Academic Excellences


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Education


Join our educational Telegram channel for daily insights, tips, and resources to enhance your learning journey.
for advertisement
contact:➥ @ac_exc

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Education
Statistics
Posts filter


#ASTU

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪዎች ካርኒቫል አክብሯል።

የናዝሬት ቴክኒክ ኮሌጅ በሚል ስያሜ በ1986 ዓ.ም የተመሠረተው አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፤ አሁን ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ሁለት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ነው፡፡

ወደ ራስገዝ ዩኒቨርሲቲ ለመሸጋገር ዝግጅት ላይ የሚገኘው ዩኒቨርሲቲው፤ የመጀመሪያውን የቀድሞ ተማሪዎች ካርኒቫል በማክበር ላይ ይገኛል፡፡

ካርኒቫሉ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፤ በአዲስ መልክ የተገነባ የሪጅስትራርና የአለምናይ ቢሮ ምርቃት እና የቀድሞ ተመራቂዎች የግንኙነት መረብ ሥራ መጀመር ኹነቶች በዛሬው ዕለት ተከናውነዋል።

የፓናል ውይይት፣ የቴክሎጂ ፈጠራ አውደ ርዕይ እና ሌሎች የቀድሞ ተማሪዎችን የሚያስተሳስር ዝግጅቶች እንደሚደረጉ ይጠበቃል።
#AcademicExcellence #HigherEducation #StudentLife
#StudyMotivation #StudyTips
  #CollegeLife #UniversityLife
#EducationMatters
#LearnSomethingNew #OnlineLearning
#StudentResources #SuccessfulStudent
#AcademicSuccess
#EducationIsKey #LifelongLearning


#Reminder

የፋይዳ መታወቂያ አውጥተዋል?

በሰኔ 2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለመውሰድ ተፈታኞች የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ሊያወጡ እንደሚገባ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል።

የመንግሥት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

የመውጫ ፈተናውን ለመውሰድ ምዝገባውን በጊዜ በማድረግ የፋይዳ መታወቂያዎን ይያዙ።
#AcademicExcellence #HigherEducation #StudentLife
#StudyMotivation #StudyTips
  #CollegeLife #UniversityLife
#EducationMatters
#LearnSomethingNew #OnlineLearning
#StudentResources #SuccessfulStudent
#AcademicSuccess
#EducationIsKey #LifelongLearning


#MoE

በሰኔ 2017 የሚሰጠውን የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ዳግም ለመፈተን እየተጠባበቃችሁ ያላችሁ አመልካቾች ምዝገባ ከዛሬ ሚያዝያ 14 /2017 ዓ.ም እስከ ግንቦት 05/2017 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

የመመዝገቢያ ቅፅ https://exam.ethernet.edu.et ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በሟሟላት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ፈተናው የሚሰጥበት ቀን ወደፊት ይገለፃል ተብሏል፡፡

ፈተናውን ለመውሰድ የብሔራዊ (ፋይዳ) መታወቂያ መያዝ ግዴታ ሲሆን፤ የአገልግሎት ክፍያ (500 ብር) በቴሌብር በኩል ብቻ የሚፈፀም መሆኑ ተገልጿል፡፡


" የ12ኛ ክፍል ፈተና ከአንድ ወር / ከአንድ ወር ተኩል በኃላ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው " - ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከአንድ ወር / ከአንድ ወር ተኩል በኃላ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።

ሚኒስትሩ ፥ " ይሄ አራተኛው ነው በአዲሱ የፈተና አሰጣጥ ፈተና የሚሰጥበት " ብለዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ባለፉት ዓመታት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከትምህርት ቤቶች ወጥቶ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አስገብቶ ፈተና እንዲሰጥ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ስለዘንድሮው የ2017 ዓ/ም ፈተና በተናገሩበት ወቅት 150 ሺህ ተማሪዎች ፈተናቸውን በኦንላይ እንዲወስዱ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ብርሃኑ (ፕሮፌሰር) ፥ " እንደ ከዚህ ቀደሙ አድካሚ በሆነ ከቦታ ቦታ ልጆችን እያዘዋወሩ ከመሄድ ባለፈው ዓመት 29 ሺህ ተማሪ ነበር ኦንላይን ፈተና የሰጠነው ዘንድሮ ደግሞ 150 ሺህ ተማሪ ኦንላይን ፈተና ለመስጠት እየተዘጋጀን ነው " ብለዋል።

ሚኒስትሩ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበትን ቀን ቆርጠው ባይናገሩም ፈተናው ከአንድ ወር / ከአንድ ወር ተኩል በኃላ እንዲሰጥ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ

#AcademicExcellence
#HigherEducation
#StudentLife
#StudyMotivation
#StudyTips
  #CollegeLife
#UniversityLife
#EducationMatters
#LearnSomethingNew
#OnlineLearning
#StudentResources
#SuccessfulStudent
#AcademicSuccess
#EducationIsKey
  #LifelongLearning


Two identical coaxial circular coils carry the same current / but in opposite directions. The magnitude of the magnetic field B at a point on the axis midway between the
coils is
(a) Zero
(b) The same as that produced by one coil
(c) Twice that produced by one coil
(d) Half that produced by one coil.

