Ethiopian Digital Library


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Education


በዚህ ቻናል ስለ
👉ትምህርት፣
👉ሥራ እና
👉ማህበራዊ ጉዳይ
መረጃ ያገኛሉ!
Contact: @ethiodlbot

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Education
Statistics
Posts filter




Khaby Lame - 161.4 million followers - TikTok

2020: 0 Dollar

2023: 16,000,000 Dollar

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


ፈተናውን ሙሉ በሙሉ ደፍኖታል

ሳህሌ ነጋሲ የተባለው የ17 አመቱ ታዳጊ በአሜሪካ ኒው ጀርሲ ተማሪ ሲሆን የዘንድሮውን የኮሌጅ መግቢያ ፈተና ወይንም ሳት (SAT) የወሰደ ነው፡፡ በውጤቱም 1600 ነጥብ ማምጣት ችሏል፡፡ ይህም ማለት ፈተናውን ሙሉ በሙሉ ደፍኖታል፡፡

በመላው አሜሪካ በሚሰጠው በዚህ ፈተና እንዲህ አይነት ውጤት እንብዛም አይመጣም፡፡

የሳት ፈተናን መድፈን የሚችሉት ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከአንድ ፐርሰንት በታቹ ብቻ ናቸው፡፡ ማለትም በየአመቱ የሚደፍን ተማሪ የማይኖር ሲሆን ከአመታት በኋላ አንድ ተማሪ ደፍኖ ይገኛል፡፡ ሳህሌ ነጋሲ ከእነዚህ ጥቂት ተማሪዎች መካከል ዘንድሮ ተገኝቷል፡፡

በኒውዮርክ ተወልዶ በኒው ጀርሲ ያደገው ይህ ተማሪ ለዚህ ፈተና ዝግጅት ያደረገው በትምህርት ቤት በሚሰጠው ትምህርት ብቻ እንዳልሆነ ገልጿል፡፡ ከኢንተርኔት ላይ በነፃ የሚሰጡ ትምህርቶችን መከታተሉ እንደጠቀመውም አስረድቷል፡፡

በኒውዮርክ ተወልዶ በኒው ጀርሲ ያደገው ይህ ተማሪ ለዚህ ፈተና ዝግጅት ያደረገው በትምህርት ቤት በሚሰጠው ትምህርት ብቻ እንዳልሆነ ገልጿል፡፡ ከኢንተርኔት ላይ በነፃ የሚሰጡ ትምህርቶችን መከታተሉ እንደጠቀመውም አስረድቷል፡፡

በቀጣይነት በሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ የህግ ትምህርት የመከታተል ፍላጎት እንዳለው ያስረዳው ሳህሌ ጨምሮም ‹‹ከአስር አመት በኋላ በዚህ ፈተና ካመጣሁት ውጤት የበለጠ ትልቅ ነገር እሰራለሁ›› በማለት ህልሙን አስታውቋል፡፡

የዚህ ተማሪ መረጃ ከትላንት ጀምሮ ይፋ ከሆነ በኋላ አንዳንድ ኢትዮጵያዊያን ተማሪው ኢትዮጵያዊ እንደሆነ እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡ ኤርትራዊያን በበኩላቸው ደግሞ የአገራቸው ዜጋ መሆኑን እየገለፁ ናቸው፡፡ #Zehabesha

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library




ስንት ገባች ከእናንተ ጋር?

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


" በዚህ ዓመት 150 ሺህ የሚደርሱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናቸውን በበየነ መረብ (ኦንላይን) ይወስዳሉ " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሁሉም ተማሪዎች በተማሩበት ሥርዓተ ትምህርት ይዘት ይዘጋጃል፡፡

የ2017 ዓ.ም ተፈታኝ ተማሪዎች ከ9ኛ - 10ኛ በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት፣ ከ11ኛ - 12ኛ ደግሞ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ናቸው። ነገር ግን በ2015 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ በናሙናነት በተመረጡ ት/ቤቶች የስርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ ላይ የተሳተፉ ት/ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች 10ኛ ከፍልን በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ናቸው፡፡  በአማራ ክልል በ2016 የትምህርት ዘመን መፈተን ሲገባቸው በጸጥታ ችግር ምክንያት ሳይፈተኑ የቀሩና የ11ኛ ክፍልን በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ት/ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች በ2017 ዓ.ም  የሚፈተኑ አሉ፡፡ በመሆኑም የ2017 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከላይ የተገለጹትን ሶስቱንም ነባራዊ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ባስገባ እና ሁሉንም የዘመኑን ተፈታኝ ተማሪዎች በማከለ መንገድ ስታንዳርዱን፣ ደህንነቱንና ሚስጢራዊነቱን ጠብቆ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል።

