ኢትዮ - ኮን ሬድዮ ፕሮግራም/Ethio con radio perogram/


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Music


በግንባታው ዘርፍ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሳምንታዊ የባለሙያዎች ፕሮግራም የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር ከአሀዱ ሬድዮ 94.3 ትብብር
ዘወትር ሰኞ ምሽት ከ2፡30-3፡30 ሰዓት የሚተላለፍ ሳምንታዊ ፕሮግራም ነው።

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Music
Statistics
Posts filter


🔵 የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያቀረቧቸውን ተሿሚዎች በሙሉ ድምፅ አፅድቋል ።

በዚህም መሰረት:-

1.  አቶ ወንድሙ ሴታ - በም/ከንቲባ ማዕረግ የአ/አ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ

2.  አቶ ተንኩዌይ ጆክ ሮም - የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ኃላፊ

3.  አቶ ይመር ከበደ ይማም የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽንኮሚሽነር

የቦታ ለውጥ ያደረጉ

1.  አቶ አደም ኑሪ - የፕላንና ልማት ቢሮ ሃላፊ

2.  አቶ ቢንያም ምክሩ - የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ

3. ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ - የንግድ ቢሮ ኃላፊ ሲሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን አጠናቅቋል::

(ኢቢሲ)


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ኢትዮ ኮን ህዳር 9፤ 2017


ምሸት 2:30 በአሀዱ ሬድዮ 94.3 የቀጥታ ስርጭት ይጠብቁን!


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
የከተማ ግንባታን በተመለከተ


የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከጀሞ 2 አደባባይ ወደ ጀሞ ሚካኤል በሚወስደው ጎዳና ላይ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ለማቃለል፤ ለፈጣን አውቶብሶች መተላለፊያ በተገነባው መስመር ላይ ተሸከርካሪዎች በፈረቃ የሚንቀሳቀሱበትን ሁኔታ አመቻችቷል፡፡

(የአዲሰ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሰልጣን)


Types of cracks in RCC beam


የሪል ስቴት ልማትና ግብይት እንዲቀላጠፍና አሰራሩ  ህግን የተከተለ እንዲሆን ለማስቻል እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

የሪል ስቴት ልማትና ግብይት እንዲቀላጠፍ እንዲሁም ከብልሹ አሰራር ነጻና ህግን የተከተለ እንዲሆን ለማስቻል እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ይህ የተገለጸው በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ፣ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሪልስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ባደረገበት ወቅት ነው።

ረቂቅ አዋጁ በሚወጣበት ወቅት የማይንቀሳቀስ ንብረት ግመታ ስርዓቱ ዘመናዊና በመረጃ በተደገፈ መልኩ ተገማች ዋጋ እንዲኖረው በማድረግ ከተሞች ልማታቸውን ማፍጠን በሚችሉበት ሁኔታ ለመምራትና የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ጋር ተያይዞ የሚመጣ የንብረት ዕሴት ጭማሪ መሰረት ተድርጎ የከተሞች የገቢ መሰረት ማስፋት እንደሚያስችል ተገልጿል።

በማይንቀሳቀስ ንብረት ገበያው ግልጽነት መጓደሉ የኢኮኖሚ መዛባት እያስከተለና የመንግስት ጥቅምን እያሳጣ ስለሚገኝ፣ ወደፊት ከአጠቃላይ ኢኮኖሚው ማደግ ጋር በተያያዘ የንብረት ገበያው እየሰፋ እንደሚሄድ ስለሚታወቅ ችግሩ አብሮ እንዳይሰፋ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ሲሉ የዘርፉ ባለሙያዎች ተናግረዋል።

በመሬት ላይ ለተደረገ ማንኛውም ንብረት ባለንብረቱ የንብረቱ ተገቢ የገበያ ዋጋ መረጃ ኖሮት የካፒታል ገበያው ተሳታፊ እንዲሆን አስፈላጊ ነው ተብሏል።

