የሶማሊያ መንግስት ኢትዮጵያ ጦሯን ወደ ኪስማዮ አስገብታለች ሲል ያቀረበውን ክስ ጁባላንድ ውድቅ አደረገች
የጁባላንድ የደህንነት ሚኒስትር ጄኔራል ዩሱፍ ሁሴን ኦስማን ዱማል የሶማሊያ ፌዴራል መንግስት ሁለት የጦር መሳሪያ የጫኑ የኢትዮጵያ አውሮፕላኖች ቅዳሜ ዕለት ኪስማዮ አርፈዋል ሲል ያቀረበውን ክስ ውድቅ አድርገዋል። ሚንስትሩ፤ ወቀሳውን “መሰረ-ቢስ” ሲል ጠርተው “መንግስት ያለ ማስረጃ እንዲህ ያለ ክስ ማቅረብ የለበትም” ሲሉ ለቪኦኤ ሶማሊ ተናግረዋል።
ዱማል አክለውም የኢትዮጵያ ወታደሮች በቡላ ሃዎ ውስጥ የጦር ሰፈር ለመመስረት ሲሞክሩ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል በማሉንም ውድቅ አድርገዋል። እንደ ጌዶ፣ ባይ፣ ባኮል እና ሂራን ባሉ ክልሎች የኢትዮጵያ ኃይል መኖራቸውን በመጥቀስ ይህም የተለመደ እንቅስቃሴዎች ነው ብለዋል።
ሚንስትሩ ይህን አስተያየት የሰጡት የሶማሊያ ምክትል የመረጃ ሚኒስትር አብዲራህማን ዩሱፍ አል-አዳላ ኢትዮጵያን "ህገወጥ እና ተስፋፊ እንቅስቃሴዎች" አድርጋለች በማለት መክሰሳቸውን ተከትሎ ነው። አል-አዳላ ኢትዮጵያ የጦር መሳሪያዎችን ወደ ፑንትላንድ እና ጋልሙዱግ እያስገባች እና በሂርሻቤሌ ውስጥ ሚሊሻዎችን እየመለመለች ነው በማለት ከሰዋል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