ስለሆነም የፈተና ዝግጅቱ፡-
    1) ከ9ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከነባሩ ሥርዓተ ትምህርት፣
    2) ከ10ኛ ክፍል በነባሩና በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ተመሳሳይ ይዘቶች፣
    3) ከ11ኛ ከፍል በነባሩና በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ተመሳሳይ ይዘቶች፣
    4) ከ12ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሰረት የሚዘጋጅ ይሆናል።

ከላይ የተዘረዘረው የዝግጅት ሂደት በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች ላይ እንደተጠበቀ ሆኖ የኢኮኖሚክስ የትምህርት ዓይነት ግን በስርዓተ ትምህርቱ አዲስ የተጀመረ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በ12ኛ ክፍል ይዘት ላይ ብቻ ተመስርቶ የሚዘጋጅ ይሆናል።

በአጠቃላይ ሁሉም ተማሪዎች ከ9ኛ -12ኛ ክፍል በየተማሩበት የሥርዓተ ትምህርት ይዘት ላይ መመስረት ፈተናው እንደሚዘጋጅ አውቀው ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።

ስለሆነም ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ወላጆች፣ መምህራንና መላው የትምህርት ማህበረሰብ ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
                         
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት!

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


#መልካም_ዜና: አሊባባ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ #በኢትዮጵያ_ብር ክፍያ መቀበል እንደሚጀምር አስታወቀ!

አለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ተቋም የሆነው አሊ ባባ እንደገለፀው ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ #በአሊ_ኤክስፕረስ የበርካታ አገራትን ገንዘብ ጥቅም ላይ ያውላል፡፡

ከእነዚህ አገራት መካከል ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ፤ ግብፅ፣ ኬንያ እና ደቡብ አፍሪካ ይገኙበታል፡፡ የክፍያ መፈፀሚያ ገንዘቦችን ማስፋፋት ያስፈለገው ለአፍሪካ ተጠቃሚዎች በስፋት ተደራሽ ለመሆን በማሰብ እንደሆነ የጠቀሰው አሊ ባባ በተጨማሪም በአለም አቀፍ የክሬዲት ካርዶችና #የውጭ_ምንዛሬ ላይ ያለውን ጥገኝነት ለማስቀረት እንደሆነ አስረድቷል፡፡

የአፍሪካ አገራትን ገንዘብ በግብይቱ ውስጥ ጥቅም ላይ ማዋሉ በአለም አቀፍ የክፍያ ስርአት የተነሳ ለአፍሪካዊያን ትልቅ ማነቆ የሆነውን ችግር ለመቅረፍ ማቀዱንም አስታውቋል፡፡ በዚህም አዳዲስ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎችን እንደሚያገኝ ተስፋ ሰንቋል፡፡

ለዚህ እንዲረዳው በተጠቀሱት አገራት ከሚገኙ የዲጂታል ክፍያ አገልግሎት ሰጪዎች ጋር ጥምረት መፍጠሩን የገለፀው አሊ ባባ ከሚቀጥለው ሳምንት ማለትም #የካቲት_17 ጀምሮ ብርን ጨምሮ የተለያዩ ገንዘቦችን በግብይት ስርአቱ ውስጥ እንደሚያካትት አስታውቋል፡፡

#ለምሳሌ፦ አሊባባ ከቴሌ ብር ጋር ለመስራት ቢስማማ ከአሊ ኤክስፕረስ ላይ ኦንላይን/Online እቃ ለመግዛት ቴሌ ብር ተጠቅሞ መክፈል ይቻላል ማለት ነው!

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


በ2017 የትምህርት ዘመን ከ50ሺ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለመውሰድ ተመዝግበዋል

በአዲስ አበባ በማህበራዊና በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት መስኮች የ2017 ዓመት 50ሺ 807 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ፈተና እንደሚወስዱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

በ2017 የትምህርት ዘመን  የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በከተማ አስተዳደሩ በበይነ መረብ ኦን ላይን በውጤታማነት ለመስጠት በሚያስችል ስራ እየተሰራም መሆኑን የቢሮው ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በከተማ አስተዳደሩ በበይነ መረብ በውጤታማነት ለመስጠት እንዲቻል ከወዲሁ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ለማከናወን እቅድ መዘጋጀቱንና ወደ ስራ መገባቱን አንስተዋል። ፈተናው ኦን ላይን እንደመሰጠቱ ኮምፒውተሮችና እና መሟላት የሚገባቸውን መሰል ግብዓቶች የመለየት ስራ ተጀምሯል።

ለፈተናው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን የማዘጋጀት ተግባራት ከወዲሁ በመጀመር ፈተናው በታቀደለት መርሃ ግብር እንዲሰጥ በትኩረት መስራት ይገባል ተብሏል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