በማይንቀሳቀስ ንብረት ልማቱና ግብይቱ እንዲቀላጠፍ፤ ከብልሹ አሰራር የነጻና ህግን የተከተለ እንዲሆንና የተዋዋይ ወገኖችን ፍላጎት የሚያረካ፤ ጤናማ የኢኮኖሚ ግንኙነት እንዲኖርና የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ችግር እንዲቀረፍ የሚያግዝ ወጥነት ያለው የህግ ማዕቀፍ መኖር ስለታመነበት ረቂቅ አዋጁ መዘጋጀቱ ተገልጿል።

ከፍላጎት አንጻር የሪልስቴት ልማቱ አቅርቦት እጅግ ወደኋላ የቀረ በመሆኑ ቤት ለመግዛትና ለመከራየት የሚፈልጉ ወጎኖች በከፍተኛ ሁኔታ የሚቸገሩበት ሁኔታ መቀየር ስላለበት የሪል ስቴት ኢንቨስትመንትን ማበረታታትና የቤት አቅርቦት እንዲሻሻል ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረውም በመድረኩ ላይ ተብራርቷል።

በውይይት መድረኩም የቋሚ ኮሚቴው አባላት፣ የሪል ስቴት አልሚዎች፣ የአርክቴክቸር ማህበራት፣ ኮንትራክተሮች፣ የዩንቨርስቲ ምሁራን እንዲሁም የተለያዩ የሙያና የንግድ ማህበራት የተገኙ ሲሆን፤ በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ መነሳት የሚገባቸውን የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን እንዲሁም መሻሻልና መዳበር ይገባቸዋል ያሏቸውን ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።

(ፖርላማ)


4ተኛ አመት 3ተኛ መደበኛ የካቢኔ ስብሰባች ሁለተኛ ኮሪደር ስራ ያለበትን በጥልቀት ገምግሟል ።

በግምገማው በዋናነት ትኩረት ያደረግነው የልማት ተነሺዎች የተስተናገዱበትን አግባብ፤ በመንግስት የሚኖሩ የነበሩ የተነሱበት አግባብ፤ መሰረተ ልማት የተሟሉላቸው መሆኑን፤ በተመሳሳይ ሁኔታ የግል ተነሺዎች ደግሞ የካሳ የ3 አመት የቤት ኪራይ እና ምትክ መሬት መውሰዳቸውን ፤የትራንስፖርት አቅርቦት እና የሞራል ካሳ በህጉ መሰረት የተከፈለ መሆኑን የተተነተነ ሪፖርት በየኮሪደሩ አስተባባሪዎች ቀርቦ ተገምግሟል።

በግምገማውም ሁሉም ህጋዊ ውል ወይም ሰነድ ኑሯቸው እንዲሁም በመጠለያ በተገኙበት ተጠልለው የሚኖሩ ነዋሪዎችን ሁሉ የቤት መስተንግዶ እና የቤት መሰረተ ልማቶች በተሟላላቸው እጅግ የተሻለ ፣ ንፁህ ፣ መሠረታዊ መገልገያዎች የተሟሉላቸው ቤቶች የተስተናገድ ሲሆን፤ ለመኖር ምቹ አካባቢ ያገኙ ስለመሆኑ እና አንዳንድ ሳይቶች ላይ የመንገድ ደረጃውን ለማሻሻል ግንባታ እየተካሄደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦ ካቢኔው በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ውሳኔ አስተላልፏል።

ሌሎች ሳይት ላይ አስፈልጊው መሰረተ ልማት ተጠናቆ ነዋሪዎች የየእለት ኑሯቸውን እንዲቀጥሉ ተደርጓል ፤የማህበራዊ ኑሯቸው ሳይበታተን እድር ፤ ማህበር እና አብሮነታቸው የመሰረቱት ማህበራዊ መስተጋብር እንደተጠበቀ መስተናገዳቸው ን አቃቂ ፤ገላን ጉራ ፤ፉሪ ሃና ፤አራብሳ አምስት እና ስድስት አያት ሶስት፤ ላፍቶ ሃይሌ ጋርመንት እና ለሚኩራ አጠገብ የተሰሩት ሎኮስት ፤አየርጤና ቂርቆስ ለገሃር አካባቢ ፤አራዳ ሰባ ደረጃ አካባቢ በማሃል ከተማ የተገነቡ ቤቶች ላይም የተስተናገዳቸውን እና አፈፃፀሙም ጥሩ መሆኑን ካቢኔው ገምግሟል።

