Ethiopian Lawyers Corner


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Law


የቻናሉ አላማ ህግ እና ህግ ነክ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የተሸለ እዉቀትን ለማዳበር የተከፈተ ቻናል እና ግሩፕ ሲሆን፣ የሀገር ዉስጥ እና አለም አቀፍ የህግ መፅሀፍትንና የተለያዩ የህግ የምርምር ስራዎችን ያገኙበታል።
Ethiopia

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Law
Statistics
Posts filter


አንድ ድርጅት ባልተከፋፈለ ትርፍ ላይ ግብር እንዲከፍል የማይጠየቀው ድርጅቱ በአንድ የሂሳብ ጊዜ(የበጀት ዓመት) ውስጥ የተገኘውን ያልተከፋፈለ ትርፍ የሂሳብ ጊዜው በተጠናቀቀ በ12 ወራት ጊዜ ውስጥ የአባላቱን የአክስዮን ድርሻ መጠን እና የድርጅቱን ካፒታል በተገኘው ትርፍ መጠን ያሳደገ እንደሆነ ነው፡፡
ድርጅቱ ያልተከፋፈለ ትርፍ የሌለው መሆኑን የሚያስረዳው በአንድ የሂሳብ ጊዜ(የበጀት ዓመት) ውስጥ የተገኘው የተጣራ ትርፍ የባለአክስዮኖችን የአክስዮን ድርሻ መጠን እና የድርጅቱን ካፒታል ለማሳደግ የዋለ መሆኑን በሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንሲ የፀደቀ ቃለ-ጉባኤ እና ከንግድ ሚኒስቴር ወይም አግባብነት ካለው የክልል/የከተማ አስተዳደር ቢሮ የድርጅቱ ካፒታል ማደጉን የሚገልጽ ሰነድ በጣምራ በማቅረብ ነው በማለት የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡

https://t.me/ethiolawreview


አዲሱ ተግባራዊ የሚሆነው ውልና ማስረጃ ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚከፈል የአገልግሎት ክፍያን ለመወሰን በወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 543/2016 መሰረት የአገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ ደንብ
ከላይ ይመልከቱ

https://t.me/ethiolawreview


1002-2024.pdf
404.1Kb
Directive on monitoring, control, and investigation of civil society organization No. 1002/2024-ስለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ክትትል፣ ቁጥጥር እናምርመራ የወጣ መመሪያ ቁጥር 1002/2016

https://t.me/ethiolawreview


205206_የክልል_ፍርድ_ቤቶች_የውክልና_ስልጣን.pdf
1.1Mb
✅ የፌ/ጠ/ፍ/ሰ/ሰ/ችሎት በሰ/መ/ቁጥር 205206 (ያልታተመ) ላይ በሕገ-መንግሥቱ የክልል ፍርድ ቤቶች የፌዴራል ጉዳይን በውክልና እንዲመለከቱ የተሠጣቸው ሥልጣን መሠረቱ የፌደራል አወቃቀር በመሆኑ ሊነሳ የሚችለው በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 78/2 ላይ በግልፅ እንደተመለከተው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2/3ኛ ድምጽ ብቻ በመሆኑ ይህ በሕገ መንግስቱ የተሠጣቸውን የውክልና ሥልጣን በሕግ አግባብ እስካልተነሳ ድረስ ጉዳዮቹ ለፌደራል ፍርድ ቤት በቀጥታ ሊቀርቡ አይችሉም በማለት አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል።

✅ነገር ግን ችሎቱ ከላይ በተጠቀሰው መዝገብ ላይ የያዘውን አቋም በሌላ ውሳኔ በማሻሻል የፌደራል ፍ/ቤቶች በውክልና ስልጣን በክልል ፍርድ ቤቶች የሚታዩትን የፌደራል ጉዳዮች በቀጥታ ተቀብለው ሊያዩ የሚችሉበትን ሁኔታ አስቀምጧል።