Answer: A


Which of these statements is not characteristic of a static magnetic field?
Poll
  •   (a) It is solenoidal.
  •   (b) It is conservative.
  •   (c) It has no sinks or sources.
  •   (d) Magnetic flux lines are always closed
  •   (e) The total numberof flx lines entering is equal to the total number flx lines leaving the region.
9 votes


One of the following is not a source of magnetostatic fields: (a) A dc current in a wire (b) A permanent magnet (c) An accelerated charge (d) An electric field linearly changing with time (e) A charged disk rotating at uniform speed
Poll
  •   A
  •   B
  •   C
  •   D
  •   E
9 votes


#HawassaUniversity

በ2017 ዓ.ም ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች የምዝገባ ጊዜ ሚያዝያ 14 እና 15/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
➫ ዲግሪ እና ስቱደንት ኮፒ ዋናውና ኮፒው
➫ ሁለት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ
➫ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ (በጤና ሚኒስቴር ስፖንሰር ከተደረጉት ውጪ)
➫ የ 'NGAT' ውጤት
➫ የሥራ መልቀቂያ (Clearance) ይሰሩበት ከነበረ ተቋም

ምዝገባውን ለማድረግ ኦፊሺያል ትራንስክሪፕት በኢሜል (registrar@hu.edu.et) ወይም በፖ.ሳ.ቁ. 05 አስቀድሞ ማስላክ ያስፈልጋል።

ምዝገባው በዩኒቨርሲቲው የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሬጅስትራር ቢሮ የሚከናወን ሲሆን፤ ከዋናው ግቢ ሬጅስትራር እና ከድኅረ-ምረቃ ትምህርት ቤት የ “Admission” እና የ “Acceptance” ደብዳቤ መያዝ ይጠበቅባችኋል።


#JigjigaUniversity

በ2017 ዓ.ም ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች የምዝገባ ጊዜ ሚያዝያ 13 እና 14/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
➫ ዲግሪ እና ስቱደንት ኮፒ ዋናውና ኮፒው
➫ ኦፊሺያል ትራንስክሪፕት ለዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር በፖ.ሳ.ቁ. 1020 ማስላክ
➫ የ 'NGAT' ውጤት
➫ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ
➫ የሥራ መልቀቂያ ይሰሩበት ከነበረ ተቋም
➫ ሁለት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ


#HaramayaUniversity

በ2017 ዓ.ም ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና ትምህርት ቤት አዲስ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች የምዝገባ ጊዜ ከሚያዝያ 16-18/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

➫ ከ8-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች
➫ አራት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ
➫ ዲግሪ እና ስቱደንት ኮፒ ዋናውና ኮፒው
➫ የሥራ መልቀቂያ ይሰሩበት ከነበረ ተቋም
➫ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ (በጤና ሚኒስቴር ስፖንሰር ከተደረጉ ውጪ)
➫ የ 'NGAT' ውጤት
➫ ኦፊሺያል ትራንስክሪፕት ለሬጅስትራር ጽ/ቤት በፖ.ሳ.ቁ. 235 ማስላክ

ገለጻ (Orientation) ሚያዝያ 19/2017 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን፤ ሚያዚያ 23/2017 ዓ.ም ትምህርት ይጀመራል ተብሏል።


#MoE

" ከ2019 ጀምሮ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች 4ኛ አመት ከመግባታቸው በፊት የ1 ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል " - ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)

በዩኒቨርሲቲ የሚማሩ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች 4ኛ ዓመት ሳይገቡ በፊት የአንድ ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የተጀመረው እንቅስቃሴ ከ2019 ዓ/ም ጀምሮ ተግባር ላይ እንደሚውል የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ጠቁመዋል።

ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ፤ " በሚቀጥለው ዓመት ላይደርስልን ይችላል ግን ህጋዊ ስርዓቱን በሙሉ ጨርሰን በ2019 ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚማሩ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች ከ2019 ጀምሮ 4ኛ አመት ከመግባታቸው በፊት የ1 ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ይድረጋል " ብለዋል።

