Posts filter


ክርክር መኖሩን እያወቀ ፍርድ ሲሰጥ ጠብቀው በመምጣት የተሰጠው ፍርድ ይነሳልኝ በማለት አቤቱታ ማቅረብ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 ላይ የተመለከተውን የህግ ድንጋጌ አላማ የሚያሳካ አይሆንም፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ድንጋጌ የውርስ ሀብት ክርክርን በተመለከተ ተፈጻሚነት ያለው ነው ለማለት የሚቻል አይደለም፡፡
እንኳን የውርስ ሀብቱ ሳይከፋፈል ቀርቶ ከተከፋፈለ በኋላም ቢሆን በሌለበት የውርስ ሀብቱ የተከፋፈለበት አካል በሚያቀርበው አቤቱታ ክፍፍሉ ሊፈርስ እና እንደገና ክፍፍሉ ሊደረግ እንደሚገባ የፍ/ብ/ህ/ቁ 1080 ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ክርክር የውርስ ሀብት ክርክር ከሆነ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 358 መሰረት የሚቀርብ ተቃውሞን አቤቱታ አቅራቢው የቀድሞውን ክርክር ያውቃል በማለት አቤቱታውን ውድቅ ማድረግ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው፡፡
- የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅጽ 26 በመ/ቁ 144359 ከሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም ላይ የተወሰደ፡፡

533 0 14 1 12

በቅጽ 19 መ.ቁ. 110549 ላይ የገጠር የእርሻ መሬትን መሸጥ ህገ ወጥ ድርጊት በመሆኑ በይርጋ ሳይገደብ በማንኛውም ጊዜ ሊፈርስ የሚችል ውል ነው ተብሎ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ተሠጥቷል።

የገጠር የእርሻ (ባዶ) መሬት ከገዛ በኊላ ይዞታው ወደ ከተማ ክልል ገብቶ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ገዥ የይዞታው ማረጋገጫ ሰንድ ቢወስድም ይዞታው ወደ ገዢው የገባበት የገጠር መሬት ሽያጭ ውል ከመነሻውም ህጋዊ ባለመሆኑና በህግ አግባብ ባልተገኘ ይዞታ ላይ የሚሰጠው የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ስልጣን ባለው አካል በመሰጠቱ ብቻ ህጋዊ ሊሆን የሚችልበት አግባብ የሌለ መሆኑን ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1195 እና 1196 ጣምራ ንባብ አንፃር ተቀባይነት የሚያገኝ አይደለም።


አንድ የመሬት ሽያጭ ውል ህገወጥ ውል መሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ ገዢው ወገን በመሬቱ ላይ የሰራው ቤት በሻጭ ፍቃድ እንደተሰራ ተደርጎ ግምት የሚወሰድበት አግባብ የለም ።
ቅፅ 22 የሰ/መ/ቁ 141606


የውርስ ሀብት ሰ/መ/ቁ. 210911

ሟች በህይወት እያለ ኑዛዜ ስጦታ ካደረገ በኋላ ይህንኑ ንብረት በተወካዩ አማካይነት በሽያጭ ውል ካስተላለፈው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 900(1) መሰረት የኑዛዜ ስጦታውን ፈራሽ የሚያደርገው በመሆኑ በሽያጭ የተላለፈው ንብረት በፍ/ብ/ሕ/ቁ.826 (1) መሰረት የውርስ ሀብት አይደለም።
ፍ/ብ/ሕ/ቁ. 826 (1)፤ 900 (1)


በወንጀል የማስረጃ ምዘና መርህ የተከሳሽ ሀላፊነት

በወንጀል የማስረጃ ምዘና መርህ መሰረት ከተከሳሽ የሚጠበቀው የማስረዳት ደረጃ እንደ ዐቃቢ ህግ ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በፀዳ መልኩ ማስተባበል ወይም በቂ እና አሳማኝ በሆነ መልኩ ማስረዳት ሳይሆን በቀረቡት የዐቃቢ ህግ ማስረጃዎች ቃል እና በወንጀሉ መፈፀም ላይ "ጥርጣሬ መፍጠር" ብቻ ነው ሲል አስገዳጅ ትርጉም በሰበር መዝ/ቁ 212950 ተሰጥቷል።

