EFDA የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Medicine


ETHIOPIAN FOOD AND DRUG AUTHORITY /EFDA/
This is EFDA'S official Telegram Channel
For more updates please visit
Free call 8482
join the Channel
t.me/ethiopianfoodanddrugauthority

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Medicine
Statistics
Posts filter














የህክምና መሳሪያ ደህንነት ጥራትና ውጤታማነት ጉድለቶችን በተቀናጀ መልኩ ሪፖርት ማድረግ የቁጥጥር ስራን እንደሚያሳልጥ ተገለፀ ፡፡

ታህሳስ 25/2ዐ17 ዓ.ም አዳማ፡- የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የህክምና መሳሪያ ደህንነት፣ ጥራትና ውጤታማነት  ቁጥጥር ሪፖርት አደራረግ ላይ ከአዲስ አበባ ለተውጣጡ የጤና ባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
ስልጠናውን የከፈቱት  በባለስልጣኑ የህክምና መሣሪያዎች ም/ዋና ዳይሬክተር  ዶ/ር ሻርማርኬ ሸሪፍ እንደተናገሩት ተቋማችን የህክምና መሣሪያዎች ወደ ሃገር ሲገቡ የደህንነት፣ ጥራትና ውጤታማነት ቁጥጥር ያደርግባቸዋል፡፡ሆኖም በአገልግሎት ላይ በሚውሉበት ጊዜ የተለያዩ የጎንዮሽ ጉዳት ይኖራቸዋል፡፡ ይህንን የጎንዮሽ ጉዳት በየደረጃው ያሉ የጤና ባለሙያዎች ሪፖርት ካላደረጉ ማወቅ አይቻልም፡፡ በመሆኑም የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ መናበብ እና በጋራ መስራት ስለሚያስፈልግ ስልጠናውን በተግባር ላይ እንዲያውሉ አደራ  ብለዋል፡፡ 

ስለ ስልጠናው ያብራሩት የባለስልጣኑ የህክምና መሣሪያ አምራች ኢንስፔክሽን መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ሚኪያስ ጴጥሮስ እንደተናገሩት የህክምና መሣሪያ ደህንነት፣ ጥራትና ውጤታማነት  ቁጥጥር  በአገራችን ያልተጠናከረና ያልተደራጀ መሆኑን ጠቁመው ከዚያው ጐን ለጐን በባለሙያዎችም እንከኖች ሲገኙ ሪፖርት ማድረግ ያልተለመደ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የጤና ግብአት ቁጥጥሩን ለማዘመንና የህብረተሰባችንን ጤና ለማስጠበቅ የተደራጀና የተቀናጀ የህክምና መሣሪያ ደህንነት ጥራትና ውጤታማነት  ጉድለት ሪፖርት ማድረግን እንደ ሃገር መተግበር የዚህ ስልጠና ዋና አላማ እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡


ከአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ጋር  አብሮ መስራት የምግብ  ጥራትንና ደህንነትን  ለማስጠበቅ  ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ፡፡

ታሃሳስ 23/2017 አዲስ አበባ፦  የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን  ከኦሮሚያ  ኢንዱስትሪ ፓርክ የልማት ኮርፖሬሸ(OIPDC)ን ጋር የምግብ  ጥራትንና ደህንነትን  ለማስጠበቅ የጋራ መግባብያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡ በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሔራን ገርባ እንደተናገሩት የምግብ ጥራትና ደህንነት ማስጠበቅ ዋና ተግባራችን  እንደመሆኑ  ተቋማችን የምግብ አግሮ ኢንቨስትመንቶች ከመሰረቱ ጀምሮ የተሻለ ደህንነትና ጥራት ኖሯቸው ምርታቸውን እንዲያመርቱና  ለገበያ እንዲያቀርቡ እንደግፋቸዋለን፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ኢንቨስተሮች መዋለ-ንዋያቸውን በምግብ አግሮ-ፕሮሰስ ላይ እንደያፈሱ  በማበራታታት የማሰተናገድ አቅማችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሳደግን  ለአገር ኢኮኖሚ ዕድገት የበኩላችንን  እያተወጣን  አንገኛለን ያሉ ሲሆን ፊርማውም ከወረቀት አልፎ ተግባራዊ  ይሆናል ሲሉ ተነግረው ሁሉም የአግሮ ፕሮሰሲንግ ፓርኮች የምግብ ጥራት ምርመራ ላብራቶሪ እንዲያደረጁ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡

