NewsAlert‼️
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ እየሱስ በጋምቤላ ክልል ባንድ የቤተክርስቲያኗ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ የደቡብ ሱዳን ሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ግንቦት 12 ቀን ባደረሱት ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች እንደተገደሉ ዛሬ ባወጣችው መግለጫ አስታውቃለች።
ጥቃቱ 11 ሰዓት ገደማ የተፈጸመው፣ በምዕራብ ጋምቤላ ቤተል ሲኖዶስ አገልግሎት ክልል "ማታራ" በተባለ ቀበሌ ውስጥ መኾኑን መግለጫው አመልክቷል።
ከ2 ሺህ 700 በላይ የመንፈሳዊ ጉባዔው ተሳታፊ ወጣት ሴቶች፣ እናቶችና ሕጻናት የዕለቱን መንፈሳዊ መርሃ ግብር አጠናቀው ለእራት በተቀመጡበት ወቅት፣ ድንገት የደረሱ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ሕጻናትን አፍነው ለመውሰድ በሞከሩበት ወቅት በተፈጠረ ግብግብ፣ መንፈሳዊያኑ ላይ ተኩስ እንደከፈቱ ቤተክርስቲያኗ ጨምራ ገልጣለች።
ከተገደሉት መካከል አንዲት ሕጻን እንደምትገኝበትና፣ በጥቃቱ የቆሰሉ በርካታ ምዕመናን ጋምቤላ ሆስፒታል ውስጥ ሕክምና ላይ እንደኾኑም በመግለጫው ላይ ተገልጧል። [ዋዜማ]
@ethio_mereja_news