share 👇👇
t.me/ethiolawtips


ጀማሪ ጠበቃ የመቅጠር 7 ጥቅሞች

1. የፍርድቤቱ ቀጠሮ 4:00 ሆኖ 2:30 ደርሶ በር ያስከፍታል።😂😂
2. ስልክ ሲደወልለት ገና ጭርር ከማለቱ በግማሽ ጥሪ ያነሳል።😂😂
3. በጣም ለቀላል ጉዳይ ከሀገር ውስጥ ሕግ እስከ አለምአቀፍና አህጉራዊ ተጓዳኝ ሕጎች ያነባል።😂😂
4. ጉዳዩ መልስ ለመቀበል ወይም ብይን ለመስማት (ምንም ክርክር የሌለው ቀጠሮ) ቢሆንም እንኳን እንደ ማትሪክ ተፈታኝ ለሊቱ አጋማሽ ድረስ ይቸክላል።😂😂
5. ጀማሪ ጠበቃ የሀገሪቱን የወደቀ የፍትህ ሲስተም በጫንቃው ተሸክሞ ይጎብጣል፣ያዝናል፣ የሆነ ነገር አድርጎ ለማስተካከልና ለውጥ ለማምጣት ያልማል።😂
6.ይዘንጣል፣ሽክ እምሽክ ይላል፣ጸጉሩን ጢሙን ይቆረጣል፣ሴቷም ሁሌም ፀጉሯን ትተኮሳለች።😂
7. ደንበኞቹን በሸራተን ደረጃ ይንከባከባል 😂
8. ቆይ ግን ነባር ጠበቆች ለምንድነው ቀስ ብላችሁ የማትራመዱት? እግዞ ፍጥነት! እግረመንገዳችሁን የጠበቃ ፈጣን አረማመድ ስልጠና የሚሰጥ ተቋም ካለ ጠቁሙንማ ኤሊነት እየተሰማን ነው።😂
😂😂ይኸው እኔም ዚኒጥጥጥ ብዬ ለ5:00 ቀጠሮ 3:00 በመድረሴ ምክንያት የተጻፈ ፖስት ነው።
ሰናይ ሰኞ ጓደኞቼ!
በጠበቃ Mesi Bahiru


ጋብቻ፣ፍቺና የንብረት ክፍፍል ሕግ በኢትዮጵያ
(የፌደራልና የክልል የቤተሰብ ሕጎች ማብራሪያ)
በዳኛ ድጋፌ አገዙ የተዘጋጀ አዲስ መፅሐፍ


የድርጅቱን አስተዳደር በሚመለከት በውክልና ያለው ሰው ያስተላለፈ መሆኑ እና ተወካዩም በተቀበለው ውክልና መሠረት ሥራውን የሚያከናውን መሆኑ በተረጋገጠ ጊዜ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሆኖ ያለተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ ግብይት ማከናወኑ ሲረጋገጥ ተጠያቂ የሚሆነው ውክልናውን ተቀብሎ ስራውን በውክልና የሚያስተዳድረው ሰው እንጂ ስራ አስኪያጁ ወይም የድርጅቱ ባለቤት ሊሆን አይገባም፡፡

የሰ.መ.ቁ 211028/ያልታተመ/  - ፍርድ ቤት ቅጣት እንዲገደብ የቀረበ ጥያቄ ካለ ምክንያት ሳይሰጥ ተቀባይነት የለውም በሚል ውደቅ ማድረጉ አግባብነት ያለው የውሳኔ አሰጣጥ አይደለም።
በአዋጅ ቁጥር 285/94 በአዋጅ ቁጥር 609/2001 እንደተሻሻለው አንቀጽ 56/1/ አንቀጽ 22/1/ እና አንቀጽ 50/ለ/1 መሠረት የአንድ የንግድ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ በወንጀል ተጠያቂ የሚሆነው እሱ የሚመራው ድርጅት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሆኖ ያለተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ ግብይት ማከናወኑ ሲረጋገጥ እንደሆነ፤ የድርጅቱ ሃላፊነት ከተረጋገጠ የሥራ አስኪያጁ ሃላፊነት የሕግ ግምት የሚወሰድበት ስለመሆኑ እንገነዘባለን፡፡ ሆኖም የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ የድርጅቱን አስተዳደር በሚመለከት በውክልና ያለው ሰው ያስተላለፈ መሆኑ እና ተወካዩም በተቀበለው ውክልና መሠረት ሥራውን የሚያከናውን መሆኑ በተረጋገጠ ጊዜ ተጠያቂ የሚሆነው ውክልናውን ተቀብሎ ስራውን በውክልና የሚያስተዳድረው ሰው እንጂ ስራ አስኪያጁ ወይም የድርጅቱ ባለቤት ሊሆን አይገባም፡፡

የልዩነት ሃሳብ- አንድ ስራ አስኪያጅ ከአዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 132/1/ከተመለከተው የወንጀል ሀላፊነት ነፃ ሊሆኑ የሚችለት ወንጀሉ የተፈፀመው ሳይፈቅዱ ወይም ሳያውቁ መሆኑን አሊያም በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ያለና ነገሮችን በጥንቃቄ የሚያይ ሰው የጥፋቱን መፈፀም ለመከላከል ይወስዳቸዋል ተብለው የሚገመቱ ጥንቃቄዎችን ለማድረግ ተገቢውን ትጋትና የአሰራር ጥበብ የተሞላበት እርምጃ መውሰዳቸውን በአንቀፅ 132/2/ አግባብ ሲያስረዱ ቢሆንም በዚህ አግባብ ለማስረዳታቸው የሥር ፍርድ ቤት መዝገብ አያሳይም፡፡
s-DFLO
Join👇
https://t.me/ethiolawtips