✅የሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁጥር 219089 (በቅጽ 25 ላይ የታተመ) ላይ በሕገ-መንግሥቱ የክልል ፍርድ ቤቶች የፌዴራል ጉዳይን በውክልና እንዲመለከቱ የተሠጣቸው ሥልጣን በሕግ አግባብ እስካልተነሳ ድረስ ጉዳዮቹ ለፌደራል ፍርድ ቤት በቀጥታ ሊቀርቡ አይችሉም የሚለው የህግ ትርጉም ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው ጉዳዩን ለመመልከት ሥልጣን ያለዉ ክልል መደበኛ የዳኝነት አገልግሎት መስጠት በሚችልበት ሁኔታ ላይ ሲሆን ብቻ ስለሆነ የክልል ፍርድ ቤቶች በህግ በታወቀ ምክንያት በሕገ መንግስቱ የተሰጣቸውን የውክልና ሥልጣን መጠቀምና ለዜጎች ፍትህ መስጠት በማይችለበት ሁኔታ ላይ ሲሆኑ እና ጉዳዩም የፌዴራል ጉዳይ ሲሆን የሰዎችን ፍትህ የማግኘት መብት፣ እኩል የሕግ ጥበቃ የማግኘት መብት እና ሌሎች መብቶችን ለማስከበር የፌደራል ፍርድ ቤቶች በቀጥታ ጉዳዩን ተቀብለው የመዳኘት ሥልጣን አላቸው በማለት አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል

https://t.me/ethiolawreview


ቀለብ_የመስጠት_ግዴታን_አለመወጣት_ተጠያቂነት_የሚያስከትል_ስለመሆን_ያውቃሉ_.pdf
113.5Kb
ቀለብ የመስጠት ግዴታን አለመወጣት ያለውን የወንጀል ተጠያቂነት።

የቀለብ ገንዘብ መጠራቀም አይችልም፤ ቀለብ ተቀባዩ ለኑሮ አስፈላጊ መሆኑን የሚያሳይ ማረጋገጫ ካላቀረበ በስተቀር ቀለቡን መቀበል ካለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ሶስት ወራት ውስጥ ቀለቡን ያልተቀበለ ወይም ያልጠየቀ እንደሆነ የተጠራቀመውን ቀለብ መጠየቅ አይችልም፡፡

ቀለብ ተቀባይ የሆነ ሰው በቀለብ ሰጪው ላይ ወይም በቀለብ ሰጪው ወደላይ እና ወደታች በሚቆጠሩ ወላጆች ወይም ተወላጆች ወይም ባል ወይም ሚስት ህይወት ወይም ንብረት ላይ የወንጀል ተግባር የፈጸመ ወይም ለመፈጸም የሞከረ እንደሆነ ቀለብ የማግኘት መብቱን የሚያጣ
ይሆናል፡፡

በቂ ምክንያት በህግ መሰረት ሊሰጥ የሚገባውን ቀለብ ለባለመብቶቹ አልሰጥም ያለ ወይም መስጠትን ያስተጓጎለ የወንጀል ተጠያቂነት የሚኖርብት ሲሆን የግል አቤቱ ሲቀርብ ከስድስት ወር በማይበልጥ ቀላል እስራት ወይም በገንዘብ መቀጮ ሊቀጣ ይችላል።

https://t.me/ethiolawreview


📎የትራፊክ ደምብን በመጣስ በቸልተኝነት በሰው ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ እና የወንጀል ተጠያቂነት

➡️ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 59(2) ግልፅ ንባብ እንደምንረዳው በወንጀል ህጉ ላይ ያስቀጣል ተብሎ በግልፅ ካልተደነገገ በስተቀር በቸልተኝነት የሚፈፀም ማንኛውም ድርጊት በወንጀል አያስቀጣም። በመሆኑም አንድ በቸልተኝነት የተፈፀመ ድርጊት በወንጀል ሊያስጠይቅ የሚችለው በወንጀል ህጉ ልዩ ክፍል ውስጥ ድርጊቱ ወንጀል መሆኑ በግልፅ ተደንግጎ ሲገኝ ብቻ ነው። ሰለቸልተኝነት ይህን ካልን የትራፊክ ደምብን በመጣስ በቸልተኝነት በሰው ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ በወንጀል ያስጠይቃል ተብሎ በህጉ በግልጽ ተደንግጓል ወይስ አልተደነገገም የሚለውን እንመለከታለን።

➡️ የትራፊክ ደምብን በመጣስ በቸልተኝነት በሰው ንብረት ላይ ጉዳት በደረሰ ግዜ ጉዳቱን  ያደረሱ ሰዎች በወንጀል ሊጠየቁ ይገባል ወይስ አይገባም በሚለው ጉዳይ ላይ በህግ ባለሞያዎች መካከል ልዩነት የሚስተዋል ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘ ሊነሳ የሚችለው ድንጋጌ የወንጀል ህግ አንቀጽ 572 ስር የተመለከተው ነው።

