ዛሬ ንጋት ላይ ከፊል የጨረቃ ግርዶሽ መታየቱን የኢትዮጵያ እስፔስ ሳይንስና ጂኦ እስፓሻል ኢንስቲትዩት አስታወቀ!!
ሠመራ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ እስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲዩት እንዲሁም እስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ጋር በመተባበር የጨረቃ ግርዶሽ ትዕይንት ለዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሰብና ለሠመራና አካባቢ ህብረተሰብ በሠመራ ዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ ተከናውኗል። የኢትዮጵያ እስፔስ ሳይንስና ጂኦ እስፓሻል ኢንስቲትዩት የእስፔስ ሳይንስ ተመራማሪ ዶክተር ኤፍሬም በሺር ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ክስተቱ መሬት በጸሃይና ጨረቃ መካከል ስትሆን የሚከሰት ነው።
ይህም በተለያዩ ደቡብ አሜሪካና አውሮፓ አገራት እንዲሁም ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች የተከሰተ መሆኑን ገልጸዋል።በአገራችንም በተለያዩ አካባቢዎች በከፊል የጨረቃ ግርዶሽ ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ታይቷል ብለዋል።
ከዚህም ውስጥ በአፋር አካባቢ ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ከፊል የጨረቃ ግርዶሹ ሲጀምር በቀላሉ በአይን ሲታይ እንደነበር ገልጸዉ፤ በሂደት ጭጋጉ እይታ የሚከለክል ቢሆንም በተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ትዕይንቱን መመልከታቸዉን ጠቁመዋል።
ፕሮግራሙ በአፋር የተዘጋጀዉ ህብረተሰቡ ሳይንስ የመጠቀም ባህሉን ለማጎልበትና በአካባቢዉም ከሌሎች አካባቢዎች በተሻለ ለትዕይንቱ ያለዉን ምቹ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ ከፊል ግርዶሹን በተሻለ በጥራት ማየት ስለሚቻል መሆኑን ተናግረዋል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