#EthiopiaCheck Scam Alert
"የኳታር ኤምባሲ የከፈተው የቴሌግራም ቻናል የለም"--- አዲስ አበባ የሚገኘው የኳታር ኤምባሲ ለኢትዮጵያ ቼክ
ከሰሞኑ "የ2022 የአለም ዋንጫ አዘጋጅ ኳታር የአለም ዋንጫ መረጃዎች የምትለቅበትን የቴሌግራም ቻናል ለብዙዎች ተደራሽ ለማድረግ በማሰብ ቻናሉን ለሚቀላቀሉ በሙሉ የ 10,000 ሺህ ብር ቦነስ አዘጋጅታለች" የሚል መረጃ በተለይ ቴሌግራም ላይ በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል።
ይህ ቻናል "የኳታር መንግስት ለኢትዮጵያ እና ለሌሎች 8 የአፍሪቃ ሀገራት ከ 20,000,000 ብር በላይ በመመደብ ዜጎች ስልኮቻቸውን (ቴሌግራማቸውን) ብቻ ተጠቅመው ወደ አለም ዋንጫው የቴሌግራም ገፅ በመግባት ወይም ሌሎች ወዳጆቻቸውን ወደ ገፁ ሲጋብዙ ተሸላሚ የሚሆኑበትን መንገድ አዘጋጅቷል" የሚል መረጃ በማሰራጨት በአምስት ቀናት ብቻ ከ23,000 በላይ የቴሌግራም ተከታታዮችን አፍርቷል።
ሽልማቱን እያስተዋወቀ ያለው እና ያዘጋጀው በአዲስ አበባ የሚገኘው የኳታር ኤምባሲ እንደሆነ፣ እንዲሁም ገንዘብ መቀበያ መንገዱ በቴሌብር እና በ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆኑን ያስረዳል።
በዚህ ዙርያ ኢትዮጵያ ቼክ አዲስ አበባ የሚገኘውን የኳታር ኤምባሲ ያነጋገረ ሲሆን "የኳታር ኤምባሲ የከፈተው የቴሌግራም ቻናል የለም፣ እንዲህ አይነት ሽልማትም አልተዘጋጀም። ይህ በኤምባሲው እውቅና የሌለው ነው" የሚል ምላሽ አግኝቷል።
ምንጫቸው የማይታወቅ፣ በይፋ ያልተነገሩ እና ለማጭበርበር የተከፈቱ አካውንቶችን ባለመከተል ራሳችንን ከመጭበርበር እንከላከል።
@EthiopiaCheck