👉ጠፋ የተባለ ሰው በተመለሰ ጊዜ ንብረቶቹ የተሸጡ ከሆነ ለማግኘት መብት የሚኖረው የንብረቶቹን የሸያጭ ዋጋ ስለመሆኑ፣
==================================
✍️ አንድ ሰው የጠፋና ከሁለት ዓመት ወዲህ ወሬውን ያልሰጠ እንደሆነ ማናቸውም ባለጉዳይ ቢሆን የሰውየው መጥፋት በፍርድ ቤት እንድወሰን ማመልከት እንደሚችል በፍ/ህ/ቁ 154(1) ተደንግጓል።
ይሁን እንጂ ጠፍቷል የተባለ ሰው ልመለስ ይችላል። ስለሆነም ጠፋ የተባለ ሰው በተመለሰ ጊዜ ንብረቶቹ የተሸጡ ከሆነ ለማግኘት መብት የሚኖረው የንብረቶቹን የሸያጭ ዋጋ እንጂ ንብረቶቹ እንድመለስለት መጠየቅ አይችልም።
👉 ማጣቀሻ(Ref):- የፍ/ብ/ህ/ቁ. 171(1)፣ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር መ/ቁ 30298 (ቅጽ 5)


#DNA(የዘረ-መል ምርመራ) ለአባትነት ክስ አቅራቢ ማስረጃ አይሆንም።🤔
አባትነት ክስ በፍርድ ቤት ሊቀርብ የሚችለው በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 143(ከሀ -ሠ) ባሉ አምስት ምክንያት ብቻ ሲሆን አባትነት ክስ አቅራቢ የዘረ መል ምርመራን(DNA) ማስረጃ አድርጎ ማቅረብ የማይችል ሲሆን ማስረጃ አድርጎ ማቅረብ የሚችለው ክስ የቀረበበት ወገን በመካድ አቤቱታ በተሻሻለው ቤተሰብ ህግ አንቀጽ 167 ነው። በተሻሻለው ቤተሰብ ህግ አንቀጽ 143 ከተዘረዘረው የአባትነት ክስ ምክንያት ወይም ማስረጃ ሊሆኑ ከሚችሉት ውስጥ የዘረ መል ምርመራ(DNA) በማስረጃነት አላሰፈረውም። ይህንን ሀሳብ የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 145 የሚያስረው ሲሆን በአንቀጽ 143 ከተገለጹት ማስረጃ ውጪ አባትነት ክስ በፍርድ ቤት ሊረጋገጥ እንደማይችል ያስቀምጣል።


አንድን ተከሳሽ ከወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 67(ሀ) አኳያ በዋስትና ቢለቀቅ ግዴታውን አክብሮ ሊቀርብ አይችልም ብሎ ዋስትናን ለመከልከል የወንጀል ድርጊቱ አፈፃፀም ሁኔታ እና የወንጀሉ ክብደት ሊመዘን የማይገባ ስለመሆኑ፤ ይህ መመዘኛም በክርክር ሂደት ወደፊት የሚረጋገጥ ከመሆኑ አንፃር ከጥፋተኝነት በፊት ንፁህ ሆኖ የመገመትን መብትኖ የሚጥስ በመሆኑ የዋስትና መብትን መከልከያ ምክንያት ተደርጎ የማይወሰድ ስለመሆኑ የተሰጠ አዲስ የሰበር ውሳኔ በሰበር መዝ/ቁ 269430 ጥቅምት 29/2017
Join👇
https://t.me/ethiolawtips


የድምጽ ሁከት ወይም ተገቢ ያልሆነ ሽታ ከጎረቤት ደርሶብኛል በሚል የሚቀርብ ክስ - በባለሀብትነት መብት አላግባብ መገልገል - (የፍ/ህ/ቁ.1225/1226 ) የሚመለከት በመሆኑ የክስ ማመልከቻውም ሆነ የሚሰጥ ዝርዝር ፍርድ ሁከት ( የፍ/ህ/ቁ .1149 ) ላይ የተመለከተውን ፍሬ ሀሳብ በማንሳት ሳይሆን ተገቢውን ድንጋጌ በመለየት ሊሆን እንደሚገባ የፌ/ሰ/ሰ/ችሎት በመ.ቁ 232474 ላይ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል።
( ያልታተመ )
Join👇
https://t.me/ethiolawtips


ምንም እንኳ መኪናው በወንድም ወይም በአባት ስም የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ የወጣ ቢሆንም የግዥውን ገንዘብ የከፈልኩት እኔ ነኝ በሚል የንብረቱ ባለቤት ለመሆን አይቻልም ። በተመሳሳይ በቤትና ቦታ ላይም ተመሳሳይ አስገዳጅ ውሳኔ ተሰጥቷል። እንዲሁም ስመ- ንብረቱ በእርሱ ወይም በእርሷ ቢሆንም ቤቱን የሰራሁት በራሴ ገንዘብ ነው የሚለው መከራከሪያም በፍ/ህ/ቁ 1723 መሰረት የተደረገ ስምምነቱ ከሌለና ግራ ቀኙ ከተካካዱ ዋጋ እንዴለሌው በፌዴሬሽን ም/ቤት ትርጉም የሰ/መ/ቁ 156318 ተሰጥቶበታል።
Join👇
https://t.me/ethiolawtips





16 last posts shown.