➡️ አንዳንድ የህግ ባለሞያዎች የትራፊክ ደምብን በመጣስ በቸልተኝነት በሰው ንብረት ላይ ጉዳት ያደረሱ ሰዎች በወንጀል ህግ አንቀጽ 572(1) ስር ሊጠየቁ ይገባል ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ የወንጀል ህግ አንቀጽ 572 የሚደነግገው የትራፊክ ደምብን በመጣስ ሌሎችን ለ አደጋ ስለሚያጋልጡ ሰዎች እንጂ የትራፊክ ደምብን በመጣስ በቸልተኝነት በሰው ንብረት ላይ ጉዳት ስለሚያደርሱ ሰዎች አደለም ስለዚህ በደምብ መተላለፍ አንቀጽ 856  ሰር ካልሆነ በስተቀር የወንጀል ህግ አንቀጽ 572 ስር በወንጀል ሊጠየቁ አይገባም በማለት ይከራከራሉ።

➡️ የፌ/ጠ/ፍ/ቤ/ሰ/ሰ/ችሎት የትራፊክ ደምብን በመጣስ በቸልተኝነት በሰው ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ በወንጀል ህጉ ያስቀጣል ተብሎ በግልፅ አለተደነገገም። የወንጀል ህግ አንቀፅ 572 የተደነገገው የትራፊክ ደምብን በመጣስ የሰዎችን ህይወት፣ አካል ወይም ንብረት ለአደጋ የሚጋልጡትን ለመቅጣት እንጁ የትራፊክ ደምብን በመጣስ በሰው ንብረት ላይ በቸልተኝነት ጉዳት የሚያደርሱትን ለመቅጣት አይደለም በማለት በመ/ቁ/194880 ላይ አስገዳጅ ውሳኔ ሰጥቷል። እንዲሁም በመ/ቁ.200948 /ያልታተመ/ ለይም በተመሳሳይ መልኩ ውሳኔ ሰጥቷል።

➡️ ለምሳሌ (A) እግረኛ ነው ብንል ለእግረኞች ባልተፈቀደ በኩል መንገድ በሚያቋርጥበት ግዜ (B) ባልተገባ ፍጥነት እያሽከረከረ ስለነበረ (A) ላይ ጉዳት እንደይደርስ በማሰብ መሪውን ወደሌላ አቅጣጫ ለማዞር በሚሞክርበት ሰዓት መኪናው ከቁጥጥር ውጪ ስለሆነበት (C) እያሽከረከረ ከነበረው መኪና ጋር ይጋጭና ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል።

በፌ/ጠ/ፍ/ቤ/ሰ/ሰ/ችሎት ውሳኔ መሠረት ከላይ ባነሳነው ምሳሌ ላይ የወንጀል ህግ አንቀፅ 572 የተፈፃሚነት ወሰን ሲታይ (C) እያሽከረከረ በነበረው መኪና ላይ በቸልተኝነት ጉዳት ያደረሰውን (B)'ን ለመቅጣት የተደነገገ ሳይሆን ለእግረኞች ባልተፈቀደ ቦታ ላይ ሲያቋርጥ B እና C ለ አደጋ እንዲጋለጡና ግጭት እንዲፈጥሩ ያደረገው (A)'ን ለመቅጣት ነው።

➡️ እንደሚታወቀው የፌ/ጠ/ፍ/ቤ/ሰ/ሰ/ችሎት የሚሰጣቸው ውሳኔዎች በማንኛውም የሀገሪቱ ፍርድ ቤት አስገዳጅነታቸው የማያጠያይቅ ቢሆንም ችሎቱ የወንጀል ህግ አንቀጽ 572 ን የተረጎመበት አግባብ ህግ አውጪው ሊደስበት ያሰበውን አላማ የሚያሳካ መስሎ በኛ በኩል አልታየንም። አንዳንድ የህግ አካላትም ይህንን የሰበር ውሳኔ የተቀበሉት አይመስልም። ለምሳሌ ይህ የሰበር ውሳኔ (ቁ.194880) ታትሞ ከወጣ በኋላ የኦሮሚያ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ቢሮ የትራፊክ ደምብን በመተላለፍ በቸልተኝነት በሰው ንብረት ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሰዎች ላይ የወንጀል ህግ አንቀፅ 572 ስር ክስ እንዲመሠርቱ በስሩ ላሉት ዐቃቤ ህጎች መመርያ ሰጥቷል።

➡️ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ማብራራው (ሐተታ_ዘምክንያት) ላይ የወንጀል ህግ አንቀጽ 572 የተቀረፀበት ዋና ምክንያት እንደሚከተለው ሰፍሯል

