📍መገናኛ
"የመሬት ውስጥ የእግረኛ መተላለፊያ መስመር ግንባታ ተጀምሯል ፤ ለገንቢው እንዲያጠናቅቅ የተሰጠው 45 ቀናት ነው " - አቶ ጥራቱ በየነ
ከፍተኛ መጨናነቅ ባለበት " መገናኛ ' አካባቢ የመሬት ውስጥ የእግረኛ መተላለፊያ መስመር ግንባታ መጀመሩ ተገልጿል።
በአዲስ አበባ ከፍተኛ የሆነ የትራፊክ መጨናነቅ ያለበት ፣ መኪና የሚበዛበትና የሚገናኝበት ፣ እጅግ በርካታ እግረኞችም የሚንቀሳቀሱበት ስፍራ ነው " መገናኛ " አካባቢ። በዚህ አካባቢ ያለውን ከፍተኛ የሆነ የትራንስፖርት መጨናነቅ ለመፍታት ያግዛል የተባለ የመሬት ውስጥ ለውስጥ የእግረኛ መተላለፊያ መሰራት ጀምሯል።
ይህ ፕሮጀክት ከቦሌ ኤርፖርት እስከ መገናኛ ባለው የመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት ስራ አንዱ አካል እንደሆነ ተመላክቷል።
ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ምን አሉ ?
" ..የታክሲ መጫኛና ማውረጃ ተርሚናልም ይገነባል በማዶ በኩል። በሙልጌታ ህንጻ ስርም ሁለት ወለል ያለው ተርሚናል ይገነባል።
እግረኞች ከአንዱ ተርሚናል ወደሌላኛው ተርሚናል የሚገናኙት በመሬት ውስጥ ይሆናል። ከላይ ምንም አይነት የሰው እንቅስቃሴ በማይኖርበት ወይም በኒቀንስበት ሁኔታ ነው እየሰራን ያለነው። ገንቢው ተቋራጭ ይህንን ስራ እንዲያጠናቅቅ የተሰጠው ጊዜ 45 ቀን ነው።
ለ45 ቀናት በ3 ሺፍት ነው የምንሰራው። ከዛም ባጠረ ጊዜ ለማጠናቀቅ ከሚሰሩት ኮንትራክተሮች ጋር ተግባብተናል " ብለዋል። የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የሚያማክረው ሲሆን" የመገናኛ እግረኛ መተለለፊያ ስራ በአይነቱ የተለየ እና ዘመናዊ ነው " ብሎታል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