በ1929 የካቲት 12 ቀን የተፈጸመውን ግፍ ደራሲ ተመስገን ገብሬ በአይኑ የተመለከተውን እንደሚከተለው ከትቦ አስነብቧል

"ቀኑ ብርቱ ፀሐይ ነበር፡፡ በዚያ እስር ቤት በማዘጋጃ ቤት ሜዳ ነበርና ብርቱ ክቢያ ተከበን ታላቅ ፍርሃት ነበር፡፡ ውሃና መብልም አላገኘንም፡፡ በሦስተኛው ቀን ጊዜውም ስድስት ሰዓት ሲሆን አስራ ሰባት ሰዎች በውሃ ጥማቱ ሞቱ፡፡ ይህም ቀን ጨለመ፡፡ እህልና ውሃ ሳናገኝ ሦስተኛው ቀን ነበርና ገንዘብም እየተቀበሉ በኰዳቸው ጣሊያኖች ለእስረኞች ውሃ መሸጥ ጀመሩ፡፡

"ሕይወታችንም በዚህ ስቃይ ውስጥ ታንቃ ስንጨነቅ መሸ፤ እንጂ ለቀን ቀኑ ረጅም ነበር፡፡ ከዚያ ረሐብና ውሃ ጥማት እንዲገድሉን መርጠን ነበር፡፡ ይህንንም ከልክለውን ሁለት ካሚዮን አምጥተው ከዚህ ወደሚሰፋ እስር ቦታ ሊወስዱን እየቆጠሩ ስሙን እየፃፉ 30ውን አሳፈሩት፡፡ እንደተናገርኩት እኔ በጽህፈት ቤቱ በር አጠገብ ስለነበርኩ እስረኛውን አየቆጠሩ አያሳፈሩ መጓዝ የጀመሩ ከወዲያ በኩል ነበርና ስለዚህ የኔ መሄዴ ዘግይቶ ነበር፡፡ ብዙ የሚያሳዝን ቁም ነገሮች በመዘግየቴ አየሁ፡፡

"ሦስት ሴቶች በወሊድ ተጨንቀው ኖረዋል፡፡ ሊወልዱም ቦታ አላገኙምና በአስረኛው ግፊ ተጨፍልቀው ሞተዋል፡፡ ሦስቱም ከትንንሽ ህፃናቶቻቸው ጋር ሬሳቸው ወድቆ አየሁት፡፡ በውሃ ጥማትና በረሃብ እነርሱም በቦምብ ከገደሉት ከሞተው ሰውና ከሬሳው ብዛት የተነሳ እኒህን በወሊድ የሞቱትን ያስተዋላቸው አልነበረም፡፡ እኔንም ሊገድሉኘ ስሜን በሊስት ይዘው ይፈልጉኝ ነበርና ስሜን ፅፈው ሊያሳፍሩኝ ሲሉ ሌላ ስም ነገርኳቸው፡፡ በካሚዮንም እስረኛውን ወደወሰዱበት ስፍራ አጓዙን፡፡

"በመንገድም የካሚዮኑ መብራት በሚወድቅበት እንመለከት ነበር፡፡ መንገዱ ሁሉ ሬሳ ተሞልቶ ነበር፡፡ በገደሏቸው በሐበሾች ሬሳ ተሞልቶ ነበር፡፡ ዝም ብለው በላዩ ይነዱበት ነበር፡፡ በሬሳው ብቻ አይደለም፡፡ ነገር ግን ሬሳውን ደግሞ በካሚዮናቸው በጨፈለቁት ወቅት በሰው ሬሳ መንገዱ ተበላሽቶ ያስጸይፍ ነበር፡፡ ከመንገዱም ዳር የወደቁትን ሬሶች የካሚዮኑ ብርሃን በወደቀባቸው ጊዜ ድመቶች ጐንጫቸውን ነክሰው ጺማቸውን እያራገፉ ሲበሏቸው አየሁ፡፡"
ገጽ 94-95

ተመስገን ገብሬ ህይወቴ (ግለ-ታሪክ)

ክብር ለየካቲት 12 ሰማዕታት !!

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


እናንተ ጋር ስንት ነች?

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


ባጃጅ የሠራው የ8ኛ ክፍል ተማሪ

የ14 ዓመት ታዳጊና የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው አብዱልሃፊዝ ጸጋዬ የሚኖረው በጉራጌ ዞን ሙኽር አክሊል ወረዳ ነው።
የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች የሠራው አብዱልሃፊዝ እስካሁን ወደ አምስት የሚጠጉ የፈጠራ ሥራዎች መሥራቱንም ገልጿል። ከእነዚህም ውስጥ በኤሌክትሪክ እና በፀሐይ ብርሃን የሚሰራ ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ ይገኝበታል።

ከቴክኖሎጂው ጋር የተዋወቀው የሰባት ዓመት ልጅ እያለ መሆኑን የሚገልጸው የፈጠራ ባለሙያው÷ የመብራት እና የመኪና ፈጠራ እጅግ እንደሚያስደስተው ተናግሯል።
ታዳጊው ወደ ፈጠራ ሥራ የተሳበው ነገሮች እንዴት እንደሚሰሩ መጠየቅ እና መመራመር ስለሚወድ መሆኑንም ይገልጻል።