"ድንጋጌው ከዚህ በፊት በነበረው የወንጀል ህግ ያልነበረ አዲስ ድንጋጌ ሲሆን፣ ብዙን ግዜ ተሽከርካሪ በሚንቀሳቀስባቸው መንገዶች ላይ እግረኞች ግራ ቀኙን ሳያዩ ሲያቋርጡ ወይም ትክክለኛ መስመራቸውን ትተው ሲጓዙ የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ ከመግታትም በላይ ተሽከርካሪዎች እርስ በእርስ ሊጋጩ ወይም በዕግረኞች ላይ አደጋ ሊያደርሱ የሚችሉበት ሁኔታ ይከሰታል። በሌላ በኩል ተሽከርካሪዎች በትራፊክ ደምቦች ላይ የተሰጠውን ልዩ ልዩ ምልክት በመጣስ እና ትክክለኛ መስመራቸውን ባለመያዝ አንዳንድ ግዜም በግረኛ መንገድ ላይ በመውጣት በሰው ሕይወት ፣ አካል ወይም ንብረት ላይ ጉዳት ለማስከተል የሚችሉበት ሁኔታ ሲፈጠር ይታያል። ይህ አንቀፅ የተቀረፀው የዚህ አይነቱን ድርጊት ለመከላከል ነው።"

➡️ ከማብራሪያው የምንረዳው ድንጋጌው በ አድስ መልኩ የተጨመረበት ዋናው ምክንያ የትራፊክ አደጋ አስከፊ እየሆነ በመምጣቱ እግረኞችም ሆኑ አሽከርካሪዎች በሰው ህይወት፣ አካል ወይም ንብረት ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ ለመከላከል ሲሆን ጉዳት ደርሶ ቢገኝ ደግሞ አጥፊዎችን መቅጣት የህግ አውጪው ሀሳብ መሆኑን ይጠቁማል።

➡️ ስለዚህ በድንጋጌው ላይ "የትራፊክ ደምብን በመጣስ ለአደጋ ማጋለጥ " የሚለው ህግ አውጪው ሊደርስበት ካሰበው አላማ ጋር  በሚጣጣም መልኩ መተርጎም ይኖርበታል፣ በተለይ የትራፊክ አደጋ ከቀን ወደ ቀን በሰው ህይወት, አካል እና ንብረት ላይ እያደረሰ ያለው ጉዳት አስከፊነት እየጨመረ በመምጣቱ ድንጋጌው ይህንን አደጋ መከላከል በሚያስችል መልኩ ስራ ላይ መዋል ይኖርበታል።

➡️ በመሆኑም የወንጀል ሕግ አንቀፅ 572 ላይ "የትራፊክ ደምብን በመጣስ የሰውን ሕይወት ፣ አካል ወይም ንብረት ለአደጋ ማጋለጥ" በሚል የተገለፀው በቸልተኛነት የትራፊክ ደንብን በመጣስ በሌላ ሰው ንብረት ላይ ጉዳት የሚያደርሱትን ጭምር ለመቅጣት የተደነገገ አንቀፅ ነው ባይ ነን።

➡️ ነገር ግን የፌ/ጠ/ፍ/ቤ/ሰ/ሰ/ችሎት በመ/ቁ.194880 እና 200948 ላይ የሰጠው ውሳኔ በሌላ ውሳኔ እስከሚሻር ድረስ አስገዳጅ መሆኑ የማያጠያይቅ ጉዳይ ነው።


https://t.me/ethiolawreview
href='' rel='nofollow'>


235844 qabeenya dhunfaa dhirsaa fi nitii.pdf
663.1Kb
Murtii DhIMMWF Lakk.Galmee 235844 ta’e irratti gaafa Onkololeessa 06 Bara 2016 kennamee:- Maqaan abbaa qabeenyumnaa maqaa Abbaa manaa fi Haadha manaatiin  galmaahun qoftii qabeenya sana qabeenya waliinii isaani kan hin taasisnee ta'u.
Maqaan abbaa qabeenyummaa qabeenya hin sochonee(mana jireenyaa) maqaa Abbaa manaa fi Haadha manaatiin galmaahee kan jiru ta'uus isaan keessaa tokko qabeenyi ykn manni kun kan dhunfaa isaa ta'u hubachiisu yoo danandahe qabeenyi ykn manni kun qabeenya waliinii isaani otoo hin taane kan dhunfaa isaa dha.
ሰ-መ-ቁ 235844 ጥቅምት 06 ቀን 2016 ዓ.ም
የማይንቀሳቀስ ንብረት (መኖሪያ ቤት) ስመ ሀብቱ የተመዘገበው በባልና ሚስት ስም ቢሆንም አንደኛው ተጋቢ ንብረቱ የግሉ መሆኑን ማስረዳት ከቻለ ንብረቱ የግል እንጂ የጋራ ሀብት አይደለም። ስመ ሀብቱ በተጋቢዎቹ ስም መመዝገቡ ብቻውን በትዳር ውስጥ የተፈራ የጋራ ንብረት አያደርገውም።

https://t.me/ethiolawreview


ለሕዝብ_ጥቅም_ሲባል_የመሬት_ይዞታ_የሚለቀቅበትን፣_ካሣ_የሚከፈ_ሺዎች_ጣውን_አዋጅ_ቁጥር_11612011ን.pdf
587.5Kb
📎ሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትን፣ ካሣ የሚከፈልበት እና
ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ቁጥር
1161/2011ን ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ / አማርኛ/ እንግሊዝኛ/ ማብራሪያ

