✳️ የመረጃዎቻችን መጠባበቂያ "Backup" በምን መልኩ እና ምን ላይ ማስቀመጥ እንችላለን?
🏳️ በኮምፒውተሮቸችን በተለያየ መልኩ ሊፈጠሩ በሚችሉ ሳይበር ጥቃቶች ፣ በኮምፐውተሩ አካል ላይ በሚደርስ ጉዳቶች እንዲሁም የኮምፒውተሩ ውስጥ የሥርዓት መዛባት አማካኝነት እጅግ አስፈላጊ ምንላቸውን መረጃዎችን ልናጣ እንችላለን፡፡ እነዚህን አደጋዎችን ለመቀነስ መጠባበቂያ መረጃ መያዝ ወሳኝ ነው፡፡ በመሆኑም እነዚህን መረጃዎች ለመያዝ የሚውሉ መገልገያዎችን እንጠቁምዎ:-
🏳️ ፍሎፒ ዲስክ /Floppy Disk/:- ትንሽና አነስተኛ መጠን ያለው ዲስክ ሲሆን አቅሙም 1.4 MB ነው፡፡ ጠቃሚ መረጃዎችን በፍሎፒ ዲስክ ለመያዝ በርካታ ዲስኮች ያስፈልጉናል፡፡ የድሮ ኮምፒውተሮች በብዛት ፍሎፒ ዲስክ መጠቀሚያ የነበራቸው ሲሆን በአሁኑ ወቅት የሚመረቱ ኮምፒውተሮች አብዛኞቹ አገልግሎቱ የላቸውም፡፡
🏳️ ዚፕ ድራይቭ /Zip Drive/፡- ዚፕ ድራይቭ በመቶዎች የሚቆጠር MB መጠን ያላቸው ፋይሎችን /data/ የመያዝ አቅም አላቸው፡፡ ዚፕ ድራይቮችን ለመጠቀም የግድ ኮምፒውተራችን ላይ መሰካት /hook up/ ይኖርባቸዋል፡፡
🏳️ ቴፕ ድራይቭ / Tape Drive/፡- ቴፕ ድራይቭ በመቶዎች የሚቆጠር GB (በሺዎች የሚቆጠር MB) መጠን ያላቸው ፋይሎችን ይይዛል፡፡ ይህም ተጨማሪ ድራይቭ በመሆኑ የግድ በኮምፒውተራችን ላይ መሰካት ይኖርበታል፡፡
🏳️ ሲዲ በርነር /CD Burner/፡- ሪከርድ የሚያደርጉ ሲዲዎች /CD-Rs/ እስከ 700 MB የሚሆኑ ፋይሎች የመያዝ አቅም አላቸው፡፡ አሁን ላይ የምንጠቀምባቸው አብዛኞቹ ኮምፒውተሮች ሲዲ በርነር /CD Burner/ አላቸው፡፡ አንዳንዶቹም ዲቪዲ በርነር /DVD Burners/ አላቸው፡፡ ዲቪ ዲ አር ኤስ /DVD-Rs/ እስከ 4.7 GB ፋይል የመያዝ አቅም አላቸው፡፡ ስለዚህ በአማራጭ የመጠባበቂያ ፋይል መያዣ ሊያገለግሉ ይችላሉ፡፡
🏳️ ፍላሽ ድራይቭ /Flash Drive/፣ የ ኤስ ቢ ድራይቭ /USB Drive/ እና ተምብ ድራይቭ /Thumb Drive/፡- ለአንድ ነገር የተለያየ ስያሜ ቢኖርም በኮምፒውተሮቻችን የዩ ኤስ ቢ /USB/ ፋይል መቀበያ በኩል በቀላሉ የሚሰኩ ተነቃይ ድራይቨሮች ናቸው፡፡ እነዚህ ድራይቨሮች ከ10 MB የሚጀምሩ ሲሆን 1 GB፣ 2 GB፣ 4 GB፣ 8 GB፣ 16 GB፣ 32 GB፣ 64 GB … እያሉ አሁን ላይ 4TB ፋይል የመያዝ አቅም ያላቸው ፍላሽ ድራይቮች በገበያ ላይ ይገኛሉ፡፡ ፍላሽ ዲስኮች በቀላሉ በኪስ የሚያዙና ተንቀሳቃሽ ቢሆኑም በቀላሉ ወድቀው ሊጠፉ የሚችሉ በመሆኑ ጥንቃቄ ሊደረግባቸው ይገባል፡፡