የመሠረተ ልማት ቅንጅት አካላት ከከተማ እስከ ፌደራል ተቋማት የነበራቸው ተሳትፎ በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ካቢኔው በጥንካሬ ገምግሟል ።

በተጨማሪም መሬት እና ካሳ ምትክ እስካሁን ድረስ ብቻ ከ4.6ቢሊየን በላይ መከፈሉን የሁለት አመት የቤት ኪራይ መከፈሉን እና ቀሪ ተነዴዎችም ቅድመ ዝግጅት ሂደት ካቢኔው በጥንካሬ ገምግሟል ። በሌላ በኩል በኰሙኒኬሽን ሥራዎችን በደንብ ደጋግሞ ለሕዝብ መረጃን ማድረስ ላይ ከዚህ በላይ ማድረስ እና ተደጋጋሚ የሚዲያ ሽፋን ያላቸው የመረጃ ስርጭት ለህብረተሰቡ መድረስ እንዳለበት ካቢኔው አሳስቧል። መረጃን የሚያዛቡ እና ሀገር እንዳትለማ ውዝንብር በሚፈጥሩ የተለያዩ ዝንባሌዎች የሚያሳዩ የመረጃ ምንጮችን እና አካላት ላይ ህጋዊ ርምጃ በመወሰድ እንዳለበት በአፅንኦት ኣንስተዋል ።

በ2ኛው ዙር ኮሪደር ልማት ስራ 2879 ሄክታር ስፋት ፤ 135ኪሎ ሜትር የኮሪደር ርዝመት ያለው ሲሆን ፤ 240ኪሎ ሜ የአስፋልት መንገድ፣ 237 የእግረኛ መንገድ ፣ 32 የህፃናት መጫዎች ቦታዎች ፣ 79 የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች ፣ 114የታክሲ እና አውቶቡስ መጫኛ እና ማውረጃ ፣ 58 የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ ቦታዎች፣ 368 ሄክታር አረንጋዴ ልማት ሽፋን ያላቸው ቦታዎች፣ የ 111 ኪ.ሜ ሳይክል መንገድ ፣ 17 የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች፣ 106 የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች፣ 121 ኪ.ሜ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ፣ 182 ኪ.ሜ ድሬኔጅ መውረጃ መስመር ፣ 50 የተሸርካሪና እግረኛ መተላለፊያ ፣ 75 ኪ .ሜ ሪቴይኒንግ (የድጋፍ ግንብ) ስራዎችን የሚያካትት ነው ::

ይህንኑ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ክትትል ማሳደግ፤ ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ የተተገበሩ የ አንደኛ ዙር ኮርድር ልማት ልምዶች ተቀምረው ለ2ተኛው ዙር በተሻለ ብቃት መስራት እንደሚያስፈልግ ፤ ቅንጅታዊ አሰራርም በተጠናከረ መልኩት አሳድጎ በጥንካሬ አሁን ካለው በላይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ካቢኔው አሳስቧል።

(ከፅቤ)


ቋሚ ኮሚቴው በህንጻ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያየ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሰረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የህንጻ ረቂቅ አዋጅ ማሻሻያ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል።

