ስለ እርግዝና ያልተሰሙ አስደናቂ እውነታዎች !
1. የጠዋት ሕመም (morning sickness) የሚባለው ሁሌ ጠዋት የሚከሰት አይደለም፡፡ ብዙ ሴቶች ቀኑን ሙሉ አንዳንዶች ድግሞ ጠዋት፣ግማሽ ቀን ወይም ማታ ስሜቱ ሊታያቸው ይችላል፡፡
2. እረጃጅምና ዕድሜያቸው ከ35 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች መንታ ልጅ የመውለድ ዕድላቸው ሰፊ ነው፡፡ ከቤተሰብ ውስጥ መንታ የወለደ ሰው ካለና ዕድሜዎት ከ35 በላይና ረጅም ከሆኑ መንታ ልጅ የመውለድ ዕድል አልዎት፡፡
3. የደም መጠኖ ይጨምራል፡፡ በልብዎ የሚሰራጨው የደም መጠን ከ40 እስከ 50 በመቶ ይጨምራል፡፡
4. የልብዎ መጠን በእርዝመትም በወርድም ይጨምራል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ተጨማሪ ደም ለመርጨስ ሲል ይለጣጣል፡፡
5. እርግዝና ከተከሰተበት ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ጡት ወተት ለማምረት ይዘጋጃል::
6. ልጅዎ ይሰማዎታል፡፡ ጆሮ ቀደም ተብለው ከሚሰሩት የህፃኑ አካለት አንዱ ሲሆን ልጅዎም የእለት ተዕለት ንግግሮን ይሰማል፡፡ በተለይ ከ6 ወራት ጀምሮ ብቻዎን ስላልሆኑ ልጅዎን ያናግሩ፡፡
7. ልጆ ከእርስዎ ቀድሞ ይበላል፡፡ ማንኛውም የሚመገቡት ቫይታሚንና ማእድናት ልጆ ከተጠቀመ በኃላ ነው የቀረው ወደ እርሶ የሚደርሰው፡፡ ለዚህም ነው በእርግዝና ጊዜ ጥሩ ጥሩ ነገር መመገብ ለልጆ ጤንነት ወሳኝ ነው የሚባለው፡፡
8. በእርግዝና ጊዜ ምግብ ቀስ ብሎ ወደ ትንሹ አንጀት ስለሚሄድ ሆድ በጋዝ ሊሞላ ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የአይነምድር ድርቀት ሊያጋጥም ይችላል፡፡ ስለሆነም ለብ ያለ ውሃ በብዛት መጠጣት ሊያስታግሰው ይችላል፡፡
9. የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ ይቻላል፡፡ይሕ ማለት ዕርግዝናው ጤናማ እስከሆነ ብቻ ነው፡፡፡ ውስብስብ የሆነ እርግዝና ከሆነ ግን ሐኪም ማማክር ግድ ይላል።
Join us share
'https://t.me/+S_s2mCEI9Mv5OcVWዠ' rel='nofollow'>
https://t.me/+S_s2mCEI9Mv5OcVWዠ