የኦሮሚያ አግሮ ፕሮሰሲንግ እንዱስትሪ ፓርክ ምክትል ስራ አሰኪያጅ አቶ መንግስቱ ረጋሳ  በበኩላቸው  ከኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ጋር  ለመስራት በመፈራራማችን  ለስራችን መቃናት ግማሽ መንገድ  የተጓዝን ያህል ይሰማናል ያሉ ሲሆን ከህዳሴ ግድብ በመቀጠል ብዙ  ገንዘብ  የሚፈስበት ዘርፍ ኢንዱስተሪ ፓርክ  ነው ያሉት ምክትል ስራ አስኪያጁ የባለሀብቶች ጥያቄ ላመረቱት የምግብ  ምርት የገበያ ፈቃድ ማግኘት ነው፤ በመሆኑም ከተቋሙ ጋር ስንሰራ  የምግብ ጥራትና ደህንነትን  በማስጠበቅ ሁሉንም ባለድርሻ አከላት ተጠቃሚ እናደርገለን ሲሉ ተነግረዋል፡፡


ኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ከUSPQM ፕላስ ጋር በመተባበር ከክልል ተቆጣጣሪ አካላት ጋር የአንድ ቀን አውደ ጥናት አካሄደ።

የዚህ የምክክር አውደ ጥናት የክልል ተቆጣጣሪ አካላት ከታንዛኒያ እና ዚምባብዌ ተቆጣጣሪ ባለስልጣናት ጋር በተደረገው የልምድ ልውውጥ ውጤት ላይ ለመወያየት እና የጥራት አስተዳደርን በክልል ተቆጣጣሪ አካላት ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ እቅድ የነበረውና በ2025 የመጀመሪያ ወራት ውስጥ በአለም ጤና ድርጅት ለማቹሪቲ ሌቭል ሶስት ይፋዊ የቤንችማርኪንግ ግምገማ ዝግጅት በመገምገም በክልል ተቆጣጣሪዎች በኩል የተገኘውን ልምድ በመቀር ቀሪ ስራዎችን  ለማጠናቀቅ የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።


የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 የአቅመ ደካማ ነዋሪ ቤት አድሶ አስረከበ
ታህሣሥ 22/2017 ቀን  ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከተቋቋመበት ዓላማ በተጨማሪ ማህበራዊ ግዴታን ለማገዝ በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎችን ሲሰራ የከረመው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የዚሁ ስራ አንድ አካል የሆነው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የሚገኝን ቤት በማደስ ለባለቤቱ አስረክቧል
በቤት ርክክቡ ወቅት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሔራን ገርባ እንደተናገሩት ይህ ቤት በ2 ወራት ውስጥ ታድሶ ለነዋሪዋ ወይዘሮ ስንታየሁ ባህሩ ለማስረከብ ባለስልጣኑ ከግርማ ገብረስላሴ ህንፃ ተቋራጭና ከወረዳው ስራ አስፈፃሚ ተቀራርቦ ሲሰራ መክረሙን ገልፀዋል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መንግስት በአዋጅ ከሰጠው መንግስታዊ ኃላፊነት ጎን ለጎን ማህበረሰቡን ለመደገፍ በቂርቆስ ወረዳ 02  ለሚገኙ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ፣ በጋሞ ጎፋ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት የመድኃኒትና የህክምና መሳሪያዎች፣ ለመከላከያ ሠራዊት የመድኃኒትና የህክምና መሳሪያዎች ድጋፍ ማድረጉን ገልፀው የባለስልጣኑ ሠራተኞችና አመራሮች ከደመወዛቸው ተቆራጭ በማድረግ የሚያደርጉት ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል  ጠቁመው ታድሶ ለመኖሪያነት ምቹ የሆነውን ቤት ለወይዘሮ ስንታየሁ ባህሩ በዛሬው ዕለት አስረክበዋል፡፡
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ስራ አስፈፃሚ አቶ አበራ አለሙ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በየጊዜው በወረዳው የሚገኙ ነዋሪዎችን ለመደገፍ እየሰራ ያለው ስራ ለሌሎች ተቋማትም ምሳሌ እንደሚሆን ተናግረው ቤቱ በዚህ ደረጃ ታድሶ ለነዋሪዋ በመሰጠቱ በስራው የተሳተፉትን ሁሉ ያመሰገኑ ሲሆን ቤቱን በተገቢው ጥራት አድሰው ለዚህ ያበቁት ግርማ ገብረስላሴ ህንፃ ተቋራጭን በራሳቸውና በሚመሩት ወረዳ ስም አመስግነዋል፡፡