📎 Dantaa Olaanaa ummataaf qabiyyee lafaa kan ittiin gadi lakkifamu, Beenyaan itti kanfalamu fi haala Buqqaatoota deebisanii dhaabuu murteessuuf bahe Labsii lakk 1161/2011 fooyyeessuuf wixinee seeraa dhiyaate.

https://t.me/ethiolawreview


378_የኢትዮጵያ_የጤና_መድህን_ኤጀንሲ_የጤና_መድህን_ስርዓት_የአፈጻጸም_መመሪያ_ቁጥር_378_2013.pdf
252.3Kb
የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ መመሪያ ቁጥር 378/2013
የማህበራዊ ጤና መድህንን ለመተግበር የወጣ መመሪያ

https://t.me/ethiolawreview


244928.pdf
877.6Kb
የሰ.መ.ቁ 244928

ሕዳር 27 ቀን 2016 ዓ.ም


 
የተሻሻለው የፌዴራል የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 27 በባሕል ሥርዓት የሚፈጸም ጋብቻ እንደየአካባቢው ሁኔታ የሚፈጸም መሆኑን ከመደንገግ ባለፈ በባሕል ሥርዓት የሚፈጸም ጋብቻን ለማስረዳት በአራት እማኞች ፊት መፈረም እንዳለበት እንደመመዘኛ አድርጎ ያላስቀመጠ ስለመሆኑ፡፡

Bu'uura Seera Maatii Feederaalaa Fooyya'e Kwt 27'n Gaa'elli bu'uura sirna aadaatiin gaggeeffamu akkaataadhuma seera naannawaa sanaan kan gaggeeffamu ta'uu malee dirqama ragaawwan afur bakka jiranitti akka raawwatuu fi mallattaa'uu qabu kan dirqisiisu miti.

https://t.me/ethiolawreview


235374.pdf
940.3Kb
Murtii DhIMMWF Lakk.Galmee 235374  ta'e irratti gaafa guyyaa 29/04/2016 kennamee.
“..Kireessaan tokko dirqama waliigalteen kiraa manaa akka haaromfamuuf akeekkachisa kireeffataaf kennuu isaa otoo hin bahatiin manicha ‘koree' tiin humnaan gadhisiisuuf akeekkachiisa kireeffataatti bareessuu isaa bu'uura SHH keewwata 1149(1) tiin gocha jeequmsaa dha…”

“…አከራይ የኪራይ ዉል እንዲታደስ ለተከራይ ማስጠንቀቂያ የመስጠት ኃላፊነቱን ሳይወጣ ቤቱን በግብረ ኃይል በኃይል ለማስለቀቅ ለተከራይ ማስጠንቀቂያ መጻፉ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1149(1) መሰረት የሁከት ተግባር ስለመሆኑ።

https://t.me/ethiolawreview


990-2024.pdf
825.5Kb
መመሪያ ቁጥር ፱፻፺/፪ሺ፲፮ 
የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግመታ መመሪያ
Directive No 990/2024 
Educational  Credentials  Authentication and Equivalency Directive

https://t.me/ethiolawreview


220008.pdf
674.4Kb
Murtii DhIMMWF Lakk.Galmee 220008 ta’e irratti gaafa 26/11/2014 kennamee (Murtii Hin Maxxanfamne).
Adeemsa falmii dhimma yakkaa keessatti namni yakkaan himatamee jiru tokko ragaan Abbaa Alangaa dhagahamee jalli murtii/ajajni akka ofirraa ittisu erga kennameen booda jalli murtii/ajajni akka ofirraa ittisu kennamee jiru sun dogoggora illee kan qabu yoo ta’e manni murtii dhimmicha ilaalaa jiru sun ragaa abbaa alaangaa irra deebidhaan madaaluun eejjennoo haarawaa qabachu kan hin dandeenye ta’u isaa ykn himatamaan ragaa ittisaa otoo hin dhiyeeffatiin murtii bilisaan gadi lakkisu kan hin dandenye ta’u isaa.

