👉
ስለ Athematic Error🚧በጨረታ ግምገማ ሂደት አንድ ተቋራጭ ባስገባው ጨረታ ሰነድ ላይ የሞላው እያንዳንዱ የሥራ ልኬት (quantities) በተቀመጠላቸውነጠላ ዋጋ (Unit price/rate) እየተባዙ በገምጋሚ ኮሚቴው የሚረጋገጡበት ሂደት
Athematic checking ይባላል። የዚህ ሂደት ዋናው ዓላማ አሸናፊው ተቋራጭ ያስገባቸው ነጠላ ዋጋዎች እና ብዜቶች ትክክል መሆናቸውን ለማረጋገጥ ሲሆን ስህተቶች (Errors) ሊገኝበት ይችላል።
🌟እንደ መነሻ ኬዝ ከላይ የተጠየቀውን ምሳሌ እናንሳ፦ አንድ ተቋራጭ የጨረታ ሰነዱ ሲከፈት ጠቅላላ ድምር 50,000,000 ብር ያስገባ ሲሆን ሁለተኛ የወጣው ተጫራች 50,050,000 ብር አስገብቷል።
ሃምሳ ሚሊዮን (50,000,000 ብር ) ያስገባው ተጫራች ዝቅተኛ ዋጋ (List Price) መሰረት አድርጎ
Athematic checking ላይ ችግር ካልተገኘበት አሸናፊ እንደሆነ ይገለጻል።
ተቋራጩ በ'
Athematic checking ሂደት ውስጥ ለ112 ኪዩቢክ ሜትር አርማታ በአንድ ኪዩቢክ ሜትር ልኬትነጠላ ዋጋ በ8,000 ብር ሂሳብ ጠቅላላ የአርማታ ዋጋ 896,000 ብር አስገብቷል ነገር ግን ወረቀቱ ላይ የመዘገበው ነጠላ ዋጋ
8000 (ስምንት ሺህ) ሳይሆን አንድ ዜሮ ጨምሮ
80000 (ሰማንያ ሺህ) ነው። '
Athematic checking የ112 ኪዩቢክ ሜትር አርማታ ዋጋ ከ896,000 ብር ወደ 8,960,000 ብር ከፍ ያለ ሲሆን ከስምንት ሚልዮን ብር በላይ ልዩነት አመጣ።
ነገር ግን ይህ ተጫራች ሁለተኛ የወጣውን ተጫራች በሃምሳ ሺህ (50,000) ብር ልዩነት አሸንፎ ነበር። በዚህ ሂደት ሊታዩ የሚገባቸው የሕግ አግባቦች፦
⏺የኢትዮጵያ የመንግስት ግዢ ባለሥልጣን የነበረው (Public Procurement Agency - PPA) ለተለያዩ የግዢ ሁኔታዎች መመሪያ ያጸደቀ ሲሆን ለኮንስትራክሽን ሥራዎች በሚያገለግለው መመሪያ Instructions to Bidders (ITB) አንቀጽ 33.1. (a) ላይ "
በአንድ ልኬት ላይ የተቀመጠ ነጠላ ዋጋ እና በሥራ መጠንና ነጠላ ዋጋ ብዜት በሚገኘው አጠቃላይ ዋጋ መካከል ልዩነት ከተፈጠረ በሕዝብ (በፕሮጀክት ባለቤቱ ወይም ተቀካዩ) አካል አስተያየት ግልጽ ካልሆነ በቀር የነጠላ ዋጋ (unite price) እንደገዢ ተቆጥሮ በብዜት የተገኘው አጠቃላይ ዋጋ (sub total) ይስተካከላል ወይም ይታረማል።
ነገር ግን የሕዝብ አካሉ (አሠሪው ወይም ሕጋዊ ተቀካይ ባለሙያዎቹ) የነጠላ ዋጋ ሲጻፍ የአስርዮሽ ነጥብ የተሳሳተ አቀማመጥ (misplacement of the decimal point) እንዳለ ካሰበ ወይም ካመነበት፣ በዚህ ሁኔታ የተጠቀሰው የብዜቱ አጠቃላይ ዋጋ (total price) ገዢ ሆኖ ለአንድ ሥራ ልኬት የተቀመጠው ነጠላ ዋጋ (unit price) ይስተካከላል ወይም ይታረማል" የሚል ግልጽ ሀሳብ አስቀምጧል።
በመሆኑም ተቋራጩ ያስገባው ዋጋ የአስርዮሽ ነጥብ የተሳሳተ አቀማመጥ (misplacement of the decimal point) ኖሮበት ብዜቱ ግን በአግባቡ ከተቀመጠ እና የጨረታ ኮሚቴው ስህተት መሆኑን ካለው ነበራዊ የግንባታ ሥራዎች ነጠላ ዋጋ አንጻር ተቀራራቢ የሚሆነው የአሥርዮሽ ማስተካከያ ሲሆን እንደሆነ ካረጋገጠ ነጠላ ዋጋውን ትቶ ብዜቱን እንዲይዝና ነጠላ ዋጋው እንዲስተካከል ማድረግ አለበት።
▶️ከላይ በተጠቀሰው አንቀጽ መሰረት፦
🖱
[1ኛ]፦ በሀገራችን የትኛውም ቦታ የአንድ ኪዩቢክ ሜትር አርማታ ሙሌት ዋጋ ከ6,000 እስከ 15,000 ብር ስለሆነ 8,000 ብር ተቀባይነት ይኖረዋል እንጂ "ተቋራጩ ለአንድ ኪዩቢክ ሜትር ዋጋ ሰማንያ ሺህ (80,000 ብር) አስገብቷል ብሎ መጣል ሙያዊ እምነት ያልታከለበት ወይም አውቆ እንደመካድ የሚቆጠር ነው።
🖱
[2ኛ]፦ ተጫራቹ ለ112 ኪዩቢክ ሜትር ያስገባው ብዜት ዋጋ 896,000 ብር መሆኑ የአንድ ኪዩቢክ ሜትር አርማታ ሙሌት ስምንት ሺህ (8000) ብር መሆኑ ስለሚጠቁም ለሙያው ቅርብ የሆነ ወይም ምክንያታዊ የሆነ ውሳኔ እንዲወሰን መደረግ ይኖርበታል ማለት ነው።
☄በዚሁ አንቀጽ ሥር ንዑስ አንቀጽ (b) ላይ "በእያንዳንዱ የሥራ ክፍሎች ሥር ያለው ንዑስ ድምሮች እና ጠቅላላ ድምር መካከል የመጨመር ወይም የመቀነስ ልዩነት ከተስተዋለ በእያንዳንዱ ሥራዎች ሥር ያለው ንዑስ ድምር ገዢ ይሆንና ጠቅላላ ድምሩ ይስተካከላል።
⏺በንዑስ አንቀጽ (c) ደግሞ በፊደል የተጻፈው እና በአሐዝ የተቀመጠው ልዩነት ካለው በፊደል የተቀመጠው ዋጋ ገዢ ይሆናል። ነገር ግን ይህ በፊደል የተቀመጠው ዋጋ ከ'Athematic Error ጋር የሚገናኝ ከሆነ በአሐዝ የተቀመጠው ዋጋ ገዢ ይሆናል በማለት አስቀምጧል።
https://t.me/ethioengineers1