#EthiopiaCheck Fact Check
የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ላለፉት አራት ወራት ሲቀንስ ነበር?
ዛሬ በተካሄደዉ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጉባዔ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ለምክር ቤቱ አባላት ማብራርያ ከሰጡባቸዉ ጉዳዮች መካከል አንዱ የዋጋ ግሽበት ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው “ባለፉት አራት ወራት የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት እያደገ ሳይሆን በመቀነስ ላይ ነዉ” ብለዋል።
ይህ ንግግራቸው በዚህ ማስፈንጠሪያ https://www.facebook.com/hoprparliament/videos/699162021523622/ ከ1፡09፡00 ጀምሮ ይገኛል።
ይህ የዋጋ ግሽበት መቀነስም የበርካታ ስራዎች ውጤት መሆኑን ተናግረዋል።
ይሁን እንጂ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ከኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የጥቅምት ወር 2015 ዓ.ም የዋጋ ግሽበት ሁኔታ ሪፖርት ጋር የሚቃረን መሆኑን ኢትዮጵያ ቼክ ተመልክቷል።
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት መረጃ እንደሚያመለክተው የመስከረም ወር 2015 አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 30.7 ሲሆን የጥቅምት ወር 2015 ዓ.ም ደግሞ 31.7 ከመቶ ነው። ይህም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበቱ በጥቅምት ወር በአንድ ከመቶ መጨመሩን ያሳያል።
“በጥቅምት ወር 2015 ዓ.ም የምግብ የኢንዴክሱ ክፍሎች በተለይ አትክልት መጠነኛ ቅናሽ ያሳዩ ሲሆን ምግብ ያልሆኑ የኢንዴክሱ ክፍሎች ላይ መጠነኛ ጭማሪ ታይቷል” ይላል የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሪፖርት።
በጥቅምት ወር 2015 ዓ.ም የአጠቃላይ ዋጋ ግሽበት መጠን መጨመር ዋና ምክንያትም በነዳጅ ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ መሆኑም በሪፖርቱ ተገልጿል።
@EthiopiaCheck