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ዶ/ር እሸቱ ተመስገን ህንፃዎች ሲሰሩ ለዲዛይኖች ጊዜ ሰጥቶ በአግባቡ በመስራት የግንባታ ጊዜን የተቀላጠፈ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። የአዋጭነት ጥናትና የአካባቢና ማህበራዊ ተጽኖዎችም  በአግባቡ   መታየት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ምክትል ሰብሳቢው ከመድረኩ ጥሩ ግብአት መገኘቱን ገልጸው፤ አዋጁ ረጅም ጊዜ የሚያገለግል እንዲሆን ተጨማሪ አስተያየቶችን በጽሁፍ ማድረስ እንደሚቻል ጠቁመዋል ። ዘርፉን ለማሳደግ የሙያ ማህበራት ተጠናክረው በጋራ መስራት እንዳለባቸውም ጠቁመዋል።

በውይይቱም የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ የአዋጁ ማሻሻያ ጥናት ላይ የተመሰረተ እና ዘርፉ የደረሰበትን ደረጃ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። 

የከተሞች ስታንዳርድ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መገባቱን ገልጸው፤ የሙያ ማህበራት በጋራ ሆነው ጠንካራ አቅም መፍጠር ቢችሉ የተሻለ መሆኑን ጠቁመዋል ።

በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የኮንስትራክሽንና መሰረተ ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ መዲና አህመድ  አዋጁን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ አዋጁ የህዝብን ደህንነት ለመጠበቅ እና ለአካል ጉዳተኞችና ለሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች የህንጻ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ዝቅተኛውን ደረጃ ለመወሰን አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል
በነባሩ ህግ በአፈጻጸም የተለዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ፣ የአካል ጉዳተኞች ተደራሽነትን፣የግንባታ ጥራትና የሀብት ብክነት ችግሮች ለመቅረፍ የሚያስችል  ግልጽና ለአተገባበር ምቹ የሆነ የአሰራር ስርአት መዘርጋት ተገቢ ሆኖ መገኘቱን  ተናግረዋል ። 

ማንኛውም ሰው አዲስ ግንባታ ለማከናወን፣ ነባር ህንፃ ለማሻሻል ፣ለማስፋፋት ወይም ለማፍረስ እንዲሁም የአገልግሎት ለውጥ ለማድረግ በቅድሚያ ተገቢውን የግንባታ ፈቃድ ማግኘት እንዳለበት እና ማንኛውም ሰው የህዝብ መገልገያ የሆኑ የተጠናቀቁ ህንፃዎች አገልግሎት ላይ ከመዋላቸው በፊት የህንጻ መጠቀሚያ ፈቃድ ማግኘት እንዳለበት ገልጸዋል።

በውይይቱ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላት አዋጁን በሚመለከት አስተያየትና ጥያቄዎችን አንስተዋል። የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ምላሽ ሰጥተዋል ።

በውይይቱ ከክልል እና ከከተማ አስተዳደር የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ የመጡ የስራ ሃላፊዎች ፣ ከኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፣ ቲንክታ
አካላት ተገኝተዋል።

(ከመልሚ)


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ኢትዮ ኮን ህዳር 2፤ 2017


👉 የዛሬ ምሽት ህዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም ኢትዮ ኮን ሳምንታዊ ፕሮግራሞቻችን

🗣ወቅታዊ ፕሮግራም

🔷 የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም  በኢንተር ላግዠሪ ተካሂዷል።

ይህን በተመለከተ ወደ እናንተ የምናደርሰው ፕሮግራም ይኖረናል።

🏗 የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የሚያቀርበው ልዩ ዝግጅት የፕሮግራማችን አንድ  አካል ነው።

✍️📞☎️የምታነሱት ሀሳብ አስተያየትና ጥያቄ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ በዚሁ በቴሌግራም ገፃችን ላይ አድርሱን፡፡

🥍📻🕰 ምርጫችሁ አድርጋችሁ ምሽት
ከ2፡30 — 3፡30 ሰዓት በአሀዱ ሬድዮ 94.3 ላይ ከቀጥታ ስርጭት ፕሮግራማችን ጋር ይሁን!
                                          


Slump Test ....very important ✅✅✅✅


🔵 የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የመሠረተ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ አቶ የትምጌታ አስራት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር ባካሄደው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ካደረጉት የመክፈቻ ንግግር መካከል እነዚህን ነጥቦች አንሰተዋል፣