አንድ በወንጀል የተከሰሰ ሰው የዐቃቤ ህግ ማስረጃ ተሰምቶ የመከላከያ ማስረጃዉን እንዲያቀርብ ብይን/ትዕዛዝ ከተሰጠ በኋላ እንዲከላከል የተሰጠው ትዕዛዝ ስህተት ቢኖረዉም እንኳን ተከሳሹ ማስተባበያ ማስረጃ ባልቀረበበት ሁኔታ ከሱን በሚሰማው ፍርድ ቤት የዐቃቤ ህግ ማስረጃ በድጋሚ መዝኖ ቀደሞ ከተሰጠዉ ብይን/ትዕዛዝ የተለየ አቋም በመያዝ ተከሳሽን በነፃ እንዲሰናበት ሊወሰን የማይችል ስለመሆኑ፡፡
የሰ.መ.ቁ.220008 ሐምሌ 26/2014 ዓ.ም (ያልታተመ)

https://t.me/ethiolawreview


243549.pdf
684.4Kb
አቶ አብነት ገብረመስቀል ኦዳ እና ሼክ መሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ የሰ/መ/ቁጥር 243549

ጉዳዩ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሥራ አሥኪያጅ እንዲሻር የቀረበ ክርክርን የሚመለከት ነው፡፡የሰበር ቅሬታ የቀረበው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 299862 በየካቲት 22 ቀን 2015 ዓ.ም የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለማሳረም ነው፡፡ ክርክሩ በተጀመረበት በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁን አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡
ተጠሪ በነሐሴ 20 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት ክስ ቦሌ ታወርስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በአመልካች እና በተጠሪ የተቋቋመ ሲሆን አመልካች 40% ተጠሪ 60% የአክስዮን ድርሻ አላቸው፡፡ ይህ የንግድ ማህበር ከተቋቋመ ጀምሮ አመልካች ሥራ አሥኪያጅ በመሆን ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ 1ኛ. በማሕበሩ የመመስረቻ ጽሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የማህበሩን የማይንቀሳቀስ ንብረት ስም ለማዛወር በቅድሚያ የማህበርተኞችን ስምምነት ማግኘት የሚያስፈልግ ሆኖ እያለ አመልካች የማህበርተኞችን ስምምነት ሳያገኙ እና ከተጠሪ የተሰጣቸውን የውክልና ስልጣን ተጠቅመው በቂርቆስ ክፍል ከተማ የሚገኙ 3383 እና 1971 ካ.ሜ ይዞታዎች ላይ ለቦሌ ታወርስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የብር 120,000,000.00 የግንባታ ወጪ የወጣበትን በ2011 ዓ.ም እና በ2012 ዓ.ም ወደራሳቸው ስም አዛውረዋል፡፡ በዚህም በተጠሪ የአክስዮን ድርሻ ልክ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ 2ኛ. አመልካች በማህበሩ ስም ከባንክ ብር 452,000,000.00 ተበድረው ለግል ጥቅማቸው አውለዋል፡፡ 3ኛ. ማህበሩ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ያሉትን የማህበሩን ሰነዶች ሁሉ አመልካች ለጠተሪ ወይም ለወኪላቸው እንዲያስረክቡ ሲጠየቁ ሰነዶቹ ለተጠሪ እንዳይደርሱ ከቢሮ በማውጣት ወስደዋል፡፡


Dear Law Re -sit Examinees,
Please take your username from the office of Law School and be ready for tomorrow's Model Examination.
Regards!

#ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

ለድጋሚ (Re-exam) ተፈታኞች በሙሉ
የካቲት 6/2016 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለመፈተን በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ የ ድጋሚ (Re-exam) ተፈታኞች በሙሉ የመፈታኛ የይለፍቃል (Password) ከታችበተዘረዘሩት አማራጮች ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

1. በምዝገባ ወቅት በሞላችሁት email በኩል

2. https://exam.ethernet.edu.et ላይ በመግባት የከፈላችሁበትን Transaction Number በማስገባት እንዲሁም

3. ከተመደባብችሁብት የመፈተኛ ተቋም ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ
• ለመጀመሪያ ጊዜ የመዉጫ ፈተና የምትፈተኑ እጩ ተመራቂዎች የይለፍቃል (Password) የምታገኙት ከምትማሩበት ወይም ከተመደባብችሁበት የመፈተኛ ተቋም ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን።

• ሁሉም ተፈታኞች የሞዴል ፈተናን እስከ የካቲት 5/2016 ዓ.ም መውሰድ ይኖርባቸዋል።

ትምህርት ሚኒሰቴር !

