Ethiopian News 24 ኢትዮጵያ ዜና 24


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


ኢትዮጵያ ዜና 24 || ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ
ተአማኒ እና ትክክለኛ መረጃዎችን በፍጥነት የምታገኙበት ልዩ የኢትዮጵያውያን ቻናል ነው።
🇪🇹ወቅታዊ መረጃዎች
🇪🇹ልዩ ልዩ ዘገባዎች
🇪🇹መዝናኛ ዜናዎች
🇪🇹ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል
ሀሳብ፣አስተያየት ካላችሁ
👇 👇
@Ethiopia_newsbot
የፌስቡክ ገጻችን
👇
www.fb.com/ethiopianews24
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


ፈጣሪ ሀገራችንን ሰላም እስኪያደርግልን ድረስ ዜና መጻፍ አቁመናል።
ለጊዜው ደህና ሁኑ።


ፎቶ : የጅማ ኤርፖርት መደበኛ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ላይ ነው። ኤርፖርቱም አልተዘጋም።

በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በኤርፖርቱ ፍንዳታ እና አደጋ እንዳጋጠመ ፤ ኤርፖርቱም እንደተዘጋ የሚናፈሰው ወሬ ሀሰት ነው።

ጅማ ኤርፖት ፍንዳታ ደረሰ እያሉ ሲያሰራጩ ከነበሩት መካከል የውጭ ሀገራት ሚዲያዎች እንዲሁም ውጭ ሀገር ሆነው በኢትዮጵያ ጉዳይ የሚፅፉ የማህበራዊ ሚዲያዎች ይገኙበታል።

ይህንን ሀሰተኛ መረጃ በርካቶች ሲያጋሩት ነበር።

የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ካሳሁን ጎፌ ድርጊቱ ከእውነት የራቀ እና የሃሰት ዜናዎችን በመዘገብ ህብረተስቡን ማሸበር እና ስጋት ማጫር የሚፈልጉ አካላት ሴራ ነው ያሉት ሲሆን ሁሉም አካል መደበኛ የትራንስፖርት እንቅስቃሴውን እንዳያስተጏጉል አሳስበዋል።

Photo Credit : Kominikeeshinii Magaalaa Jimmaa


"በጅማ ኤርፖርት ፍንዳታ አልደረሰም፤ በረራም አልቆመም" - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

በአንዳንድ የማህበራዊ ትስስር ገፆች በጅማ ኤርፖርት ፍንዳታ እንደደረሰና በረራም እንደቆመ ተደርጎ የሚናፈሰው ወሬ #ፍፁም_ሐሰት መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አረጋግጧል።

በአሁኑ ሰዓት በጅማ መደበኛ የኤርፖርት እና የበረራ ስራዎቻችን በተለመደው መልኩ እየተከናወኑ ይገኛሉ ሲልም አየር መንገዱ አሳውቋል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ


#Metekel : በሀገር መከላከያ እና ፌዴራል ፖሊስ ስልጠና የተሰጣቸው 265 ሚሊሻዎች ዛሬ ተመረቁ።

ዛሬ የተመረቁት ሚሊሻዎች የመተከልን ሰላም ለመመለስ ሲስለጥኑ የቆዩ እንደሆኑ ተገልጿል።

በአካባቢው የሚገኛው ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ኮ/ል መልካሙ በየነ ፥ መከላከያ ሰራዊት እና በፌዴራል ፖሊስ አማካኝነት ህብረተሰቡ ራሱን እንዲከላከል እና ፀረ ሰላም ሃይሎችን ለህግ አሳልፎ እንዲሰጥ አስፈላጊው ወታደራዊ ስልጠና ተሰጥቷል ማለታቸውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ይፋ ባደረገው መረጃ አሳውቋል።


#Assosa : በአሶሳ ከተማ የጋሪ-ዎሮ የቦሮ-ሽናሻ የዘመን መለወጫ በዓል ተከበረ።

በበዓሉ የብሔረሰቡ ባህላዊ ቱፊቶች የሚንጸባረቁበት፣ አዛውንት እስከ ህጻናት በጋራ ተሰባስበው የሚያከብሩት በዓል ነው።

የብሔረሰቡ አባቶች መጪው ዘመን የሠላም፣ የጤና፣ የአብሮነትና የአንድነት ዘመን እንዲሆን መርቀዋል።


#Debark : የመስቀል በዓል በደባርቅ ተከበረ።

በበዓሉ የስሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኂሩያን እስጢፋኖስ ጥፍጤ፣ የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሰለሞን ተዘራ፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ የሃይማኖቱ ተከታዮች በተገኙበት ነው የተከበረው።

