ሙሽራ አጅበው ሲሄዱ የነበሩ ስድስት ሰዎች በመኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈ
በሐረሪ ክልል ትናንት ምሽት በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።
አደጋው የደረሰው ትናንት ምሽት አራት ሰዓት ተኩል አካባቢ በክልሉ ሶፊ ገበሬ ማህበር ቂሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የከፍተኛ አደጋ መርማሪ ዋና ሳጅን ረስተም መዝሃር ገልጸዋል።
የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ3- 88036( ኦሮ) የጭነት አይሱዙ እቃ ጭኖ ከአወዳይ ወደ ጅጅጋ በመጓዝ ላይ እንዳለ ሙሽራን አጅበው የነበሩ የአካባቢ ነዋሪ ሰርገኞችን ገጭቶ መንገዱን ስቶ በመገልበጥ አደጋው መድረሱን አስረድተዋል።
በአደጋውም ዕድሜያቸው ከ20 እስከ 25 የሆኑና አጃቢ የነበሩ የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉንና ከሟቾቹም መካከል አምስቱ ሴቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።
በተጨማሪም በስምንት ሰዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ዋና ሳጅን ረስተም ጠቁመዋል፡፡
አደጋ ያደረሰው የተሽከርካሪው ሹፌር ለጊዜው ከአካባቢው ሸሽቶ ቢያመልጥም ለመያዝ ክትትል እየተደረገበት መሆኑን ጠቁመው፤ የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን አስረድተዋል።
የትራፊክ አደጋን ለመከላከል አሽከርካሪዎች ፍጥነታቸውን በልክ አድርገው እንዲያሽከረክሩ ዋና ሳጅኑ አሳስበዋል ሲል ኢዜአ ነው የዘገበው።
@ethio_mereja_news