የትምህርት ሚኒስቴርን መረጃዎች በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-

በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ

https://t.me/ethiolawreview


220008.pdf
674.4Kb
Murtii DhIMMWF Lakk.Galmee 220008 ta’e irratti gaafa 26/11/2014 kennamee (Murtii Hin Maxxanfamne).
Adeemsa falmii dhimma yakkaa keessatti namni yakkaan himatamee jiru tokko ragaan Abbaa Alangaa dhagahamee jalli murtii/ajajni akka ofirraa ittisu erga kennameen booda jalli murtii/ajajni akka ofirraa ittisu kennamee jiru sun dogoggora illee kan qabu yoo ta’e manni murtii dhimmicha ilaalaa jiru sun ragaa abbaa alaangaa irra deebidhaan madaaluun eejjennoo haarawaa qabachu kan hin dandeenye ta’u isaa ykn himatamaan ragaa ittisaa otoo hin dhiyeeffatiin murtii bilisaan gadi lakkisu kan hin dandenye ta’u isaa.

አንድ በወንጀል የተከሰሰ ሰው የዐቃቤ ህግ ማስረጃ ተሰምቶ የመከላከያ ማስረጃዉን እንዲያቀርብ ብይን/ትዕዛዝ ከተሰጠ በኋላ እንዲከላከል የተሰጠው ትዕዛዝ ስህተት ቢኖረዉም እንኳን ተከሳሹ ማስተባበያ ማስረጃ ባልቀረበበት ሁኔታ ከሱን በሚሰማው ፍርድ ቤት የዐቃቤ ህግ ማስረጃ በድጋሚ መዝኖ ቀደሞ ከተሰጠዉ ብይን/ትዕዛዝ የተለየ አቋም በመያዝ ተከሳሽን በነፃ እንዲሰናበት ሊወሰን የማይችል ስለመሆኑ፡፡
የሰ.መ.ቁ.220008 ሐምሌ 26/2014 ዓ.ም (ያልታተመ)

https://t.me/ethiolawreview


208865.pdf
477.1Kb
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 208865 በማኅበር ተደራጅቶ የቤት መሥሪያ ቦታ ለማግኘት በመጠባበቅ ላይ እያሉ በሥራ ወደ ሌላ ቦታ መዘዋወር ከመኖሪያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበር አባልነት የሚያሰርዝ ስላለመሆኑ የሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም፡፡

https://t.me/ethiolawreview


ሰ.መ.ቁ. 182136 ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም
በተከራካሪው የተወከለው ጠበቃ ሌል ችሎት ስለተደረበበት ክርክሩ በሚሰማበት ቀን መቅረብ ባለመቻሉ መዝገቡ ከተዘጋ እንደነገሩ ሁኔታ በቂ ምክንያት በመሆኑ የተዘጋው መዝገብ ሊከፈት ይገባል።
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.74 [2] ደንጋጌ መሰረት “በቂ ሆኖ የሚገመት እክል” ምን እንደሆነ የተመለከተ ባይሆንም አመልካች ቀጠሮ ለመቅረት የቻለዉ በምን ምክንያት እንደሆነ አጠቃላይ ሁኔታዉን መመርመር የሚያስፈልግ ሆኖ፣ አመልካች በራሱ ጉድለት ወይም ቸልተኛነት ቀጠሮዉን ሳይከታተል ቀርቶ ካልሆነ በስተቀር፣ ፍትሕ የማግኘትና የመከራከር መብት ከግምት በማስገባት አመልካችን የገጠመዉ እክል እንደበቂ ምክንያት በመውሰድ ለተጠሪ [መዝገቡ የተዘጋው በክልል ሰበር ችሎት በነበረው ክርክር ነው] ተገቢ ኪሳራና ወጪ በማስከፈል፣ የተዘጋዉ መዝገብ ተከፍቶ ክርክሩ እንዲሰማ መድረጉ አግባብ ነዉ። በመሆኑም አመልካች ክርክሩን በጠበቃ ለማካሄድ ወስኖ በሕጉ አግባብ ተገቢዉን ዉክልና ሰጥቶ እያለ ጠበቃዉ ችሎት በሚሰጠዉ ቀነ ቀጠሮ ተገኝቶ አመልካችን ወክሎ ተገቢዉን ክርክር የማቅረብ ኃላፊነት ይኖርበታል። ነገር ግን ጠበቃ የተለያዩ ደንበኞች ሊኖሩት ስለሚችል ፍ/ቤት በሚሰጠዉ ቀነ ቀጠሮ በተቻለ መጠን ለደንበኞቹ ተገቢዉን የጥብቅና አገልግሎት መስጠት በሚያስችለዉ አግባብ አጀንዳዉን አስማምቶ ቀጠሮ እንዲያዝለት ለፍ/ቤቱ ማመልከት ይጠበቅበታል። ይህም ሆኖ ቀጠሮ ተደራርቦበት በአንድ ጊዜ በተለያዩ ችሎቶች የሚቀርበበትን እድል በማዛባቱ ምክንያት የባለጉዳዩ መዝገብ ከፍ ሲል በተጠቀሰዉ የህጉ ድንጋጌ መሰረት ተዘግቶ እንደሆነ፣ አጠቃላይ የነገሩን ሁኔታ በመመርመር፣ የአመልካች የመከራከርና ፍትሕ የማግኘት መብት ታሳቢ በማድረግ መዝገቡ ተከፍቶ ክርክሩ እንዲሰማ ማድረጉ ተገቢ ነዉ።