የታዳጊው እህት አምሪያ ጸጋዬ የወንድሟን የፈጠራ ሥራዎችን በተመለከተ በሰጠችው አስተያየት የመጀመሪያ ሥራው የምግብ ማቅረቢያ ትሪን እንደመሪ በመጠቀም በእንጨት እና በሌሎች ቁሳቁስ መኪና መስራቱን ታስታውሳለች። ከዛ በኋላ ግን በተለያዩ የትምህርት ቤት ውድድሮች ላይ እየተሳተፈ ማሸነፍ መቻሉን ትናገራለች።

አብዱልሃፊዝ ወደ ፈጠራ ሥራዎች የገባው በአካባቢው ያሉ እናቶችን ችግር በመመልከት በተለይም እናቶች ወደ ጤና ተቋም ለመሄድ የሚገጥማቸውን ውጣ ውረድ በአቅሙ መፍትሄ ለመስጠት እንደሆነም ገልጿል። ታዳጊው በፀሐይ ብርሃን የምትሄድ ባለሦስት እግር ወይም በተለምዶ ባጃጅ የምትባለውን ተሽከርካሪ፣ መለስተኛ አይሱዚ እና እሳት ማቀጣጠያ ከሠራቸው የፈጠራ ሥራዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

አብዱልሃፊዝ በፈጠራ ሥራዎቹ ምክንያት በወረዳ እና ዞን ደረጃ በተደረጉ የተለያዩ ውድድሮች ላይ በመሳተፍ ተሸላሚ መሆን ችሏል።
ወደ ፊት የሠራትን ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪውን ወደ ገበያ ለማውጣት እና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ድጋፍ እንዲደረግለትም ጠይቋል ።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


በአማራ ክልል ከ02/05/2017 እስከ 10/06/2017 ዓም በ1 ወር ከ በ9 ቀን በሹፌሮች በተሳፋሪወች ላይ የደረሱ ችግሮችን በዝርዝር

👉 29 ሹፌሮች እና ረዳቶች ታግተዋል
👉 6 ሹፌሮች ተገድለዋል
👉 1 ረዳት ተገድሏል
👉 3 ተሳፋሪዋች ተገድለዋል

👉በ02/05/2017 ከደብረ ታቦር ጋሳኝ ባለው የመንገድ ክፍል 5 ቦቴ ሾፌሮች ታግተዋል :;
👉በ 03/05/2017 በሀሙሲት እና ወረታ መሀከል አንድ ካሶኒ ሹፌር ተገድሏል:
👉 በ7/05/2017 ከመተማ ጎንደር በመጓዝ ላይ ባለበት ሂደት አውላላ አካባቢ በሽፍቶች በተተኮሰ ጥይት ሹፌሩ እና የ2 ተሳፋሪዎች ህይወት አልፏል::
👉በ 09/05/2017 ከ አጣዬ ወደ ማጀቴ ሽንኩርት ለመጫን እየሄደ በዘራፊወች ተገድሏል::
👉 በ12/05/2017 በሀሙሲት እና በወረታ መሀከል ጉማራ አካባቢ 2 የቦቴ ሾፌሮች ታግተዋል : :
👉በ12/05/2017 ከፍልቅልቅ እና ደጀን መሀከል ኩራር አካባቢ ሹፌር ታግቷል
👉 በ13/05/2017 መሽንቲ ከተማ አካባቢ 2 ሾፌሮች ታግተዋል መኪኖች አንዱ ሰሊጥ አንዱ በቆሎ የጫኑ ሲሆን መኪኖች በሌላ ሾፌር ተነድተው የት እንደተወሰዱ አልታወቀም::
👉በ13/05/2017 ከሳንጃ እና ሙሴባምብ መሀል አንድ የህዝብ ተሽከርካሪ ሾፌሩን እና ረዳቱን አፍነው ወስደዋል ::
👉 በ013 /05/2017 በሳንጃ እና አሸሬ ማህከል ከአሸሬ ወጣ ብሎ አንድ የካሶኔ ሾፌሩን በጥይት መተውታል ሆስፒታል ገብቷል::
👉በ14/05/2017 ከሳንጃ እና ፈንድቃ መሀከል አንድ የቤት መኪና ይዞ እየተጓዘ የነበረን ነጋዴ በጥይት ተገድሏል::
👉 በ15/05/2017 በሳንጃ እና በሙሴባምብ መሀከል 1 FSR ሾፌር ታግቷል
👉 በ 19/05/2017 አዳርቃይ ከተማ መግቢያ ላይ ልዩ ስሙ እንዞ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ 2 ካሶኒ የ2 Fsr ሹፌሮቹ እና ረዳቶቹ ታግተው ተወስደዋ ::
👉 በ19/05/2017 ዘይት ጭኖ ከባህር ዳር ወደ ጎንደት እየተጓዘ የነበረ አይሱዙ መኪና ከባህር ዳር ወጣ ብሎ ጎምባት አካባቢ ሹፌር እና ረዳቱን በማፈን መኪናውን ባህር ዳር ወስደው ጭነቱን አራግፈው አቁመውት ሄደዋል ::
👉 በ22 /05/2017 አባይ በርሀ ከድልድዩ ወደ ደጀን ባለው የመንገድ ክፍል ኩራር ዝቅ ብሎ ገልባጭ ሊሳን አስቁመው ሹፌሩ እሮጦ አመለጠ አብሮት የነበረውን ጓደኛውን አግተው ይዘውት ሄደዋል ::
👉27/05/2017 ከሶሮቃ እርጎየ ባለው የመንገድ ክፍል አንድ ሹፌር በዘራፊዎች ታፍኖ ሲወሰድ አንድ ተሳቢ በጥይት ሳልባቲዮው ተመቶ ሊያመልጥ ችሏል::
👉28/05/2017 ከጎንደር ደባርቅ ባለው የመንገድ ክፍል በወቅን እና በገደብየ መሀከል 2 የቦቴ ሾፌሮች ታፍነው ተወስደዋል ::
👉 29/05/2017 የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ሹፌር ሙሤባንብ እና ኩርቢ መካከል አግተው ወስደውታል
👉 በ 30/05/2017 ጎንደር -ደባርቅ መስመር ገደብየ አካባቢ የህዝብ መኪና አባዱላ ሹፌሩን አፍነው ወስደዋል::
👉 በ01/06/2017 በደብረ ታቦር እና ወረታ መሀከል በምትገኘው ወጂ ከተማ 1 አሽከርካሪ ሲገደል ረዳቱ ቆስሎ ባህር ዳር ፈለገ ህይወት ሆስፒታል ህክምና ላይ ገብቷል::
👉 በ06/06/2017 አሸሬ ከተማ ተገንጥሎ ዶጋው /ጭርክኝ/ የሚባል አካባቢ አንድ ሹፌር ታግቷል::
👉በ 05/06/2017 ከጎንደር እና መተማ መሀከል አውላላ በመባል የሚጠራ አካባቢ ላይ ከእነ ረዳቱ ተገድሏል ::
👉 በ07/06/2017 በሳንጃ እና አሸሬ መሀከል ፍልውሀ አካባቢ የህዝብ ተሽከርካሪ ለማገት ሲሞክሩ መኪናው ሊያመልጥ ሲሞክር አጋችች ጥይት በመተኮስ የአንድ ተሳፉሪን ህይወት አትጥፍተዋል ::
👉 በ10/06/2017 ከአዲስ ዘመን እንፍራዝ ሰብአ አካባቢ 2 ረዳት አንድ ሹፌር አግተው ወስደዋል ::