🏳️ ኤክስተርናል ሃርድ ዲስክ /External hard Drive/:- ኤክስተርናል ሀርድ ድርይቭ በኮምፒውተር ሲስተሞቻችን ውጪ ከፍተኛ መጠን ያላቸው ፋይሎችን የምናስቀምጥበት መሣሪያ ነው፡፡ ይህ መሣሪያ /Drive/ ፋይሎችን ይዞ ከቦታ ወደ ቦታ ለመንቀሳቀስ የሚያስችል እና ከኮምፒውተራችን ጋር በዩ ኤስ ቢ /USB/፣ በፋየርዋየር /Firewire/ ኮኔክሽን ወይም በገመድ አልባ /wirelesely/ ሊገናኝ የሚችል ነው፡፡
🏳️ ታይም ማሽን /Time Machine/፡- Time Mac ለተጠቃሚዎች አማራጭ የኤክስተርናል ፋይል መጠባበቂያ መያዣ መንገድ ነው፡፡ ይህ መጠባበቂያ መያዣ ዘዴ ለ24 ሰዓት በቀጥታ ፋይሎቻችንን ለማስቀመጥ ያስችላል፡፡ በመሆኑም ፋይሎች ተረስተው ለጉዳት እንዳይጋለጡ ያግዛል፡፡ ታይም ማሽን በመጠባበቂያው የሚይዘው የተመረጡ ፋይሎችን ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ድራይቨሩን ነው፡፡
🏳️ ኔትወርክድ የሆነ የመረጃ ማካማቻ /Networked Attached Storage/:- ይህ ከአንድ በላይ የሆኑ ኮምፒውተሮች በኔትወርክ ተገናኝተው መረጃ የሚቀመጥበት ሥርዓት ሲሆን ይህም በስርዓት የተደረደሩ፣ ያልተደጋገሙ የፋይል ማከማቻ ኮኒቲነሮችን እና በርካታ የዲስክ ድራይቭ አካላትን የያዘ ነው፡፡ ይህም በፍጥነት መረጃ ለማግኘት፣ በቀላሉ መረጃዎችን ለማስተዳደርና ለማስተካከል የሚያስችል ዘዴ ነው፡፡
🏳️ ስውር የበይነ መረብ መረጃ ማከማቻ /Cloud Storage/:- ይህ የፋይል ማከማቻ ዓለም አቀፍ የመረጃ ማከማቻ ሥርዓት ሲሆን በኔትወርክ አማካኝነት በመገናኘት መረጃዎቻችን ክላውድ ተብሎ በሚጠራ የመረጃ መጠባበቂያ ሥርዓት /Cloud Server/ ውስጥ የምናስቀምጥበት መንገድ ነው፡፡ በርካታ የክላውድ ማማቻ ዓይነቶች በበየነ-መረብ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን እነዚህም በነጻ ወይም በክፍያ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው፡፡ iCloud፣ Dropbox፣ Google Drive እና OneDrive የታወቁ የመረጃ ማከማቻ መንገዶች ናቸው፡፡ መረጃዎቹ የሚከማቹበት ሥፋራ በመራጃ በለቤቶቹ ቁጥጥር ሥር ባለመሆኑ የመረጃዎቹ ደህንነት አስተማማኝ እንደስጋት ይታያል፡፡
🏳️ ፕሪንት ማድረግ /Printing/:- ምንም አንኳን መረጃዎቻችን በሶፍት ኮፒ የምናስቀምጠውን የህል የተማቹ ባይሆኑ ኮምፒውተሮቻችን በተለያየ ምክንያት ለቀናት አገልግሎት መስጠት የሚያቆሙበት አጋጣሚ ቢፈጠር ፕሪንት ያደረግናቸው ፋይሎች እጅጉን ይጠቅሙናል፡፡
‼️Join & Share
📢 :
@samitech0👥 ፡
@Samitech0