https://t.me/ethiolawreview


ሰበር_መዝገብ_ቁጥር_219887_ታህሳስ_25_ቀን_2015_ዓ_ም.pdf
832.8Kb
ሰ/መ/ቁጥር - 219887 ታህሳስ 25 ቀን 2015 ዓ.ም
አንድ ሰው ሁለት ሚስቶችን ያገባ እንደሆነ እና ጋብቻው በሞት ወይም በሌላ ህጋዊ ምክንያት የፈረሰ እንደሆነ እና ከሁለቱ ሚስቶች አንደኛዋ ንብረቶቹን በማፍራት ሂደት የተለየ አስተዋጽኦ ያደረገች መሆኑን ያረጋገጠች እንደሆነ ከተፈራው ንብረት ግማሽ ድርሻ የሚገባት ሲሆን፣ የሌላኛዋ ተጋቢ ከባል ጋር ግማሹን ትካፈላለች።

በእርግጥ ሟች ሁለት ሚስቶች ኖረውት የሞተ እንደሆነ ሁለቱ ሚስቶች የንብረቱን ድርሻ ግማሹን ለሁለት ሊካፈሉ እንደሚገባ የፌዴራል ጠቅሊይ ፍርድ ቤት በሰ/መ/ቁጥር 24625 ላይ ውሳኔ ሰጥቷል። በሌላ በኩል በሰ/መ/ቁጥር 45548 ላይ (ቅጽ 13 ላይ እንደታተመው) አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ያሉት እንደሆነ ንብረቶቹን በማፍራት ረገድ ከሚስቶቹ አንደኛዋ ሚስት ከሌላኛዋ የተሻለ አስተዋጽኦ ያደረገች መሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ ባደረገችው አስተዋጽኦ ልክ ልትካፈል ትችላለች የሚል ሃሳብ መነሻ በማድረግ ባል ንብረቱን በሚያፈራበት ጊዜ ከእርሱ ጋር በትዳር የነበረች ሚስት ንብረቱን በማፍራት ረገድ በቀጥታ አስተዋጽኦ እንዳደረገች ግምት ተወስዶ ከንብረቱ ግማሹን ድርሻ የማግኘት መብት እንዳላት እና በአንፃሩ በቀጥታ አስተዋጽኦ ያላደረገች ሚስት ከባል ድርሻ ግማሹን የማግኘት መብት ብቻ ያላት ስለመሆኑ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ::

https://t.me/ethiolawreview


220108.pdf
806.4Kb
Murtii DhIMMWF galmee lakk.isaa 220108 ta'ee irratti gaafa guyyaa 28/11/2014 "....Itti gaafatamummaa yakkaa iyyata sobaa himatni ykn iyyatni dambii hiyyumaatin akka banamuuf dhiyaatu irratti kennamee...

ተጠሪ ሀብት ንብረት እያላቸው እና በንግድ ስራ ላይ ተሰማርተው እያለ ምንም ዓይነት
ንብረት እንደሌላቸው በቃላ መሃላ አቤታ ከማረጋገጣቸውም በላይ ስለዚሁ ጉዳይ በችሎት በተጠየቁበት ወቅት በተመሳሳይ ሁኔታ መናገራቸው ሆነ ብለው ሀሰተኛ ፍሬ ነገርን ለችሎት መግለጻቸውን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 481 እና የኢ.ፌ.ዴ.ሪ
የወንጀል ህግ አንቀፅ 452 መሰረት የወንጀል ክስ ማቅረብ ሳያስፈለግ በቀጥታ በወንጀል ሊያስቀጣ የሚችል ለመልካም ችሎት አመራር ተቃራኒ የሆነ በፍትህ ስራ ላይ ሊደረግ የሚገባው በእውነተኝነት እና በታማኝነት ተግባር ላይ የሚፈፀም የወንጀል ተግባር ነው፡፡

የሰመ.ቁ.220108 ሐምሌ 28/2014 ዓ.ም

https://t.me/ethiolawreview

20 last posts shown.