🔷የኮንስትራክሽን ዘርፋ ከአጠቃላይ የስራ ዕድል ፈጠራ ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። በአሁኑ ወቅት በየዓመቱ ከ150,000 በላይ ባለሙያዎች ወደ ዘርፋ እንደሚንቀሳቀስ የተለያዩ መረጃዎች ያሳያሉ።

🔷ባለፋት 26 ዓመታት በተሰሩ ስራዎች የአገር በቀል ተቋራጮች (የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ጨምሮ ) ከፌደራል የመንገድ ፕሮጀክቶች በገንዘብ 54 በመቶ በፕሮጀክት ብዛት ደግሞ 79 በመቶ አካባቢ የሚሆነውን ኮንትራት በመፈረም እየተሳተፈ ነው። ይህ እውነታ ከብዙዎቹ የአፋሪካ ሀገራት ጋር ሲነፃፀር የተሻለ ነው።


🔷 የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን ዛሬ በአሁኑ ሰዓት ጥቅምት  30 ቀን 2017 ዓ.ም
  በኢንተር ላግዠሪ (የቀድሞው ኢንተር ኮንቲነታል) ሆቴል በመካሄድ ላይ ይገኛል

🔵 የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የመሠረተ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ አቶ የትምጌታ አስራት ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።


ዛሬ ከሲሚንቶ አምራች ኩባንያ ባለቤቶች እና የስራ ሃላፊዎች ጋር በሲሚንቶ ግብይት የአሰራር ስርዓት ላይ ውይይት ማድረጋቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

በተለያዩ ውጪያዊና ውስጣዊ ምክንያቶች በበቂ ደረጃ ያለማምረት የምርት ፍላጎትና አቅርቦት ላይ ከፍተኛ መዛነፍ መፍጠሩንና የሲሚንቶ ግብይት በፋብሪካ እና በቸርቻሪዎች መካከል የሚሸጥበት የግብይት ሰንሰለት ለተጋነነ ዋጋ ጭማሪ በር የሚከፍቱ አሰራሮችን አስተካክለው በበቂ አምርተው ባጠረ የግብይት ሰንሰለት በሚሸጡበት አግባብ ላይ ግልፅ አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን ተናግረዋል።


**ማስታወቂያ *

🫵 ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር አባላት በሙሉ!

🔷 የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን ጥቅምት 23 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚያካሂድ ቀደም ብሎ የተገለፀላችሁ መሆኑ ይታወሳል፡፡

🔷ይሁንና የምርጫ አመቻች ኮሚቴ አባላቱ በዚሁ ዕለት ቀደም ብለው በተያዙና  በተለያዩ ፕሮግራሞቻቸው ምክንያት መገኘት የማይችሉ መሆኑን በመረዳታችን ጉባዔውን በአንድ ሣምንት ወደፊት ለመግፋት መገደዳችንን  በታላቅ አክብሮትና ትህትና ጋር ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

- ጉባኤው የሚካሄደው ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም

- ቦታው ኢንተር ላግዠሪ (የቀድሞው ኢንተር ኮንቲነታል) ሆቴል

- ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ መሆኑን እናስታውቃለን።

🔷የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር ዳይሬክተሮች ቦርድ


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ኢትዮ ኮን ጥቅምት 25፤ 2017


👉 የዛሬ ምሽት ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ኢትዮ ኮን ሳምንታዊ ፕሮግራሞቻችን

🗣ወቅታዊ ፕሮግራም

🔵የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በተገኙበት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም አካሂዷል።

በዚሁ ስብሰባ ላይ ከመሰረተ ልማት፣ ከኮሪደር ልማትና ሌሎች የተያያዙ ጉዳዮች ጋር ከምክር ቤት አባላት ለቀረበላቸውን ጥያቄ የሰጡትን ምላሽ በዛሬ ወቅታዊ ፕሮግራማችን እንመለከተዋለን።

