ከማኅበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ማሳሰቢያ ተሰጠ
ግንቦት 6/2014 (ዋልታ) በየጊዜው እየተባባሰ ከመጣው የማኅበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ሰለባ ላለመሆን ዜጎች ማንነታቸው ከማይታወቁ ግለሰቦች ጋር በበይነመረብ በሚደረጉት ግንኙነት ላይ ጥንቃቄ እንዲወስዱ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት እና የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት ጥምር ግብረ ኃይል አሳሰበ።
ግብረ ኃይሉ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ማኅበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም የሚፈጸሙ የማጭበርበር ወንጀሎች በይዘትም ሆነ በአፈጻጸም ስልታቸው ውስብስብ እየሆኑ ከመምጣታቸው ባሻገር በርካታ ግለሰቦች የጉዳቱ ሰለባ እንዲሆኑ እያደረገ ነው።
የማጭበርበር ወንጀሎቹ በዋናነት የሚፈጸሙት በውጭ አገር የሚኖሩ፣ በቱሪስት ቪዛ ወደ አገር ውስጥ በሚገቡ የተለያዩ ሀገራት ዜግነት ባላቸው ግለሰቦች መሆኑንም በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡
ኢትዮጵያውያን በስፋት የሚጠቀሟቸው ማህበራዊ ሚዲያዎች ማለትም ፌስቡክ፣ ኢ-ሜይል፣ ዋትስአፕ፣ ቴሌግራም፣ ኢንስታግራም፣ ኢሞና ቫይበርን በመጥለፍና ወዳጅ መስሎ በመቅረብ ወንጀሎቹ እንደሚፈጸሙ ከተደረገው ክትትል ማወቅ እንደተቻለም ተገልጿል።
https://t.me/esat_television_official