Ethio Menzuma


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


Welcome to Ethio Menzuma! We preserve the traditional spiritual music and prayers of Ethiopia. Join us to experience the beauty and power of this spiritual music. Stay connected for daily updates, unique content, and a chance to celebrate and honor our cu

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter


የአዲስ አበባዉ የዐሊ መስጊድ ጉዳይ በሽምግልና ተይዞ ስለነበር ሂደቱ በዚያዉ አቅጣጫ ይፈታል የሚል እምነት ነበረኝ። መጅሊሱ የሽምግልናውን ውጤት ተከትሎ የአንድን መስጊድ ችግር መፍታት አለመቻሉ ያለንበትን አሳዛኝ ሁኔታ ያሳያል፡፡ ሲፈጸሙ የከረሙ ነዉሮችና ትላንት በማህበራዊ ሜዲያ ሲሰራጩ ያደሩ ምስሎች እጅግ የሚያሙ ከመሆናቸዉ የተነሳ ሀላፊነት እንደሚሰማዉ አንድ ዜጋና ሙስሊም የበኩሌን ማለት እንዳለብኝ ተሰማኝ፡፡ በዚህ የተከበረ ወር በድ*ብደ*ባ ዓይኑ የጠፋ፣ አናቱ የተ*ፈ*ነከተ፣ በስ*ለ*ት ተ*ወ*ግ*ቶ የሚያቃስት ወዘተ ወንድሞችን ማየት፣ የእናቶችን ለቅሶ መስማት እጅግ ሲበዛ ያሳዝናል፤ ይሰቀጥጣል፡፡

ዐሊ መስጊድ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአራቱም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች የገጠመዉን ፈታኝ ሁኔታ ለማየት የሚያስችል አንድ ናሙና ነዉ፡፡ ሙስሊሙ ህብረተሰብ በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ተመሳሳይ ወይም የባሱ ፈተናዎችን ማስተናገዱን እየወጡ ያሉ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

በነዚህ ጥቂት ዓመታት ውስጥ ምንድን ነዉ የተፈጠረዉ? አሁን ካለንበት ሁኔታ ዉስጥ እንዴት ልንገባ ቻልን? ወደፊትስ ምን ዓይነት ሁኔታ ይጠብቀናል? እንዴትስ መዉጣት ይቻለናል? የሚሉ ጥያቄዎች እያንዳንዱን ሙስሊም ዜጋ ሊያሳስቡ የሚገቡ ናቸዉ፡፡ ስለሆነም አጠቃላይ የመፍትሄ አቅጣጫ የሚያመላክት የምክክር መድረክ ይዘጋጅ ዘንድ የሀገር ሠላምና የዜጎች ደህንነት ለሚያሳስባቸዉ የሁሉም ወገን የእስልምና ሊቃዉንት (ዑለሞች)፣ መምህራን (ዳዒዎች)፣ ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና ተቋማት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ እንዲሁም ጉዳዩ ለሚመለከታቸዉ የመንግስት አካላት የሚጠበቅባቸዉን ሚና እንዲጫወቱ ጥሪየን አቀርባለሁ፡፡

በሀገሪቱ ትርጉም ያለዉ አሀዝ ያላቸዉ ዜጎች ሰቆቃና ዋይታ ከጫፍ ጫፍ በሚሰማበት በዚህ ወቅት በየትኛዉም ግላዊም ሆነ ቡድናዊ ስሌት ተሸብቦ ዝምታን መምረጥ ከአላህ ፊት ተጠያቂ፣ በታሪክም ተወቃሽ የሚያደርግ ነዉር መሆኑን ማስታወስ እወዳለሁ።

https://t.me/hassentaju




Video is unavailable for watching
Show in Telegram


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


የሀሰን ታጁ መልእክት ነው የኡማ






🤣🤣🤣😂😂ቤት ውስጥ ትንሽ ት/ት ቤት

#Ethiopia | ሳውዲ አረብያዊው የ50 ዓመት ሰው ከአንድ ት/ት ቤት ከየአይነቱ ማለትም ተማሪ ፣መምህር ፣ የት/ት ቤቱን መሪዎች ማግባታቸውን አል አረብያ ዘግቧል::🤣🤣🤣😂😂😂🤣




ሰበር ዜና! ቅዳሜ 1
የስነ ፈለክ ተመራማሪ እና ባለራዕይ ሊቅ አብዱላህ አልኩዳይሪ እንዲህ ይላሉ፡- በሥነ ፈለክ ጥናት የተባረከው የረመዳን ወር የመጀመሪያው ቀን ቅዳሜ መጋቢት 1 ቀን 2025 ብለው ገምተዋል ። 🌙🤲😍




መልኳም ኳሚስ ይሁንላችሁ


Forward from: HASSEN TAJU
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
እንኳን ለወርሀ ረመዷን በሠላም አደረሰን።




የደራሲ ኸድር ታጁ መፅሃፎች በመመረቅ ላይ ናቸው
......................................
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ዑመር እንድሪስን ጨምሮ ታላላቅ የሃገራችን ዑለማዎች ማዲሆች እና ሙሁራን በተገኙበት በቢላሉል ሃበሺ ማእከል በኢንጅነር ኸድር ራህመቶ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በመመረቅ ላይ ናቸው ።
በምረቃውም ከዳናዎች ቅፅ ሁለት በተጨማሪ የደራሲው ቀደምት ስራዎች በመመረቅ ላይ ናቸው።


