#EthiopiaCheck Fake Account Alert
የኢንዱስትሪ ሚንስትሩን የአቶ መላኩ አለበልን ስምና ምስል በመጠቀም የተከፈተ ሀሰተኛ የፌስቡክ አካውንት።
የኢንዱስትሪ ሚንስትሩን የአቶ መላኩ አለበልን ስምና ምስል በመጠቀም የተከፈተ የፌስቡክ አካውንት የገንዘብ ድጋፍ (grant) የሚያስገኝ ውድድርን የተመለከተ መልዕክት እያጋራ እንደሆነ ተመልክተናል።
ይህ 'Mr. Meleku Alebel' የሚል ስያሜን የሚጠቀምና ከ750 በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ አካውንት ከሁለት ሳምንት በፊት የተከፈተ ሲሆን የገንዘብ ድጋፉን የተመለከቱ መልዕክቶችን ለፌስቡክ ክፍያ በመፈፀም (promote/sponsor በማድረግ) እንደሚያስተጋባም አስተውለናል።
በገጹ የሚጋሩ የገንዘብ ድጋፍ የሚያስገኙ ውድድሮችም በመቶ ሚሊዮኖች የሚያስገኙ መሆናቸው የሚነበብ ሲሆን በአቀራረብም ትክክለኛ እንዲመስሉ ሆነው የተዘጋጁ ናቸው።
ኢትዮጵያ ቼክ የገጹን እና የገንዘብ ድጋፉን ትክክለኛነት ለማወቅ የኢንዱስትሪ ሚንቴርን ጠይቋል። የሚንስቴሩ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ገጹም ሆነ በገጹ የሚጋሩ የገንዘብ ድጋፍ ውድድሮች ሀሠተኛ መሆናቸውን ገልጿል።
በተጨማሪም አቶ መላኩ አለበል በትዊተር ማረጋገጫ ያለው አካውንት እንዳላቸው ነገር ግን የፌስቡክ ገጽ እንደሌላቸውና መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።
ተመሳስለው የተከፈቱ ሀሰተኛ ገጾችን እና አካውንቶችን ባለመከተል ከሀሰተኛና ከተዛቡ መረጃዎችን ስርጭት እራሳችንን እንጠብቅ።
@EthiopiaCheck