"ኢትዮጵያ የወደብ ፍላጎት ጥያቄዋን አሁንም አልቀየረችም" የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርኢትዮጵያ የወደብ ፍላጎት ጥያቄዋን አሁንም አልቀየረችም፤ የባሕር በር የማግኘት ብሔራዊ ጥቅሟን መጠየቅ ትቀጥላለች ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ተናገሩ።
የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግንኙነት ከውጥረት ወደ መደበኛ ግንኙነት መቀየሩንም የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የሚኒስትሩ ቃል አቀባይ በዛሬዉ ዕለት በሰጠጡት ሳምንታዊ መግለጫ፤ "በሳምንቱ ጉልህ ስፍራ የተሰጠው ፖለቲካል ዲፕሎማሲ ከሶማሊያ ጋር የተደረገውና የታደሰው ስምምነት ነው" ሲል ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትላትናው ዕለት በሶማሊያ ባደረጉት የሥራ ጉብኝት ከፕሬዚደንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ ጋር መወያየታቸው፤ ግንኙነቱ በአዲስ መንገድ መሄዱ መጀመሩ ማሳያ ነው ሲሉም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡
ሀገራቱ ከዚህ ባለፈም አሸባሪነትን ለመዋጋት በተለይም አልሻባብን ለመዋጋት በጋራ ለመስራት መወሰናቸውን አምባሳደር ነብያት ገልጸዋል።
ይሁን እንጂ አሁን ላይ ሀገራቱ ጥሩ ግንኙነት ቢኖራቸውም፤ "ኢትዮጵያ ዛሬም መቼም የወደብ ፍላጎት ጥያቄዋን አልቀየረችም" ሲሉ ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ለጋራ ጥቅም ትብብራቸውን ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆናቸውን በትላትናው ዕለት በጋራ ባወጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ማስታወቃቸው አይዘነጋም።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