የሾፌሮች አንደበት

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library




ይህ መረጃ አሳዛኝም አስተማሪም ስለሆነ በፋስት መረጃ አቅርበነዋል።

ወጣቱ አረብ ሀገር የምትኖረዋን ልጅ በፌስቡክ ይተዋወቃል፣ ፍቅር ጀመሩ የእሱ ፍቅር አላስቀምጥ አላሰራ ብሏት ከስድስት ወር ትውውቅ በኋላ ወደ ሀገር ቤት መጣች።

ወደ ሀገር ቤት መጣች ተቀበላት ቦሌ ወረዳ 12 ቤት ተከራይቶ ገቡ፣ ይህ ሁሉ ሲሆን ቤተሰብ አያውቅም። በሚያሳዝን ሁኔታ በዛው ቀን ለእሱ ብላ የመጣችውን ፍቅረኛውን ገደላት።

ከገደላት በኋላ ሬሳዋን ጠቅልሎ ቤት ውስጥ ካስቀመጠ በኋላ ይዛ የመጣችውን ንብረት ይዞ ጠፋ። የእሱ አድራሻ እንዳይታወቅ አከራዮቹን «ፋይዳ መታወቂያ ላወጣ ስለሆነ እናንተ ጋር ያለውን መታወቂያ ኮፒ ስጡኝ» ብሎ ተቀብሎ እንደሄደ አከራዮቹ ይናገራሉ።
ከአንድ ሳምንት በኋላ አከራዮቹ ጥሩ ያልሆነ ሽታ በመኖሩ ለፖሊስ አመልክተው በሩ ሲከፈት ሬሳ ቤቱ ውስጥ ተገኘ።

እሱ ብቻ እንደተከራየ የሚያውቁት አከራዮች የሴት ሬሳ ቤት ውስጥ መገኘቱ ዱብ እዳ ነው የሆነባቸው። የተገኘው ሬሳ ለምርመራ ሆስፒታል ከገባ በኋላ ቤቱን የተከራየው ልጅ ሲፈለግ አንድ መንገድ ተገኘ።

የቤት ኪራይ በባንክ አስገብቶ ስለነበር ስልክ ቁጥሩ ተገኝቶ በጂፒኤስ ልጁ እዛው ሰፈር መጠጥ ቤት እየተዝናና ሊያዝ እንደቻለ ለፋስት መረጃ ጉዳዩን ያስረዱ ግለሰቦች ገልጿል።

