ______

የነብያቱን ነው ጸሎቱን ብታደርስ
አሰምታ ብትጮህ ማርያም በመቅደስ
ከነገረኝ በቀር ገብርኤል በብስራት
ምንም አላውቅ አለች እመ ትህትና ናት

አዝ______

ባትጽፍ በርሷ እቅፍ አንድ ልጇ ወንጌል
በአርምሞ ብትጸና እርሷ ግን ናት ፊደል
ቃል የተጻፈባት ጽሌ ናት ሰሌዳ
ሕይወቷን አንብበን ልጇን እንረዳ



ዘማሪ ዲያቆን ዘለዓለም ታከለ (ዘጎላ)

እ__ንዘም__ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbe
llta ~ @enzmrbellta
@enzmrb
ellta ~ @enzmrbellta
እ__ን
ዘ__ም__ር


በቅዱስ አጠራርህ

ዘማሪ ዲያቆን ዘለዓለም ታከለ (ዘጎላ)

እንዘ_ም____ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@en
zmrbellta ~ @enzmrbellta
እንዘ_
ም____ር


በቅዱስ አጠራርህ

እንደ ስራዬ አይደል እንደራስህ ሃሳብ
እንደጸጋህ መጠን በምህረት ልሳብ
'በቅዱስ አጠራርህ ጥራኝ
ጌታ ሆይ ወደ ሕይወት ምራኝ/2/


የአለም ብርሃን ሆነህ ጎልማሳነቱን ባረክህ
ናዝራዊው ድንገት መጥተህ እንደ ንስር አደስከው
ጴጥሮስ ጀልባውን ጣለ ቀረ አሳ ማጥመዱ
አንተ ጠራኸውና ወንጌል ሆነ መንገዱ
ታናሽ የምሆን እኔ
ኃጥእ ነው ብለህ አትናቀኝ
በቅዱስ አጠራርህ ጥራኝ/4/

አዝ__

የጦር ጋሻውን ጣለ ጳውሎስ ጥሪህ ማረከው
ሊገድል ፈቃድ ያለውን ሊያድን ምክንያት አደረከው
አንተ ቅዱስ ነህና ጥሪህ ቅዱስ ያደርጋል
ጌታ እኔንም ጥራኝ ልቤ አንተን ይፈልጋል
         ታናሽ የምሆን እኔ
         ኃጥእ ነው ብለህ አትናቀኝ
         በቅዱስ አጠራርህ ጥራኝ/4/

አዝ__

ጸጋ በዝቶልኝ ለኔ በምህረት አይን አይተኸኝ
የቅዱስ ልጅ ተብዬ ቅዱሱ አንተ ጠርተኸኝ
ልኑር እሻለሁና ልቤ በአንተ እንዳመነ
ጌታ እኔንም ጥራኝ አንተ ጠርተኸው ማነው ቅዱስ ያልሆነ
         ታናሽ የምሆን እኔ
         ኃጥእ ነው ብለህ አትናቀኝ
         በቅዱስ አጠራርህ ጥራኝ/4/

ዘማሪ ዲያቆን ዘለዓለም ታከለ (ዘጎላ)

እንዘ_ም____ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzm
rbellta ~ @enzmrbellta
@enz
mrbellta ~ @enzmrbellta
ንዘ_ም____ር


ታድነኝ ዘንድ

    ዘማሪ ዲ/ን ዮሴፍ ግርማ

እ_ን_ዘም__ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@
enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
እ_ን_ዘም__ር


ታድነኝ ዘንድ

አቤቱ ታድነኝ ዘንድ ውደድ ውደድ
አቤቱ ታድነኝ ዘንድ ፍቀድ ፍቀድ
ከክፉዎች ምክር ወጥመድ
አቤቱ ታድነኝ ዘንድ ውደድ


ይሁን ስትል ሆኖ አዘዝክ ተፈጠሩ
በቃልህ ጸንተዋሉ ምድርና ጠፈሩ
ልክ እንደመጻጉ ዳን ያልከው ይድናል
'በአቅሌስያ ሳይዳ ፍጥረት ደጅ ይጠናል/2/

አዝ_____

ሐዋርያት በታንኳ አድነን እንዳሉ
በቃልህ ተግሳጽ ጸጥ እንዲል ማዕበሉ
ሞገድ ጾር ተነስቷል በባህርየ ስጋየ
አድፈኒ ክርስቶስ ሊቃባርያየ
አድነኝ አምላኬ አድነኝ ጌታዬ

