መግለጫ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28 ቀን 2016 ዓ. ም
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ ኤርትራ በየቀኑ የሚያደርገውን በረራ ለመቀጠል ከአቅም በላይ የሆኑ ችግሮች አስመራ ውስጥ ስላጋጠሙት ከነገ ነሐሴ 28 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ አስመራ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ማቋረጡን ለክቡራን ደንበኞቹ ከይቅርታ ጋር ይገልጻል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ ለመጓዝ ቀድመው ትኬት ለቆረጡ ውድ መንገደኞቹ ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ በሌሎች አየር መንገዶች የሚጓጓዙበትን ሁኔታ ያመቻቻል። አለያም እንደአማራጭ በውድ ደንበኞቹ ፍላጎት ለትኬት የከፈሉትን ገንዘብ ሙሉውን ተመላሽ ያደርጋል።
ድረገጻችንን በመጎብኘት www.ethiopianairlines.com አልያም ወደ ዓለም-አቀፍ የጥሪ መቀበያ ማዕከላችን በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል።
በዚህ አጋጣሚ ከአየር መንገዳችን አቅም በላይ በሆነ ሁኔታ በተፈጠረው የበረራ መቋረጥ በውድ ደንበኞቻችን ላይ ለሚፈጠረው መጉላላት አየር መንገዱ ከልብ ይቅርታ ይጠይቃል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የስታር አላያንስ አባል