በቡራዩ ሁለት ህጻናት በአሳዳጊያቸዉ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ
በሸገር ከተማ አስተዳደር ቡራዩ ክ/ከተማ ከታ በተሰኘዉ አካባቢ እድሜያቸዉ የ 12 እና 4 አመት የሆኑ ወንድምና እህት በአሳዳጊያቸዉ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ተሰምቷል።
የ12 አመት ታዳጊ የሆነዉ ናኦል ጌቱ እና የ 4 አመቷ ህጻን የሆነችዉ ናኑ ጌቱ ከትናንት በስቲያ ሌሊት የቤት ሰራተኛ ሆና ወደ ቤታቸዉ በገባችና በኋላም ከሟቾቹ ህጻናት አባት ጋር የፍቅር ግንኙነት አላት በተባለችዉ "ነጋሴ ከበደ" ግድያ ተፈጽሞባቸዋል። ግለሰቧ ህጻናቱን በማረድ ከገደለች በኋላ አስክሬናቸውን በእሳት ማቃጠሏም ነዉ የተሰማዉ።
በሸገር ከተማ የቡራዩ ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ረዳት ኮሚሽነር ሽቱ ለኪሳ በተለይ እንደተናገሩት ፤ ግለሰቧ ራስዋን "ትግስት" ብላ የምትጠራ ሲሆን ድርጊቱን ከፈጸመች በኋላ ከአካባቢዉ መሰወሯን ገልጸዋል።"ነጋሴ ከበደ" አልያም ራሷን "ትግስት" የምትለዉ ግለሰብ ፤ ከሟች ህጻናቶቹ አባት ጋር ግንኙነት እንደነበራቸዉና ከሶስት ወራት በፊት ተጋጭተዉ ከቤት መዉጣቷን ረዳት ኮሚሽነር ሽቱ ተናግረዋል። በኋላም በእርሷ ቤተሰቦች አሸማጋይነት ሁለቱ ጥንዶች እርቅ አድርገዉ ወደ ቤት መመለሷን ይገልፃሉ።
ሆኖም አባት በከተማዉ ባለ የቄራዎች ድርጅት ሰራተኛ እንደመሆኑ እንደተለመደዉ ከትናንት በስቲያም በሌሊት ወደ ስራ ያቀናል። በዚህ ወቅትም ግለሰቧ ቤቱ መቃጠሉን ለአባት በስልክ ታሳዉቃለች። በኋላም አባት በቦታዉ ሲደርስ እና የህጻናቱ አስክሬን ሲገኝ ህጻናቱ ላይ ጉዳት እንደደረሰባቸዉ ይረጋገጣል።
ግለሰቧም ከአካባቢው ራሷን መሰወሯን እና ፖሊስም በፍለጋ ላይ መሆኑን በሸገር ከተማ የቡራዩ ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ረዳት ኮሚሽነር ሽቱ ለኪሳ ጨምረዉ ተናግረዋል።
---ETHIO-MEREJA---
T.me/ethio_mereja