አዝ____

ለሞት በተሰጠ ጎስቋላ ሰውነት የማልወደውን ነው የማደርገውን
ከሲኦል ከሰዶም ከአለመ መአቱ
'ያውጡኝ እጄን ይዘው እንደ ሎጥ መላእክቱ/2/

አዝ_____

የነፍስ እድፍ ማጠብ ልምዱ ነው የኤልሻዳይ
ቢቀላ እንደ አለላ ይነጣል ከአመዳይ
በሄጾጵም ይርጨኝ ያንጻኝ ከበረዶ
'ቸር ወመስተሳህል ድኅነቴን ወዶ/2/


    ዘማሪ ዲ/ን ዮሴፍ ግርማ

እ_ን_ዘ__ም____ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbell
ta ~ @enzmrbellta
_ን_ዘ__ም____ር


👉 ሴት በወር አበባዋ ጊዜ መጸለይ ትችላለች?
👉 ግብረ አውናን / ሴጋ /ማስተርቤሽን/ የፈጸመ ሰው በተክሊል ማግባት ይችላልን?
👉 በሱባኤ ወቅት ህልመ ሌሊት (ዝንየት) ቢመታን ምን እናደርጋለን?
👉 ሕልመ ሌሊት በራሱ ኃጢአት ነውን?
👉 ሕልመ ሌሊት በምን ይከሰታል?
👉 ከዝሙት አጋንንት እና ከዝንየት በተጨማሪ በሕልመ ሌሊት የሚፈትነን አጋንንት የትኛው ነው?
👉 የሕልመ ሌሊት መፍትሔ ምንድን ነው?

ለእነዚህ ሁሉ መልስ ለማግኘት ወደ ቦቱ ይግቡ 👇👇


ኢየሱስ ከትንሳኤው በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው ለማነው?


ካህናተ ሰማይ ስንት ናቸዉ?


እንወድሻለን ኪዳነምሕረት❤️
ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ

እን_ዘም_ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrb
ellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbe
llta ~ @enzmrbellta
እን_ዘ_ም_
_


እንወድሻለን ኪዳነምሕረት✝

ለእግዚአብሔር ታቦቱ መቅደሱ
ቀርበናል ባንቺ ወደ ንጉሡ
የክብራችን ጌጥ ሽልማት
እንወድሻለን ኪዳነምሕረት


በጨለማው ላለ ብርሀንን አየ
ለእርስቱ ተካፋይ እንዲሆን ተለየ
ወደ ቀድሞ ክብሩ ሊመለስ ዳግመኛ
አንቺ ነበርሽ ተስፋው ለአዳም መዳኛ

አዝ__

ያን ሁሉ ዘመናት የፈሰሰው ደም
ዓለምን ከእስራት ሊፈታ አልቻለም
ወደ ሚሻል ኪዳን በደም ሊያሻግረን
ደምሽን ተዋህዶ መድኃኔዓለም ዋጀን

አዝ__

አለን ብዙ ምክንያት አንቺን ምንወድበት
ዓለም ያልተረዳው ያለወቀው እውነት
ያወቀ የተረዳ የመድኃኑን ምስጢር
አያፍርም ክብርሽን ቆሞ ለመናገር

አዝ__

አውቃለው እግዚአብሔር የሰጠሽን ክብር
ላመስግንሽ እኔም ሳልቀንስ ሳልጨምር
ሚባርክሽ ቡሩክ ነው እና እናቴ
ኪዳነምሕረት ንገሽ እመቤቴ

በዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ

✍️ እን_ዘም_ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzm
rbellta ~ @enzmrbellta
@enz
mrbellta ~ @enzmrbellta
ን_ዘ_ም__ር


​​
ቅዱሳን በሙሉ

ቅዱሳን በሙሉ ከአምላክ አማልዱን/2/ 
ልንጠፋ ነውና በዝቶ በደላችን/2/

ፃድቃን ሰማዕታት ንጹሐን ሁላችሁ/2/
ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ዓለምን ንቃችሁ/4/