" ከዚህ በፊት የነበረ ነው አዲስ አይደለም በጃንሆይ ጊዜ (በአጼ ኃይለስላሴ ጊዜ ማለታቸው ነው) የነበረ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ሁለት ጥቅም አለው ብለን ነው ይሄን የምናደርገው አንደኛ ልጆቹ ዝም ብሎ የቀለም ትምህርት ብቻ ተምረው ሳይሆን ተግባራዊ የሆነ ትምህርትም ለአንድ ዓመት ሄደው የሚሰሩበት ከማህበረሰቡ ጋር የሚተዋወቁበት ነው። ሁለተኛ የአስተማሪዎች እጥረትም ስላለ ልጆችን ወደ አስተማሪነት ለአንድ አመት ቢሆንም ለማስገባት ነው " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ


#SPHMMC

በ2017 ዓ.ም በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች የምዝገባ ጊዜ ሚያዝያ 14 እና 15/2017 ዓ.ም መሆኑን ኮሌጁ አሳውቋል።

ገለጻ (Orientation) ሚያዝያ 16 እና 17/2017 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን፤ ሚያዚያ 20/2017 ዓ.ም ትምህርት ይጀመራል ተብሏል።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

➫ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ
➫ የመጀመሪያ ዲግሪ እና ስቱደንት ኮፒ
➫ የሥራ መልቀቂያ
➫ ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ
➫ ኦፊሺያል ትራንስክሪፕት ለኮሌጁ ማስላክ
➫ የ 'NGAT' ያለፉበት ሰርተፍኬት

የምዝገባ ቦታ፦ በኮሌጁ የሬጅስትራር ጽ/ቤት፣ የሰው ሀብት ልማት አስተዳደር

በተጨማሪም የቅጥር ውል ለመግባት መሟላት ያለባቸው፦

➫ የጤና ሚኒስቴር ውል የገቡበት ሰነድ
➫ የመጀመሪያ ዲግሪ እና ስቱደንት ኮፒ
➫ የሥራ መልቀቂያ
➫ ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ

ለበለጠ መረጃ፦ 0118965125


#AAU #GAT

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠውን የድኅረ-ምረቃ የመግቢያ ፈተና (GAT) ለመውሰድ የአመልካቾች ምዝገባ ዛሬ ሚያዝያ 3/2017 ዓ.ም ይጠናቀቃቀል።

ለ'GAT' ይመዝገቡ፦
https://Portal.aau.edu.et ይግቡ።
➫ Exam Application የሚለውን ይጫኑ።
➫ Test Taker Registration የሚለውን ቅፅ ይሙሉ።
➫ የፓስፖርት መጠን ፎቶ ያለው ፎቶ ያስገቡ።
➫ Submit የሚለውን ይጫኑ።
➫ ሲስተሙ የሚሰጠዎን መለያ ቁጥር ይያዙ።
➫ ቴሌብር በመጠቀም የምዝገባ ክፍያ 750 ብር ይክፈሉ።
➫ አድሚሽን ቲኬትዎን በማውረድ ፕሪንት ብለው ይያዙ።

🔔 የ'GAT' ፈተና ፊታችን ማክሰኞ ሚያዝያ 7/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

የባለፈው ዓመት የ 'GAT' ውጤት ለዘንድሮ ስለማይሰራ፣ ፈተናውን ባለፈው ዓመት ወስዳችሁ ያለፋችሁ ዘንድሮ የድኅረ-ምረቃ ትምህርት ለመከታተል ፈተናውን በድጋሜ መውሰድ ይኖርባችኋል፡፡

የ 'GAT' ፈተና ካለፋችሁ በኋላ ሰነዶች የማስገቢያ ቀናት ከሚያዝያ 8-10/2017 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ቅበላ ቢሮ፣ ሬጅስትራር ህንጻ ቢሮ ቁ. 203


#Digital_ID

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ማውጣት ይጠበቅባቸዋል።

ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች እና ሰራተኞችን መረጃ በተደራጀ መልኩ እንዲይዙ እና የሀገር አቀፍ ፈተናዎችን ደኅንነት ለማስጠበቅ ጠቀሜታ አለው ተብሏል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ኮራ ጡሹኔ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጻፉት ሰርኩላር፤ በዚህ ዓመት ሰኔ 2017 ዓ.ም ላይ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ሁሉም የግል እና የመንግሥት ዕጩ ተመራቂዎች የፋይዳ መታወቂያ እንደ ቅድመ ሁኔታ የተቀመጠ መሆኑን አስታውሰዋል።

በመሆኑም ሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂ ተማሪዎቻቸው የፋይዳ መታወቂያ እንዲያወጡ እንዲያደርጉ እና የተማሪዎቹን የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ቁጥር በኤሜል አድራሻ eyobie2002@yahoo.com በኩል እንዲልኩ አሳስበዋል።