🏗 የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የሚያቀርበው ልዩ ዝግጅት የፕሮግራማችን አንድ  አካል ነው።

✍️📞☎️የምታነሱት ሀሳብ አስተያየትና ጥያቄ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ በዚሁ በቴሌግራም ገፃችን ላይ አድርሱን፡፡

🥍📻🕰 ምርጫችሁ አድርጋችሁ ምሽት
ከ2፡30 — 3፡30 ሰዓት በአሀዱ ሬድዮ 94.3 ላይ ከቀጥታ ስርጭት ፕሮግራማችን ጋር ይሁን!
                                          


ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ወደ ሀገር ከሚያስገባቸው 330 ገልባጭና የጭነት ከባድ ተሸከርካሪዎች 44ቱ ለሚ ከተማ ደረሱ።

ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ በሦስተኛ ዙር 44 ገልባጭ ከባድ ተሸከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባቱ ተገልጿል፡፡

ኩባንያው ወደሀገር ውስጥ እያስገባቸው ከሚገኙት 330 ገልባጭና የጭነት ከባድ ተሸከርካሪዎች መካከል በመጀመሪያ ዙር 36፣ በሁለተኛው ዙር 30 ተሸከርካሪዎችን በሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ መግባታቸው ይታወቃል፡፡

በሦስተኛ ዙር ደግሞ 44 ተጨማሪ ገልባጭ ከባድ ተሸከርካሪዎች ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡

እነዚህ ከባድ ተሽከርካሪዎች የሲሚንቶ ምርት ግብዓት የሆነውን ማዕድን ከማምረቻ ጣቢያው ማከማቻ ቦታ የሚያጓጉዙ እጅግ ግዙፍና ዘመናዊ የሆኑ ገልባጭ ከባድ ተሸከርካሪዎች መሆናቸውን ከፋብሪካው ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ከጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ምርቱን ለገበያ ማቅረብ መጀመሩን ማስታወቁ ይታወሳል ሲል አሚኮ ዘግቧል።


የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የኮንስትራክሽን ግብዓት ማምረቻ ማዕከልና ሁለት ባለ 13 ወለል ህንጻዎችን አስመረቀ

በ1 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባው የኮርፖሬሽኑ የኮንስትራክሽን ግብዓት ማምረቻ ማዕከል ጥራት ያለው ብሎኬት እና የኮንክሪት ውህድ በማምረት የራሱን የኮንክሪት ፍላጎት ከማሟላት ባሻገር በዘርፉ ያለውን የግብዓት እጥረት ይሞላልም ተብሎ ይጠበቃል።

የኮንስትራክሽን ግብዓት ማምረቻ ማዕከሉ በአመት 202ሺ 752 ሜትር ኩብ የኮንክሪት ውህድና እና ባለ 20 ሴንቲ ሜትር ብሎኬት በቀን 25ሺ፣ ባለ 10 ሴንቲ ሜትር በቀን እስከ 50ሺ እንዲሁም ባለ 15 ሴንቲ ሜትር በቀን 37ሺ ብሎኬቶችን የማምረት አቅም አለው።

በ1ሺ 263 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈውና ባለ 13 ወለል ሆኖ የተገነባው የኮከበ ጽባህ ሳይት ህንጻ ሌላው ኮርፖሬሽኑ አስገንብቶ ያስመረቀው ፕሮጀክት ሲሆን ከባለ ሁለት እስከ ባለ አራት መኝታ ቤት 60 የሚደርሱ ዘመናዊ ቤቶች ያሉት ነው።

ሌላው በ1ሺ 541 ካሬሜትር ቦታ ላይ ያረፈውና ከባለ 1 እስከ ባለ አምስት መኝታ ቤቶች ያሏቸው መኖሪያ ቤቶች እና የንግድ ሱቆችን አካቶ የተገነባው ባለ 13 ወለሉ የምስራቅ አጠቃላይ ሳይትም ኮርፖሬሽኑ ገንብቶ ያስመረቀው ፕሮጀክት ነው።

20 last posts shown.