ኩባንያችን ለሃገራችን ፈር ቀዳጅ የሆነውን ስማርት የመማሪያ ክፍል (SMART CLASS ROOM) ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አራት ኪሎ ካምፓስ በመገንባት በዛሬው ዕለትበ ይፋ ሥራ አስጀምሯል፡፡
የስማርት መማሪያ ክፍሉ የተለያዩ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የተሟሉለት ሲሆን የትምህርት ጥራትን እና አካታችነትን ለማረጋገጥ፣ የትምህርት መረጃዎችን በቀላሉ ለማግኘት፣ የቤተ ሙከራ ፍተሻዎችን በተሻለ ተሞክሮ ለማከናወን፣ የምዘና ፈተናዎችን ለመስጠት፣ ለማረም እና ውጤቶችን ወዲያውኑ ለማሳወቅ የሚያስችል ነው::
ተማሪዎች በስማርት የመማሪያ ክፍሉ በየትኛውም ጊዜና ቦታ በቀላሉ በቨርችዋል ክላስ ትምህርታቸውን መከታተል እንዲችሉ፣ በትምህርት አሰጣጡ የተሻለ ተሳትፎ እና ተሞክሮ እንዲኖራቸው ለማድርግ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል፡፡
ኩባንያችን የትምህርት ዘርፉን ለማሻሻል፣ አካታች፣ ወጪ ቆጣቢ እና ጥራት ያለው ትምህርት ለዜጎች እንዲደርስ እና የዲጂታል ኢትዮጵያን ራዕይ እውን ለማድረግ ሃገራዊ እና ማህበራዊ ሃላፊነቱን መወጣቱን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡
https://rb.gy/59c6b