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ምዝገባ ማድረግ መጀመራቸው ይታወቃል።


#MoE

የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ለአንድ ዓመት እንዲያስተምሩ የሚያደርግ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ታስቧል።

ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ማኅበረሰቡን ለአንድ ዓመት በቅድሚያ እንዲያስተምሩ ወይም እንዲያገለግሉ የሚያደርግ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን አስታወቀ።

ትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ውጤት ዝቅተኛ የሆነበትን መንስዔ በተመለከተ ጥናት አቅርበዋል።

ውይይትም ሲደረግ ነበር።

በዚህም ወቅት በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ስለተያዘው እቅድ አብራርተዋል።

ላለፉት ዓመታት (እሳቸው  በኃላፊነት ከተሾሙ ጀምሮ) ፣ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ውጤት በከፍተኛ ደረጃ ዝቅተኛ  እንዲሆን ካደረጉ መንስዔዎች መካከል፣ የመምህራን ብቃትና የተነሳሽነት ማነስ ተጠቃሽ መሆናቸው ጠቁመዋል።

ችግሩን በአጭር ጊዜ ለመፍታት እንዲቻል የተለያዩ ተግበራት እየተሰሩ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

'' የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ሰርቪስ '' የሚል መጠሪያ የተሰጠው አሠራር ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ዕቅድ የተያዘ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ " በአራት ዓመት የሚመረቅ ተማሪ፣ የሦስተኛ ዓመት ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ ወደ አስተማረው ማኅበረሰበብ ተመልሶ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ይሰጥና (ማኅበረሰቡን እንዲያገለግል ይደረግና) እንዲመረቅ ይደረጋል " ሲሉ ተናግረዋል።

ይህም ሲሆን የተማሪዎቹ መሠረታዊ ወጪ የሚሸፈን እንደሚሆንም አክለዋል።

ይህ አሰራር ለተማሪዎች ለራሳቸው የተግባር ትምህርት እንደሚሆንና የበለጠ እንዲበስሉ እንደሚያደርጋቸውም ተናግረዋል።

ተማሪዎች የመምህርነትን ሙያ ተላብሰው በዚያው ወደ ሙያው እንዲያመሩ ዕድል በመፍጠር ለጊዜውም ቢሆን በዘርፉ እየቀነሰ የመጣውን ወደ ሙያው የሚገባ የአስተማሪን ቁጥር ለማሳግ እንደሚረዳም ሚንስትሩ አብራርተዋል።

በቅርቡ በመምህራን ላይ በተደረገ ግምገማ ፣ 100,000 የሚደርስ የመምህራን ዕጥረት መኖሩ መታወቁን የተናገሩት ብርሃኑ (ፕሮፌሰር)፣ አሰራሩ በከፍተኛ ደረጃ ያለውን የመምህራን ዕጥረት እንዲቀንስ የበኩልን እንደሚወጣ አስረድተዋል።

ወደ መምህርነት ሙያ የሚገቡ ሰዎችን ክፍተት ለማስተካከል ከተያዙ ዘርፈ ብዙ የማትጊያ ሥርዓቶች አንዱ፣ መምህራን በአገሪቱ የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ የራሳቸው ድርሻ እንዲኖራቸውና የኑሮ ውድነቱን እንዲቋቋሙ ለማድረግ፣ " የመምህራን ባንክ " ማቋቋም አንዱ እቅድ መሆኑን አንስተዋል።

ባንኩ " በአንድ ዓመት ውስጥ ወደ ሥራ ይገባዋል ብለን እንጠብቃለን " ያሉት ሚኒስትሩ፣ በ2019 ዓ.ም ደግም በእርግጠኝነት ወደ የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ሰርቪስ አሰራር እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።


Maths For Social - Hamle 2015 - booklet 391.pdf
8.2Mb
📘የሀምሌ 2015 ዓ.ም የሶሻሎች ማትስ ኢንትራንስ ፈተና ከነመልሱ

🎯JOIN US 👇👇


Maths for Natural - Hamle 2015 - booklet 341_2.pdf
6.0Mb
📘የሀምሌ 2015 ዓም የናቹራሎች ማትስ ኢንትራንስ ፈተና ከነመልሱ

🎯JOIN US 👇👇




Global HandOut ቀለሜ .pdf
1.6Mb
📒 Global Handout!
━━━━━━━━━━━━━━━━━
📚••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬, |


Global Trends summary notes full Hayat II.pdf
775.1Kb
🎯 Global trends Handout

✔️Short
━━━━━━━━━━━━━━━━━
📚••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬, 
                    

20 last posts shown.