የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት "ከትጥቅ ትግል ወደ ሰላም ዕድል" በሚል ርዕስ ለመጀመሪያ ጊዜ ባወጣው የፖለቲካ ማንፌስቶ በኦሮሚያ ክልልና በአገሪቱ ለሚታዩ ግጭቶችና ቀውሶች ብቸኛው መፍትሄ፣ "ዓለማቀፍ አደራዳሪ አካል የሚመራው ሁሉን አካታች የፖለቲካ ድርድር" ማድረግ ብቻ እንደሆነ ገልጧል።
ቡድኑ ለኦሮሚያው ግጭት "በድርድር ላይ የተመሠረተ ፖለቲካዊ መፍትሄ" ለማምጣት፣ ፌደራል መንግሥቱ አዲስ አበባን የኦሮሚያ አካል ማድረግ፣ አፋን ኦሮሞን የፌደራል የሥራ ቋንቋ ማድረግና በክልሉ የሚያካሂደውን ወታደራዊ ዘመቻ ማቆምን ጨምሮ በቅድሚያ መውሰድ አለበት ያላቸውን "የመተማመኛ ርምጃዎች" በማንፌስቶው ዘርዝራል።
የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን በበላይነት የሚመራው፣ የሠራዊቱ አባላትና ደጋፊዎች ከዓመት በፊት ባካሄዱት ጠቅላላ ጉባዔ የመረጠት የፖለቲካና ወታደራዊ ክንፎችን ያጣመረው "የኦነግ-የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጠቅላይ ዕዝ" መሆኑን ማንፌስቶው አስፍሯል።
@ethio_mereja_news