ለሰማያዊው ክብር ለአክሊል የበቃችሁ/2/
ወደ አምላክ አቅርቡን በጽኑ ምልጃችሁ/4/

ድንግል እናታችን ኪዳነ ምሕረት/2/
ቅድስተ ቅዱሳን የጻድቃን እናት/4/

ርኅርኂተ ልቦና አሳስቢ ከልጅሽ/2/ 
ይቅርታ እንድናገኝ በፍጹም ልመናሽ/4/

           
መዝሙር
በማኅበረ ቅዱሳን ዘማርያን
           

┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈
እን_ዘም_ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrb
ellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbe
llta ~ @enzmrbellta
እን_ዘ_ም_
_
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


የቸብቸቦ መዝሙር
በወንጌል

በወንጌል/፪/
እናምናለን እኛስ በወንጌል/፪/

በሰላም ምልክት በወንጌል
በክብር መገኛ በወንጌል
በቅዱስ ወንጌሉ በወንጌል
እናምናለን እኛ በወንጌል

አዝ___

ሰይጣን ድል ተመታ በወንጌል
ሰላም ተበሰረ በወንጌል
ጽድቅ የተራቆተ በወንጌል
ፀጋን ተቀበለ በወንጌል

አዝ___

ያዘነ ይጽናናል በወንጌል
ብርቱ ተደግፎ በወንጌል
እንባውን ያብሳል በወንጌል
ደስታን ተትረፍርፎ በወንጌል

አዝ___

አለም ብርሃን አየ በወንጌል
ጨለማው ተረታ በወንጌል
ወንጌል ሲተረጎም በወንጌል
ምስጢሩ ሲፈታ በወንጌል

አዝ___

ሰላምን አገኘን በወንጌል
ልባችን በደስታ በወንጌል
መናፍቅ አፈረ በወንጌል
በወንጌል ተመታ በወንጌል

አዝ___

የክህደትን መጽሐፍ በወንጌል
ቢያበዙ ቢያሰፉ በወንጌል
ወንጌል ግን አንድ ነው በወንጌል
የተማርነው ከሱ በወንጌል

አዝ___

አበው ሊቃውንቱ በወንጌል
እንዳስተማሩን በወንጌል
እመኑ ብለዋል በወንጌል
በቅዱስ ወንጌል በወንጌል

አዝ___

በሕዝቅኤል ትንቢት በወንጌል
እንደተነገረው በወንጌል
ይህን መጽሐፍ ብላ በወንጌል
ተብሎ እንደተፃፈው በወንጌል

በወንጌል /2/ ነአምን በአሐዱበወንጌል

እን_ዘም_ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
ን_ዘ_ም__ር


ሐመረኖህ ነሽ

ዘማሪት ፋሲካ ፍሰሐ
           

┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈
እን_ዘም_ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
እን_ዘ_ም__ር
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


ሐመረ ኖህ ነሽ

ሐመረ ኖህ ነሽ
የምህረት ቃል ኪዳን የተገባልሽ
ትውልድ ይህን አምኖ
ያከብርሻል አልቆ እና አግኖ


በእግዚአብሔር ሀሳብ ነበርሽ በህሊናው
ዓለምን ሳይፈጥር አዳምን ሳይሠራው
ሁሉም የናፈቀሽ የወጣብሽ ፀሐይ
ንግሥት ነሽ ድንግል እሙ ለአዶናይ

አዝ_____

ያንን የጭንቅ ቀን የጥፋቱን ዘመን
አልፈነዋል ባንቺ በአማናዊት ፅዮን
ምንጭ ነሽ የእርካታ የድህነት መፍለቂያ
የዘለዓለም እረፍት አምባ እና ማረፊያ

አዝ_____

የነቢያት ትንቢት ተፈጽሞ አየን
አንቺ ምክንያት ሆነሽ ለመዳናችን
ድምፅሽን ሲሰማ ጠላት ይሸበራል
እኛ ግን ሰምተነው በሀሴት ዘለናል

አዝ_____

አንዴ በገባልሽ ቃል ኪዳን መሠረት
ትውልዱን ይምራል ይኸው በቸርነት
ስምሽ ወለላ ነው ጣፋጭ ለአፋችን
ማርያም ማውም ታብሷል እንባችን

              
ዘማሪት ፋሲካ ፍስሐ

           

┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈
እን_ዘም_ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzm
rbellta ~ @enzmrbellta
@enz
mrbellta ~ @enzmrbellta
ን_ዘ_ም__ር
┈┈┈┈••◉❖◉●••┈┈┈


#ሁሉን_ተውኩት

መዝሙር
በዘማሪ ወንደሰን አለሙ

20 last posts shown.