ከትግራይ ክልል የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ሥራ ተጀመረ
ከትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በአፋር ክልል በመጠለያ ጣቢያዎች የነበሩ ወገኖችን ወደ መኖሪያ ቀያቸው የመመለስ ሥራ ተጀመረ፡፡
ዛሬ በተጀመረው የመጀመሪያ ዙር ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ሥራ በአፋር ክልል ሠመራ፣ ሎጊያ እና ዱብቲ የመጠለያ ጣቢያዎች የነበሩ 738 የትግራይ ተወላጆች ወደ ቀያቸው ተመልሰዋል፡፡ በተጨማሪም በክልሉ ከዞን ሁለት ኪልበቲ ረሱ፣ ባራሕሌ፣ ኮነባ እና ዳሎል የተፈናቀሉ ወገኖችንም ወደ ቀያቸው ለመመለስ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የአፋር ክልል ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት መረጃን ጠቅሶ ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja