ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በምዕራፍ ሁለት የገነባውን የኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል መረቁ
ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በምዕራፍ ሁለት በ11ሺህ 500 ካሬ ሜትር ላይ የገነባውን የኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል መረቁ።
ሆቴሉን መርቀው የከፈቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አየር መንገዱ ዘላቂ የሆነ ተቋማዊ ስርዓት መዘርጋቱ ስኬታማ ያደረገው ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን አንስተው፤ ሌሎች ተቋማትም በዚህ መንገድ መጓዝ እንዳለባቸው ገልጸዋል። አየር መንገዱ ለሁሉም ኩራትና አርዓያ መሆኑን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አየር መንገዱ ከዚህ ቀደም መሸጋገሪያ ብቻ ሆኖ ያገልግል የነበረበት ሂደት ሆቴሉን በመገንባት መቀየር የቻለ መሆኑን የሚያስደንቀው ነው ብለዋል።
ግዙፍና ቅንጡ የሆነው ቁጥር ሁለት ስካይላይት ሆቴል 651 የመኝታ ክፍሎች ያሉት ሲሆን የተለያዩ ምግብ እና ቡና ቤቶች ፣ የስብሰባ አዳራሽ ፣ የጤና ማዕከል እንዲሁም 550 መኪኖች የሚይዝ የመኪና ማቆሚያ አካቶ የያዘ መሆኑን የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ገልፀዋል፡፡ የሆቴሉን ግንባታ ያከናወነው የቻይና ህንጻ ተቋራጭ ኩባንያ ሲሆን የሆቴሉ አጠቃላይ ወጪ 155 ሚሊዮን ዶላር መሆኑ ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት በመስጠት እ.ኤ.አ በ2025 በአፍሪካ ቀዳሚ የአቪየሽን ግሩፕ ለመሆን ራዕይ ሰንቆ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን ስካይ ላይት ሆቴል አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለው ስለመሆኑ መገለፁን ኢቢሲ ዘግቧል፡
---ETHIO-MEREJA---
T.me/ethio_mereja