ዉድ ወላጆች፡
የት/ት ቤት ክፍያ ጭማሬን አስመልክቶ በ ት/ት ቤቱ የሀሳብ መስጫ ሳጥን አማካኝነት ተጨማሪ አስተያየቶችን ለማግኘት ባደረግነዉ ጥረት፤ 20 ወላጆች ብቻ የተሳተፉ ሲሆን፡ 2 ወላጅ 40%፣ 8 ወላጅ 35%፤ 2 ወላጅ 30%፣ 8 ወላጅ 25% እንዲሆን ሃሳብ ሰተዋል፡፡ ይህ ቁጥር በርግጥ በቂ ዉክልናን አያሳይም፡፡ በእንደዚህ አይንት አንገብጋቢ ጉዳይ ላይ የወላጆች ተሳትፎ አነስተኛ መሆን ዉጤታማ ዉይይትና ድርድር ብሎም ስምምነት እንዳይኖር ተፅእኖ አሳድሯል፡፡
በቀጣይም በክፍለ ከተማ ደረጃ ከ ሬጉላቶሪ አካል ጋር በተደረገዉም ዉይይትና ድርድር ት/ት ቤቱም 60 ላይ ወተመም 40 ላይ በመፅናታችን ስምምነት ላይ ሳይደረስ ቀርቷል፡፡ በመሆኑም ቀጣዩና የመጨረሻ ዉይይት በማእከል ደረጃ እንደሚሆን ስለተገለፀልን፡ ይህንኑ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
ወ.ተ.መ.ህ እና የእ.ፒ.ኤስ. አስተዳደር