በ69 ቀናት የተጠናቀቀው የአዲስ አበባው ባለ 9 ወለል ሕንጻ!!
በሃገራችን የምህንድስና የእድገት ደረጃ አዲስ ታሪክ የተፃፈበት ፈጣኑ ህንፃ በ69 ቀኑ ዛሬ ተጠናቀቀ።
የአ/አ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ልዩ ድጋፍ ሲያደርጉ በቆዩበት በቂርቆስና በልደታ ክ/ከተሞች በ60 /90 ቀናት ፕሮጀክት ተጀምረው የነበሩት ዘመናዊ ቴክኖሎጂን የሚጠቀሙት ባለ 11 ባለ 9 እና ባለ 5 ወለል ህንፃዎች ለከተማችን አዲስ አሻራ አዲስ ታሪክ እና አዲስ የስራ ባህልን እያስመዘገቡ ነው፡፡
እነሆ የዚሁ ፕሮጀክት አካል የሆነው በቂርቆስ ክ/ከተማ ሲገነባ የቆየው ባለ 9 ወለል ህንፃ በዛሬው እለት በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ የመጨረሻውን ወለል ጣሪያ በመምታት ውብ በሆነ መንገድ ማጠናቀቅ የተቻለ ሲሆን አዲስ ታሪክም ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ፈጣኑን ቴክኖሎጂ እየተገበረ ያለው ይህ ፕሮጀክት የኩምካንግ አልሙኒየም ፎርምወርክ ቴክኖሎጂ (KumKnang Aluminum formwork technology) በመባል የሚታወቀውን የተለመደውን የኮንስትራክሽን ሂደት እጅግ ባሳጠረ መንገድ የሚተገበር ድንቅ ቴክሎኖጂ ነው፡፡
ልስን ቁርቋሮ ማፅዳት ትራንስፖርት የሚባሉ ጣጣዎችን በሙሉ በማስቀረት የሚተገበረው ይህ ስራ የከተማችንን የቤት ጥያቄ ለመመለስና በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤት ለማምጣት እንደሚቻል ትክክለኛ ማሳያ ሆኖ የሚያገለግል ነው፡፡
Source: አ/አ ኘረስ ሴክሬቴሪያት
@ethio_mereja_news