TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
ETHIO-MEREJA®

24 Jan, 16:01

Open in Telegram Share Report

የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ በነገው ዕለት ይጀመራል

የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ በነገው ዕለት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በሚደረግ ሥርዓተ ጸሎት እንደሚጀመር ተገለጸ።

በወሊሶ አካባቢ በብፁዕ አባ ሳዊሮስ መሪነት በተፈፀመው ኢ-ቀኖናዊ "የኤጲስ ቆጶሳት" ሢመትን አስመልክቶ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ባደረጉት አስቸኳይ ጥሪ መሠረት፤ ከእሁድ ጥር 14 ቀን 2015 ጀምሮ በአገር ውስጥ እና በውጭ አገራት የሚገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ወደ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት እየገቡ ይገኛሉ።

በዚህም መሰረት፤ የቅዱስ ሲኖዶሱ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ በነገው ዕለት አመሻሽ ላይ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በሚደረግ ሥርዓተ ጸሎት የሚጀመር መሆኑን ከተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

በርካታ አህጉረ ስብከት የተፈፀመውን የቀኖና ጥሰት አስመልክቶ እንደማይቀበሉት እየገለጹ የሚገኙ ሲሆን፤ መላው ኦርቶዶክሳውያንም በአሁኑ ሰዓት የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ናቸው።

በሕገ ወጥ መንገድ "ኤጲስ ቆጶሳት" ተብለው ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለመውረር የተላኩት መነኮሳት በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ሆቴሎች በመዘዋወር እየኖሩ እንደሚገኙም ለማረጋገጥ መቻሉን የተ.ሚ.ማ መረጃ አመላክቷል።
    ------ETHIO-MEREJA-----
       T.me/ethio_mereja

23.9k 0 11 14 103
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Blog Telegram Research 2019 Telegram Research 2021
Contacts
Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot