⬆️
#EthiopiaCheck Explainer
ተመሳሳይ የሰሌዳ ቁጥር ስላላቸዉ እና በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተጋሩ ስለሚገኙት መኪናዎች ኢትዮጵያ ቼክ ያዘጋጀው ማብራርያ።
ሰሞኑን በተለይ በቲክቶክ /TikTok/ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ተመሳሳይ የአዲስ አበባ ታርጋ/ሰሌዳ ቁጥር ያላቸዉ ሁለት ጥንድ መኪናዎች ቪዲዮ በብዛት ሲጋራ ተመልክተናል።
እነዚህ ተመሳሳይ ታርጋ ቁጥር ያላቸዉ መኪናዎች ደግሞ ኮድ 2- አአ B09472 (ቶዮታ ኮሮላ እና ራቫ4) እንዲሁም ኮድ 3- አአ 25473 የሆኑ ሁለት ስሪታቸው ቆየት ያለ የሚመስል ፒክአፕ መኪናዎች ናቸዉ።
እነዚህ ተመሳሳይ ታርጋ ያላቸዉ መኪኖችን ጉዳይ በተመለከተ ኢትዮጵያ ቼክ የአዲስ አበባ አስተዳደር አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣንን ማብራሪያ ጠይቋል።
የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ በድሉ ሌሊሳ ኮድ 2- አአ B09472 ታርጋ ቁጥር የቶዮታ ራቫ4 /Toyota RAV4/ መሆኑን እና የዚህ መኪና ባለንብረት ታርጋዉ መሰረቁን መጋቢት 2014 ማመልከቱን ነግረዉናል።
“ትክክለኛ (ባለ ታርጋዉ) ባለ ራቫ4 ነዉ። ተሽከርካሪ አቁሞ ሰሌዳ ይሰረቅበታል፤ ከፊትም ከሗላም ማለት ነዉ” ብለዋል አቶ በድሉ።
በዚሁ መሰረትም የራቫ4 መኪና ባለንብረት የመኪናዉ ሰሌዳ እንደጠፋበት ፖሊስ ጋር አስመስክሮ ለአዲስ አበባ አስተዳደር አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ሪፖርት ማድረጉንም ይናገራሉ።
ባለስልጣኑም ጉዳዩ በጋዜጣ እንዲታተምና ለአንድ ወር እንዲቆይ ካደረገ በኋላ ሰሌዳዉ እንዲታተም ለፌደራል ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት ድርጅት ደብዳቤ መጻፉን እና ሰሌዳዉም ታትሞ መሰጠቱን ነግረዉናል።
ከወራት በኋላ ደግሞ የራቫ 4 ተሽከርካሪ ባለንብረት የተሰረቀበት ታርጋ በቶዮታ ኮሮላ ላይ ተለጥፎ ሲነዳ በማየቱ በመከታተል ለፖሊስ ሪፖርት ማድረጉን እና መኪናዉም መስከረም 18 ቀን 2015 በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን እንዲሁም ለጉምሩክ ኮሚሽን ተላልፎ መሰጠቱንም አቶ በድሉ ነግረዉናል።
“የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ (መኪናዉን) ለጉምሩክ ማስረከቡን ጥቅምት 23 ቀን 2015 ደብዳቤ ጽፎልናል። ተሽከርካሪዉ በህጋዊ መንገድ የገባ እንዳልሆነ እና ሰሌዳዉንም በዛዉ መንገድ ያገኘ ስለሆነ ይዞት ለጉምሩክ አስረክቦ ምርመራ አልጨረስኩም ብሏል” ብለዋል።
ራቫ4 ተሽከርካሪውም በቁጥጥር ስር ሁኖ ማጣራቶች እየተደረጉ እንደሆነም አቶ በድሉ ሌሊሳ ለኢትዮጵያ ቼክ ነግረዋል።
በተጨማሪም ተመሳሳይ ሰሌዳ ቁጥር ያላቸዉ ኮድ 3- አአ 25473 የሆኑ ሁለት ፒክ አፕ መኪኖችም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዉለዉ ምርመራ እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል አንዳንድ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ተጠቃሚዎች “በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ለሚገቡ መኪኖች በህገ ወጥ መንገድ ሰነዶች ተሰርተዉ ሰሌዳም ይሰጣቸዋል” የሚሉ ቅሬታዎችን ሲያጋሩ ተመልክተናል።
ይህን ጉዳይ የጠየቅናቸዉ አቶ በድሉ ሌሊሳ ሁለት መኪኖች በተመሳሳይ ሰሌዳ የሚመዘገቡበት አሰራር እንደሌለ፤ ይህን ማድረግ የሚያስችል የአሰራር ክፍተትም እንደሌለ ይናገራሉ።
“መኪና በኮንትሮባንድም ሆነ በሌላ መንገድ ገብቶ እኛጋ መጥቶ ሲስተም ላይ ተመዝግቦ ማለፍ የሚችልበት ክፍተት ምንም የለም፤ ዜሮ ነው” ብለዋል።
ነገር ግን በህገ ወጥ መንገድ ወይም በኮንትሮባንድ የገባን መኪና ነድቶ ለማሳለፍ፤ ወንጀል ለመፈጸም እና ለሌላ አላማ ለማዋል የሰሌዳ ስርቆት እንደሚፈጸም እና ፎርጅድ ቦሎ በመስራትም ለጊዜዉ ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ ጥቅም ላይ እንደሚዉልም ተናግረዋል።
ስለዚህም የመኪና ባለንብረቶች የመኪናቸዉ ሰሌዳ እንዳይሰረቅ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ፤ ከተሰረቀም ለፖሊስ እና ሰሌዳዉን ለሰጠ አካል በፍጥነት ሪፖርት ማድረግ እንዳለባቸዉ አሳስበዋል።
@EthiopiaCheck