ከተያዘ በኋላ ያደረገውን ሁሉ በዝርዝር እና በድርጊት በቦታው በመገኘት አሳይቷል።
ጉዳዩን አሳዛኝ የሚያደርገው የልጅቷ ቤተሰቦች ልጃቸው አረብ ሀገር እንዳለች ነው የሚያውቁት። #fastmereja

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

10k 0 21 8 104

የ2017 አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት ኦንላይን የመመልከቻ ሊንክ result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት ExitExam የሚለውን በመምረጥና የራስዎን User Name በማስገባት ውጤትዎን መመልከት ይችላሉ። #Exit_Exam_Result

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


በሰሜን ጎጃም ዞን ህጻን ያዘሉ ሴት አስተማሪዎችን ጨምሮ 13 መምህራን “በፋኖ ታጣቂዎች” መታገታቸውን ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ

በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ጎንጂ ቆላላ ወረዳ ኮሬ ጣንክሪ ቀበሌ በሚገኝ ኮሬ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት በማስተማር ላይ የነበሩ 13 መምህራን “በፋኖ ታጣቂዎች” ረቡዕ የካቲት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ታግተው መወሰዳቸውን የታጋች ቤተሰቦች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ። ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸውን እንዳንጠቅስ የጠየቁ አንድ የታጋች ቤተሰብ ልጆቻቸውን የያዙትን ጨምሮ 8 ሴት እና 5 ወንድ በአጠቃላይ 13 መምህራን የካቲት አምስት ቀን ከጠዋቱ 2:20 አከባቢ “በባጃጅ በመጡ ታጣቂዎች” መወሰዳቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።

ቀደም ብሎ በአከባቢው በሚንቀሳቀሱት “የፋኖ ታጣቂዎች” ት/ቤቶች እንዳይከፈቱ መመሪያ አስተላልፈው እንደነበር ያስታወሱት ነዋሪው በመንግሥት በኩል ደግሞ መምህራንም ት/ቤት እንዲገኙና የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዲቀጥል ካልሆነ ግን የወር ደመወዛቸው እንደማይከፈላቸው በመገለጹ ምክንያት መምህራኑ ከጥር 12 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በት/ቤቶቹ መገኘታቸውን ጠቁመዋል።

“መምህራን ካልሰራችሁ አይከፈላችሁም ተብለው ጥር 12 ወደ ት/ቤት ተመልሰዋል። እነሱም ለማስተማር ሳይሆን ዝምብለው እየፈረሙ ነበር የሚወጡት። ጥር 20 ጀምሮ ግን ክፍል ገብታችሁ ማስተማር አለባችሁ ተብለው ከአንዲት መምህርት ውጭ እና የጥር ወር ሙሉ ደመወዝ የተከፈለው መምህርት የለም። ሌሎች መምህራን ፈርመው ብቻ ሲወጡ ስለነበረ ከግማሽ በታች የወረደ ደመወዝ ተከፈላቸው። ከዛ ስጋት ቢኖርም ከየካቲት ወር ጀምሮ ክፍል እንግባ ብለው ተማክረው ገቡ” ብለዋል።

መምህራኑ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆነው የመማር ማስተማር ሂደቱ በቀጠለበት ሁኔታ ረቡዕ ማለዳ ላይ ታጣቂዎች መምህራኑን አግተው መውሰዳቸውን የታጋች ቤተሰቡ ተናግረዋል። አክለውም ታጣቂዎቹ “ስርዓቱን ተቃውመን እየታገልን እናንተ ለምን ታስተምራላችሁ” በሚል በነፍስ ወከፍ እያንዳንዳቸው ሀምሳ ሺህ ብር ቅጣት እንዲከፍሉ ካልሆነ ግን እንደማይለቀቁ አስጠንቅቀዋል ብለዋል።

“እነሱን (ታጋቾችን) ፍለጋ በርሃ ድረስ ተንከራተናል። ልናገኛቸው አልቻልንም። የሚገርምው ከታገቱት ውስጥ የሁለት ዓመት እና ዓመት ያልሞላው ህጻን ያዘሉ አሉ። እንግዲህ ከነልጆቻቸው ማንገላታት ማለት ምን ማለት ነው? እንዳጠቃላይ አስተምሩ ከተባለ ምንድን ነው ማስተማር ክፋቱ?” ያሉት እኚሁ ግለሰብ አያይዘውም ምንም “የፖለቲካ ፍላጎት የሌለው ባለሙያ ምን ያድርግ? ሙያተኛ አድርግ ከተባለ ያደርጋል ተው ከተባለ ይተዋል በቃ ፈጻሚ እንጂ አስፈጻሚ አይደለም።” ሲሉ ገልጸዋል።