ዉሸታሞች ሲበዙ የሚዋሹበት ነገር ራሱ ይደበላለቃል

የአቅል ፍርድ - ነገረ ተንታ
✍️
በትናንትናው ዕለት በደቡብ ወሎ ዞን ተንታ ወረዳ የመውሊድ ምግብ ተመርዞ አራት ሰዎች መሞታቸውን እና ቁጥሩ ከፍ ያለ የመውሊዱ ተሳታፊ ደግሞ መመረዛቸውን በሶሻል ሚዲያ ላይ መንሸራሸሩ እንዲሁም የወንጀል ተጠርጣሪዎቹ በአካባቢው የመውሊድ ስነስርዓቱን ሲቃወሙ የነበሩ ግለሰቦች ናቸው መባሉን ተከትሎ የተለያዩ ግለሰቦች ተቃውሞ ሲያሰሙ ውለዋል ።

✍️
የመጀመሪያው በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡት ግለሰብ "Mohammed Seid" የተባሉ ከተንታ ወረዳ አስተዳደር ሲሆኑ በአካባቢው ማህበረሰብ መዋጮ የተዘጋጀ የመውሊድ ፕሮግራም መሆኑን ገልፀው የችግሩ ምክንያት ደግሞ የታረደው በሬ ህመምተኛ መሆኑ አስረድተዋል ።

❶ ምክንያቱ የታመመ በሬ ነው ተብሎ ከተረጋገጠ ግለሰቦችን ማሰሩ ለምን አስፈለገ ?

❷ ከአካባቢው በስልክ ደውለን ባገኘነው መረጃ መሰረት የተቀቀለውን የበሬ ስጋ ብቻ የተመገቡ ተሳታፊዎች ምንም አይነት የመመርዝ ጉዳት ያላጋጠማቸው ሲሆን በአንፃሩ ተጠርጣሪ ግለሰቧ ባመጣችው ዘይት የተሰራውን ወጥ የተመገቡ ግለሰቦች መመረዛቸውን ነግረውናል ። ስለዚህ ጉዳዩ ከበሬው ስጋ ሳይሆን ከዘይቱ ነው ወደሚል ድምዳሜ ያደርሰናል ።

✍️
ሁለተኛው በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጠው አቶ ሙሐመድ አባተ ሲሆን የመውሊድ ፕሮግራም እንዳልሆነ እና የመመረዙ ምክንያት ከተለያዬ ቦታ የተሰበሰበ ምግብ መሆኑን የወረዳው ጤና ጽ/ቤት አረጋግጧል ሲል ፅፏል።

❶ መሐመድ አባተ ከወረዳው ጤና ጽ/ቤት አገኘሁ ያለው መረጃ ከወረዳው አስተዳደር መረጃ ጋር እንዴት ሊጣርስ ቻለ ?

❷ በመሐመድ አባተ መረጃ መሰረት የምግብ መመረዙ ምክንያት ከተለያዬ ቦታ የተሰበሰበ ምግብ ሲሆን የወረዳው አስተዳደር ደግሞ የታረደው በሬ የታመመ በመሆኑ ነው ብሏል ። እንዴት ?

❸ ሙሐመድ አባተ ሶስት ሰዎች መሞታቸውን ገልፆ የሞቱት ግን የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው በአራተኛው ቀን ነው ያለ ሲሆን በአንፃሩ የወረዳው መስተዳድር ሁለቱ ግለሰቦች የሞቱት የህክምና ቡድኑ በአካባቢው ሳይደርስ ነው በማለት ገልጿል። ለመሆኑ ሙሐመድ አባተ አምባሳደር ሐሰን ታጁን ለመወንጀል በዚህ ልክ መዋሸት ለምን አስፈለገው ?

❹ መሐመድ አባተ ጉዳዩን ሁለት ሳምንት ያለፈው ነው በማለት ለማጣጣል ሞክሯል ። በዕርግጥ ከአሁን በፊት ሻሸመኔ ላይ በዕድሜ የገፉ የመጅሊስ አመራሮች በአፍላ ወጣቶች በቡጢ እና በካልቾ ሲነረቱ የሚያሳይ ቪዲዮ ሶሻል ሚዲያ ላይ በተለቀቀ ወቅት ካሚል ሸምሱ "ጉዳዩ ወር ያለፈው ነው ፤ የመቷቸው አህባሽ መስለዋቸው ነው " ማለቱን አንዘነጋውም ። እንግዲህ የህግ ምሩቅ የሆነው ካሚል ሸምሱ ይህንን ካለ ጓደኛው ሙሐመድ አባተ ከዚህ የከፋ ቢናገር ገርሞ አይገርምም ።

✍️
ሶስተኛው በጉዳዩ አስተያየት የሰጠው ፕሮፌሰር ቃልኪዳን [Kha Abate] ሲሆን የችግሩ ምክንያት "በአረም መርዝ ዕቃ ዘይት ቀንሰው ወጥ ተሰራ" በማለት ፅፏል።

✍️
እንደ አጠቃላይ ከላይ የተጠቀሱት ግለሰቦች የምግብ ምረዛው ምክንያት በማለት የተለያዩ ሶስት ምክንያቶችን አስፍረዋል ። ይህም በጉዳዩ ላይ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን ከህግ ተጠያቂነት ለማስመለጥ የታሰበ ነገር ሊኖር ይችላል የሚል እሳቤን ያጭራል ። በመሆኑም የተጎጂ ቤተሰቦች እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ በጉዳዩ ላይ ያለ ምንም ጫና ለሚዲያዎች ማብራሪያ ቢሰጡ እንዲሁም የወሃብያው ወገን በህግ አፈፃፀም ላይ ጣልቃ እንዳይገባ ተደርጎ ተገቢውን የህግ ማስከበር ሒደት እንዲከናወን ስንል በትህትና እንጠይቃለን ‼️


#ለክቡር_አምባሳደር_ሀሰን_ታጁ
ረጅም ሀያት
#ቻሌንጅ@ethio_Menzuma




My Hero

20 last posts shown.