ስፖርትና እውቀትን በማቀናጀት በትምህርት ጥራት ላይ የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጥል እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታወቁ፡።
………………………………………………………………………….
(ጥር 18/2017 ዓ.ም) የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ተከፍቷል።
የትምህት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፌስቲቫሉን ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግር ስፖርትና እውቀትን ከትምህርት ጥራት ስራዎች ጋር በማስተሳሰር የአገርን እድገት ከፍ ማድረግ ይገባል፡፡
የአእምሮ እድገትና የአካል እድገት የተሳሰሩ መሆናቸውን የጠቆሙት ሚኒስትሩ ተወዳዳሪዎች በቆይታቸው ሰላምን ወዳጅነትና አብሮነትን በማስቀደም የስፖርት ፌስቲቫሎችን ማካሄድ እንደሚጠበቅባቸውም ተናግረዋል። ለሙሉ መረጃው ይህንን ሊንክ ይጫኑ።
https://www.facebook.com/share/p/1DzHGg4X57/