በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የተመራ ልዑክ በአንዋር መስጂድ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ጎበኘ!!
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጅ ኢብራሂም ቱፋ የተመራ ልዑክ፤ ትላንት አርብ ግንቦት 18/2015 በአዲስ አበባ ከተማ አንዋር መስጂድ በጸጥታ ኃይሎች ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተገኝተው ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጅ ኢብራሂም ቱፋ፤ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሱልጣን አማንን፣ የፌደራል መጀሊስ አማካሪ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል እንዲሁም የአዲስ አበባ መጅሊስ ሥራ አስፈፃሚ እና ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ካሊድ መሀመድ ተገኝተው የተጎዱትን ማጽናናታቸውን የአ/አ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት አስታውቋል።
በተያያዘ ዜና፤ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንቱ ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ትናንት በታላቁ አንዋር እና ኑር (ሠፈር በኒ) መስጊዶች ከስግደት በኋላ በሙስሊሞችና ፖሊስ ጋር በተፈጠረው ግጭት ዙሪያ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች ጋር መወያየታቸውን ምክር ቤቱ አስታውቋል።
በውይይቱ ግጭቱን ተከትሎ የተዘጋው ኑር መስጊድ ለሰላት ክፍት እንዲኾን እንደተደረገ ምክር ቤቱ ገልጧል።
ወደፊት ተመሳሳይ ችግር እንዳይፈጠር፣ ከፖሊስ፣ ከጠቅላይ ምክር ቤቱና ከአዲስ አበባና ኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤቶች የተውጣጡ መፍትሄ አፈላላጊ ቡድኖች መቋቋማቸውን ምክር ቤቱ ጨምሮ አስታውቋል።
---ETHIO-MEREJA---
T.me/ethio_mereja