ተመድ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለስድስት የአፍሪካ ሀገራትና ለየመን 100 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ!!
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በማዕከላዊ የአደጋ ጊዜ አቅርቦቱ በኩል በኢትዮጵያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ናይጄሪያ፣ ኬኒያና የመን ለችግር የተጋለጡ ሰዎችን ለመርዳት የሚያስችል ድጋፍ ይፋ አድርጓል። የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበርያ (ኦቻ) ቃል ዐቀባይ ጄንስ ላርኬ እንደገለጹት በሀገራቱ የተደቀነውን ዘርፈ ብዙ ችግርና የረሃብ አደጋ ለመቋቋም ድጋፍ ማድረጉ አስፈላጊ ኾኗል።
በዚህም ተመድ ለእያንዳንዱ ሀገራት የሚኾን 43 ሚሊዮን ዶላር ከለጋሾች መጠየቁን አስታውሰው ተመድ በበኩሉ ለአስቸኳይ የአደጋ ጊዜ መቋቋሚያ የሚኾን 100 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አድርጓል ብለዋል።
ድጋፉ የተደረገው ኮሮናቫይረስ፣ ድርቅ፣ በግጭቶችና በኢኮኖሚ ቀውስ ምክንያት በሀገራቱ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሰዎች ለከፍተኛ ችግር በመጋለጣቸው ነው። በሩስያና በዩክሬን መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት ችግሩን በማባባሱም አሁኑኑ መፍትሔ መፈለግ ስለሚያሻው ድጋፉ መደረጉን ኢዜአ ዘግቧል።
https://t.me/esat_television_official