በሀዋሳ ልታገባ ቀናቶች ብቻ የቀሯት ወጣት መጠለፏ ተሰማ!
የዳሽን ባንክ ሰራተኛና የሀዋሳ አላሙራ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆነችው ፀጋ በላቸው በሀዋሳ ከንቲባ የግል ጠባቂ በሆነው ተጠርጣሪ ኮንስታብል የኋላመብራት ወ/ማሪያም ታግታ(ተጠልፋ) ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዷም ተገልጿል።
ፀጋ በላቸው ትባላለች፤ ትውልድና እድገቷ በወልቂጤ ከተማ ሲሆን ግንቦት 15 2015 ዓ.ም ስራዋን አጠናቃ ወደቤቷ በምታመራበት ሰዓት (አሮጌው መነሀሪያ አከባቢ፤ ከምሽቱ 1 ሰዓት) ከዚህ ቀደም ይዝትባት በነበረና የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ፀጋዬ ቱኬ የግል ጠባቂ በሆነው ተጠርጣሪ ኮንስታብል የኋላመብራት ወ/ማሪያም ታግታ(ተጠልፋ) ወዳልታወቀ ቦታ ተወስዳለች። ከተጠለፈች 6 ቀን አልፏታል።
ጉዳዩን ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በማሳወቅና የፍርድ ቤት መጥሪያ በማውጣት ተጠርጣሪውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ለማዋል የተደረገው ሙከራ ጥረት ካለማስገኘቱም በላይ የህግ አካላት ድርጊቱን ቀለል አድርገው ለመመልከት ሞክረዋል።
በሐዋሳ ከተማ ውስጥ ተመሳሳይ ድርጊቶች እየተበራከቱ መምጣቸው የከተማዋን ስም የሚያጎድፍ፤ የሴት እህቶቻችንን የግል ውሳኔ የማያከብርና የነዋሪውን ነፃነት የሚጋፋ በመሆኑ የከተማው፣ የክልሉና የሚመለከታቸው የፌደራል መስሪያ ቤቶች ይህንን ለመፍታት ተገቢውን ርቀት በመጓዝ ተጠርጣሪውን ለህግ እንዲያቀርቡልን እንጠይቃለን።
ቤተሰቦቿ በከባድ ጭንቀት ውስጥ ይገኛሉ።
ፍትህ ለእህታችን (ቤተሰቦቿ እና ጓደኞቿ )
Share | ሼር
@ethio_mereja_news