አሁን ላይ በወረዳው ከሚገኙ ከ64 በላይ ት/ቤቶች መካከል ሁለቱ ማለትም ጎንጂ እና ኮሬ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ብቻ መከፈታቸውን ገልፀው “ታሪክ ነው የምታየው። አዲስ ነገር ነው የሆነብን። ለማን እንደምንጮህ ግራ ገብቶን ከባድ ጊዜ ለማሳለፍ ተገደናል።” ሲሉ በምሬት ተናግረዋል።

በተጨማሪም በአሁኑ ሰዓት ከአንድ ቀበሌ በስተቀረ አከባቢው ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ በ”ፋኖ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር” መሆኑን አመልክተዋል። ሌላኛው ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ እና ታግተው ከተወሰዱ መምህራን ውስጥ ልጃቸው እንደምትገኝ የገለጹ አንድ የታጋች ወላጅ አባት በበኩላቸው በልጃቸው መወሰድ ለከፍተኛ ስጋት እና ሃዘን መዳረጋቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።

ልጃቸው እርሳቸው በሚኖሩበት በምስራቅ ጎጃም ዞን ሰዴ ወረዳ ሙጃ ቀበሌ ከርማ እንደነበረ የገለጹት እኚሁ አባት ትምህርት አስተምሩ መባሉን ተከትሎ አንድ ልጇን አዝላ ወደ ጎንጂ ቆለላ ወረዳ በሚገኘው ኮሬ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት መሄዷን ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ ልጃቸው በዛው ዕለት ማለትም ረቡዕ የካቲት 5 ቀን 2017 ዓ.ም መታገቷንና ይህንንም በእጅ ስልካቸው ተደውሎ እንደተነገራቸው ገልጸዋል። አክለውም ለማስለቀቂያ 50ሺህ ብር እንደተጠየቁ ገልጸው “እኔ እንኳን 50 ሺህ አምስት ብር የለኝም” ሲሉ ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል።

“ልጄ ድምጿ ናፍቆኛል። ትጦረኛለች ያልኳትን ልጄን ነው የወሰዱብኝ። ሳትሰራ እንዴት ራሷን ታስተዳድራለች? የምትደጉመኝ የምትረዳኝ እያሰበች በርበሬውን ሽሮውን አዘጋጅታ የምመገብ በሷ ላይ ነበረ። ምን ላድርጋት እኔ ጉልበት የለኝ አልደርስላት ነገር።” ያሉት እኚሁ የታጋች ወላጅ አባት አክለውም” ዘንድሮ አቅቶናል። ሁሉም በፍርሃት ውስጥ ነው ያለው። የሚሰማን ነው ያጣነው።” ሲሉ ስለሁኔታው አብራርተዋል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት በሰሞኑ ጉባኤው ላይ ትምህርት ላይ ያለው ችግር ከፍ ያለ እንደኾነ ገልጿል። ለዚህም እንደ ማሳያ በ2017 የትምህርት ዘመን 3 ሺህ 736 ትምህርት ቤቶች በክልሉ አለመከፈታቸውን ገልጿል። በተጨማሪም ከ30 ሺህ በላይ መምህራን እና የትምህርት ቤት መሪዎች ወደ ትምህርት ቤታቸው ተገኝተው የመማር ማስተማር ሥራ ማከናወን አልቻሉም ብሏል፡፡ ይህም የክልሉን የትምህርት ተሳትፎ አፈጻጸም 40 መቶ እንዲኾን አድርጎታል ሲል ገልጾ ክልሉ ከሌሎች ክልሎች ጋር ያለውን ተወዳዳሪነት ጥያቄ ውስጥ ጥሏል ሲል ገልጿል።

በአማራ ክልል በመንግሥት የጸጥታ አካላት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በመካሄድ ላይ ያለውን ግጭት ተከትሎ በክልሉ በሚገኙ መምህራን ላይ እየደረሱ ስላሉ እንግልቶች በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል።

ለአብነትም በክልሉ ምስራቅ ጎጃም ዞን ስናን ወረዳ ረቡዕ ገበያ ከተማ ሁለት መምህራን መስከረም 8 ቀን 2017 ዓ.ም “በታጠቁ ኃይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን” የዞኑ አስተዳደር ማስታወቁን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል። በወቅቱ የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር ባወጣው የሃዘን መግለጫ፤ ግድያ የተፈጸመባቸዉ መምህራን በረቡ ገበያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በመምህርነት ሙያ ሲያገለግሉ የነበሩት መ/ር ጌታ እንዳለ አንማው እና መ/ር አትንኩት ሁነኛው ናቸዉ ብሏል።

በተጨማሪም “በታጠቁ ኃይሎች መምህራኑ በአሰቃቂ ሁኔታ ግድያ የፈጸሙባቸዉ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር እንቅስቃሴ አድርጋችኋል፤ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ዉስጥ ለምን ትገባላችሁ? ወዘተ… በሚል ነዉ” ሲል አስተዳደሩ ገልጿል።