የፀሎት ስነ ስርዓት ተካሂዶ ደመራው 5:30 በሀይማኖት አባቶች ፣ በሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ክቡር ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ሰለሞን ተዘራና የባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ችሎት ተቀባ በተገኙበት ተለኩሷል።

Credit : Debark Communication


" ... የእኛ ሰላምና እርቅ በየጊዜው እለት እለት ልንፈጽመው የሚገባን ተግባር መሆን አለበት " -  ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በዛረው በበዓል ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በዛሬው ዕለት የምናከበው በዓለ መስቀል የእግዚአብሔር ሰላምና እርቅ ፍለጋ በብርቱ የተንቀሳቀሰችው ታላቋ ክርስቲያናዊት ንግሥት ዕሌኒ የፈጸመችውን የቅድስና ተግባር እና ያስገኘቸውን ሃይማኖታዊ ስኬት መነሻ አድርገን ከእግዚአብሔር ጋር ለመታረቅ ነው ብለዋል። 

ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሲል በመስቀሉ ላይ ተሰቅሎ የሰውን ልጅ መርገመ ሃጢያት እንዲወገድ በማድረግ ሰው ወደቀደመ ቦታው ገነት እንዲገባ ምክንያት መሆኑን የገለጹት ቅዱስነታቸው በዚህም ምክንያት መስቀል ከሁሉም በላይ ነው ሊባል መቻሉን ገልጸዋል።

የእኛ ሰላምና እርቅ በየጊዜው እለት እለት ልንፈጽመው የሚገባን ተግባር መሆን አለበት ያሉት ቅዱስ ፓትርያርኩ አንገታችን ላይ ያለው መስቀል ጌጥ ሳይሆን በእግዚአብሄር እና በሰው፣ በእኛ እና በስነፍጥረት መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያስረዳ በመሆኑ ልንጠብቅበት ይገባል ካሉ በኋላ በዓለም ላይ ሰላም ፍቅር እና አንድነት እንዲሰፍን ጠንክረን እንስራ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ 

ያንብቡ : telegra.ph/MESKEL-09-26-2


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ሁሉ፣
እንኳን ለመስቀል በዓል አደረሳችሁ!

መልካም በዓል!


ፎቶ : የመስቀል ደመራ በዓል እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝበ ክርስቲያን በተገኘበት በፍፁም ሰላም ተከብሯል።

ከአደባባይ በዓላት መካከል አንዱ የሆነው መስቀል ደመራ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ባለፈው ዓመት እጅግ በጣም በውስን ተሳታፊዎች መከበሩ አይዘነጋም።

ፎቶ : አዲስ አበባ - መስቀል አደባባይ (2014 ዓ.ም)


በተሽከርካሪ አደጋ የ8 ሰዎች ሕይወት አለፈ።

በምዕራብ ሸዋ ዞን ኤጀርሳ ለፎ ወረዳ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የስምንት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።

የኤጀርሳ ለፎ ወረዳ ትራፊክ ፖሊስ ተቆጣጣሪ ዋና ሳጂን ፍቃዱ ሙሉጌታ እንደገለጹት አደጋው የደረሰው ትላንት ማምሻውን በወረዳው ለገ ሁሉቆ በተባለ አካባቢ ነው።

ከአዲስ አበባ ወደ ጊንጪ ሲጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3– 30485 ኦሮ የሆነ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ከአምቦ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ ከነበረ ኮድ 3 –52989 ኦሮ የህዝብ ማመላለሻ ቅጥቅጥ አይሱዙ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ አደጋው መድረሱን ተናግረዋል።

በአደጋው የሚኒባሱ አሽከርካሪን ጨምሮ ሚኒባሱ ውስጥ የነበሩ የ8 ሰዎች ህይወት ወዲያው ማለፉን ተናግረዋል።

በሚኒባሱ እና በአይሱዙ ተሸከርካሪ ውስጥ የነበሩት ጉዳት የደረሰባቸው ስድስት ሰዎች በጳውሎስ ሆሲፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

በአደጋው ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች አስከሬን ለየቤተሰቦቻቸው መሰጠቱን የገለጹት ዋና ሳጂን ፍቃዱ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም ማስታወቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።



11 last posts shown.

1 595

subscribers
Channel statistics