ሦስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ትንቢት ተነግሮለት የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠለት የሶዶ ደብረ መንክራት አቡነ ተክለሃይማኖት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ከ37 ዓመት በኋላ ግንቦት 24 ቀን 2017 ዓ.ም እቅዳሴ ቤቱ እንደሚከበር ተገለጸ።።
ዘጋቢ መ/ር ኪደ ዜናዊ
(#EOTCTV ታኅሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም)
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በወላይታ ሀገረ ስብከት በሶዶ ከተማ እየተገነባ ያለው አዲስ የደብረ መንክራት አቡነ ተክለሃይማኖት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ግንቦት 24 ቀን 2017 ዓ.ም ቅዳሴ ቤቱ እንደሚከበር የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ገልጸዋል።
ገዳሙ በብፁዕ አቡነ ተክለሃይማኖት በ12ኛ ክ/ዘመን መጨረሻ በ13ኛዉ ክ/መ መጀመሪያ የተመሠረተ ኾኖ በርካታ ዓመታት ያስቆጠረ በዝባፈተን/ዳሞት/ ተራራ ሥር በዕድሜ ጠገብ አጸዶች የተከበበ ከአዲስ አበባ በ320 ኪ.ሜ ርቀት የሚገኝ ታላቅና ታሪካዊ ገዳም መኾኑን ተነግሯል።
ገዳሙ ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ጣዖትን አፍርሰዉ ቤተ መቅደስን የሠሩበት ንጉሥ ሞቶሎምን ከእነ ሠራዊቱ አስተምረው አሳምነው ያጠመቁበት፤ ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ከእግዚአብሔር እጅ ጵጵስና የተሾሙበት እና 12 ዓመት ያገለገሉበት ጥንታዊ ገዳም እንደኾነ ተገልጿል።
ቅዱስ ቦታው የቤተክርስቲያን ባለ ውለታ የሆኑት ሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ለበርካታ ዓመታት ያስተማሩበት እና ሦስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት/ በቀድሞው ስማቸው አባ መላኩ ለፕትርክርና ከመጠራታቸዉ አስቀድሞ ለ42 ዓመታት ያክል እየጾሙና እየጸለዩ ወንጌል ያስተማሩበት ታሪካዊ ቦታ መኾኑን ተነግሯል።
ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ እንደገለጹት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ፓትርያርክ ከሆኑ በኋላ 12 ብፁዓን አበውን አስከትለው ወደ ወላይታ ሐዋሪያዊ ጉዞ ያደረጉ ሲሆን በዕለቱ ማለትም ግንቦት 13 ቀን 1980 ዓ.ም ለአዲሱ ሕንፃ ቤተክርስቲያን ግንባታ የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠው ህንጻውን ግን በእናታቸው ማህጸን ያሉ ህጻናትን ጨምሮ ኢትዮጵያውያን ልጆቼ ወደፊት ይሰሩታል ብለው በወቅቱ ቅዱስነታቸው ትንቢት ተናግረው እንደነበር ገልጸዋል።
በመኾኑም የቅዱስነታቸው ትንቢት ተፈጽሞ የዕረፍታቸው ቀን በሚታሰብበት መጪው ግንቦት 24 ቀን 2017 ዓ.ም በደማቅ ሥነ ሥርዓት ቅዳሴ ቤቱን ለማክበር መርሐ ግብር መያዙን ተናግረዋል።
ይሁን እንጂ ሕንጻውን ተጠናቅቆ በተያዘለት ቀን ለማስመረቅ ለሚቀሩትን ሥራዎች እና የሚያስፈልጉትን ቁሳቁሶች በባለሙያዎች ተጠንቶ ወደ 42 ሚልዮን ብር እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።
በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የጥንታዊውና ታሪካዊው ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን በተያዘለት ቀን እንዲመረቅ በሃገር ውስጥና ከሃገር ውጭ የምትገኙ የተዋሕዶ ልጆች እጃችሁን እንድትዘረጉ በጻድቁ ስም እማጸናለሁ ሲሉ አባታዊ ጥሪ አቅርበዋል።
#የቤተ ክርስቲያን የሆነውን ብቻ!
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++
https://youtu.be/Wqgq1KebrOo 🇪🇹 "የቤተክርስቲያን የሆነውን ብቻ" 🇪🇹
ተቋሙን በገንዘብ ለማገዝ፡-
የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት EOTC(BSA)
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000165122406
ዓባይ ባንክ 1462319237132015 🎥
📱 የዲጂታል ሚዲያ ገጾች💻
ለመረጃ 📞 +251985585858
➽ የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv➽ የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel➽የቴሌግራም ገጻችን
https://t.me/eotctvchannel➽ የቲክ ቶክ ገጻችን
https://vm.tiktok.com/ZMFSxXdUf/➽ የዩቲዮብ ገጻችን Eotc tv 2
https://youtu.be/Wqgq1KebrOo➽የትዊተር ገጻችን
https://twitter.com/EotcT/➽የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/p/CknRF0MtB77/?igshid=MDJmNzVkMjY=