አሳዛኝ ዜና‼️🕯🕯
በአርሲ ሀገረ ስብከት በጢዮ ወረዳ በዴራ አማኑኤል አጥቢያ ቤተክርስቲያን "ሸኔ" በተባለ ታጣቂ ቡድን በኦርቶዶክሳዊያን ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ ግድያ መፈፀሙን ተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል ዘገበ!
በአርሲ ሀገረ ስብከት በጢዮ ወረዳ በጨፌ ሚሶማ ቀበሌ ገበሬ ማኀበር ( #ከአሰላ ከተማ በቅርብ ርቀት የሚገኝ) በዴራ አማኑኤል አጥቢያ ቤተክርስቲያን በግንቦት 20 ለ 21 ቀን 2015 አጥቢያ ከሌሊቱ 5 ሰዓት ጀምሮ በኦርቶዶክሳዊያን ላይ ጥቃት ደርሷል።
የዚህም ጥቃት ሰለባ የሆኑትና በአሰቃቂ ሁኔታ ግድያ የተፈጸመባቸው ቄስ ታደለ የቡልጋወርቅ እድሜ 46 ሲሆኑ የስድስት ልጆች አባት እና የቤተሰብ ኃላፊ ፣ ቄስ ካሱ መንገሻ እድሜ 72 አዛውንት ሲሆኑ የአራት ልጆች አባት እና የቤተሰብ ኃላፊ ፣ ወጣት እንዳለ የቡልጋወርቅ እድሜ 34 የአንድ ልጅ አባት ፣ አቶ አድነዉ ቶላ የቤተክርስቲያን የጥበቃ ሠራተኛ ሲሆኑ እድሜያቸውም 55 አመታቸው እና የሁለት ልጆች አባት ናቸው ሲሆኑ በጥይት በግፍ ገድለዋቸዋል።
በተጨማሪ ፋንታሁን ዳኛቸዉ እና ስንታየሁ ዳንኤል የ12 ዓመት ሴት ልጅ አፍነው ወስደው ለመልቀቅም ቤተሰቦቻቸውን ገንዘብ እንዲከፍሉ በመጠየቅ ላይ እንደሚገኙ ተዘግቧል።
በአከባቢው እና በአቅራቢያው ያሉ ንፁሀን ዜጎችም ለደህንነታቸው ስጋት እንዳደረባቸው እና መንግስት አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርግላቸው በአፅንኦት ጠይቀዋል።
ፎቶ - ስምዐ ተዋሕዶ
(ምንጭ ፣ ተሚማ)
@ethio_mereja_news