መረጃው የአዲስ ስታንዳርድ ነው

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


የ500 ብር ከጅምላ አከፋፋይ አምጥቶ በ2700 ብር የሚሸጥ ነጋዴም አለ። ዘይገረም ነው ።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


የዛሬ ስንት ዓመት እንደሆነ ባላስታውስም የአፍሪካ ኅብረት ዓመታዊ ''ስብሰባ'' ሰሞን የ_______ ኮሙኒቲ ሰልፍ በመውጣት ''ድምጽ ለማሰማት'' ጥረት አድርገው ነበር።

በወቅቱ የኢት. ኦርቶዶክስ ተ/ቤ/ክ ፓትርያርክ የነበሩት ብጹዕ ወ ቅዱስ አቡነ ጳውሎስ (ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቀነጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ወ እጨጌ ዘ መንበረ ተ/ኃይማኖት ሊቀ-ጳጳሳት ዘአክሱም የዓለም አብያተ-ክርስትያናት ፕሬዝዳንት) ከፍተኛ ጥረት እንዲሁም በመንግሥት ድጋፍ እንዲከሽፍ ተደረገ።

ከዚያም በኋላ በተሠሩ ሥራዎች ቢያንስ በአደባባይ እንዳያንሰራራ ሆኖ ነበር።

ብዙ ነገር የልምምድ ውጤት ነው። በ ''ሰለጠኑት'' ሀገራት የጾታ ውዝግብ እና የወ*ሲብ ዝንባሌ ('Sexual Orientation') ዝብርቅርቅ እንዲሁ በአንድ ጀንበር የመጣ አይደለም። በግልጽና በስውር ብዙ ''ለፍተውበት'' እና አለማምደው ነው እዚህ ያደረሱት።

እንደ ሀገር ከተለያየ አቅጣጫ የሚደርስብን ጫና (በተለይ በእርዳታ ስም) እንዳለ ሆኖ አሁን አሁን በጣም የሚያሳስበው መረን በወጣ ንግግራቸው ወይም የፌስቡክ ልጥፋቸው ከፍተኛ አድናቆት እየተቸሩ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዋ*ልጌ ሴቶች እየተበራከቱ መምጣታቸው ነው።

አብዛኞቹ ኢትዮጵያ እንደማይኖሩ ልብ ይባል። እነዚህን ሴቶች ፕሮፋይላቸውን ስትመረምሩ almost ሁሉም 30ዎቹን የተሻገሩ፣ ልጅ የሌላቸው ወይም ትዳር ያልመሠረቱ ሆነው ታገኟቸዋላችሁ። ከስር የሚያሸበሽቡት/የሚያዳንቁት አብዛኞቹ ደሞ ትዳር የመሠረቱ እና ልጆች ያሏቸው ''አባ ወራዎች'' ናቸው።

ዛሬ መቃወምና መግራት ተስኖህ ስታለ'ቀልቅ እና ስታለማምድ ባጅተህ ነገ ልጅህ ከሴትም ከወንድም ጋር ሲ*ዳራ ወይም ሴቷ ልጅህ ከዚህም የከፋ ነገር ውስጥ ስታገኛት ብዙም እንዳትደነግጥ! አንተ አባትየው በልምምዱ ውስጥ የራስህን ''አሻራ'' ያኖርክ መሆንህን እንዳትረሳው!

Hawlet Ahmed

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


የተባበሩት አረብ ኢምሬት የሰለጠኑ ኢትዮጵያዊያንን የመቅጠር እቅድ እንዳላት ገለጸች

ዓለም አቀፉ የሰራተኞች ድርጅት (አይኤልኦ) እንደገለጸው ከሆነ በተባበሩት አረብ ኢምሬት ከ100 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊን ይኖራሉ፡፡ ከነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥረው የሚሰሩ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የሰለጠኑ ኢትዮጵያዊያን ወደ አረብ ኢምሬት ከተሞች እየሄዱ እና እየተቀጠሩ ይገኛሉ፡፡

የተባበሩት አረብ ኢምሬት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደገለጸው ከሆነ በቀጣይ ከቤት ሰራተኞች በተጨማሪ በተለያዩ ሙያዎች የሰለጠኑ ኢትዮጵያዊንን የመቅጠር እቅድ እንዳለው አስታውቋል፡፡ በሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የልማት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሚኒስትር ሱልጣን አል ሻምሲ በአዲስ አበባ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

ሚንስትሩ በጉብኝታቸው ወቅት ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቃለ መጠይቅ እንዳሉት “በዩኤኢ ከተሞች ብዙ ኢትዮጵያዊያን አሉ፡፡ በቀጣይ በቱሪዝም፣ ሆቴል፣ ቴክኖሎጂ እና ንግድ ሙያ ዘርፎች የሰለጠኑ ኢትዮጵያዊንን የመቅጠር እቅድ አለን” ብለዋል፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

20 last posts shown.