ለባህል መድኃኒቶች የገበያ ፈቃድ ለመስጠት የሚያስችል ጥናት ሪፖርት ቀረበ

ታህሳስ 22/2017 ዓ.ም፡- ኢትዮጵያ ለባህል መድኃኒቶች ግብዓት የሚሆኑ በርካታ እፅዋቶች እንዳሏት ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ እነዚህን የባህል መድኃኒቶች ጊዜውና ወቅቱ በሚጠብቀው መልኩ በማምረት ለታካሚዎች ለማድረስ ይቻል ዘንድ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ሰፊ ጥናት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

የተደረገውን ጥናት ለሚመለከታቸው አካላት ለማቅረብ በአዳማ ከተማ በተዘጋጀው መድረክ ላይ አቶ ፈየራ ሌጂሳ ከባለስልጣኑ የቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ማስተባበሪያ እንደተናገሩት የባህል መድኃኒቶች ለሐገሪቱ የጤና ስርዓት ሊኖራቸው የሚገባውን ሚና ግንዛቤ በመውሰድ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መድኃኒቶቹ ተገቢውን መስፈርት አሟልተው የሚመዘገቡበትን ሁኔታ እያመቻቸ ሲሆን በቅርቡም በይፋ ወደስራ እንደሚገባ ገልፀው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ይህንን ከግንዛቤ በማስገባት ያላለሰለሰ አስተዋፆ ለማበርከት ጠንካራ አቋም እንዲወስድ እና ሴክተሩን በጋራ ለህብረተሰቡ ጥቅም ማዋል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የጥናቱን ውጤት ያቀረቡት አቶ ዳዊት ዲቃሶ በበኩላቸው የባህል መድኃኒቶች የባለስልጣን መ/ቤቱን የምዝገባ ስርዓት ተከትለው እንዲመረቱና እንዲመዘገቡ ያስቻለ ጥናት ሲካሄድ መቆየቱን ጠቅሰው ይህ መድረክም ወደተግባር ከመገባቱ በፊት የሚመለከታቸው አካላት ግንዛቤ እንዲወስዱ የተዘጋጀ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ከሚመለከታቸው የፌዴራል መ/ቤቶች፣ የባህል ህክምና ማህበር ተወካዮች፣ የክልል ተቆጣጣሪዎች እና የመድሀኒት አምራቾች ጋር በተደረገው ውይይት መሰረት እያንዳንዳቸው ሊያበረክቱ የምችሉትን አስተዋጾ በማቀናጀት የተሻለ የባህል መድኃኒት ለመጠቀም እንዲያስችል ታስቦ የማጠቃለያ ሀሳብ ለተሳታፊዎች ተገልጾ ወይይት ተደርጎበታል።




የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የማኔጅመንት አባላት እየተሰሩ ያሉ የሪፎርም ስራዎች እና በተዘጋጁ ሰነዶች ዙሪያ ውይይት አካሄዱ።

ታህሳስ 19/2017 አዲስ አበባ፡- የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ማኔጅመንት አባላት ባለስልጣን በጤናው ዘርፍ የምግብና ጤናግብዓት ቁጥጥር ዘርፍ የአገልግሎትና አስተዳደር ለማሻሻል በተዘጋጁ ሰነዶች ፣እስካሁን በተሰሩ የሪፎርም ስራዎች ዙሪያ ለሁለት ቀናት ባካሄዱት ውይይት ላይ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሔራን ገርባ እንደተናገሩት የቁጥጥር ስራውን ማጠናከር የሚቻለው የአገልግሎትና አስተዳደር ማሻሻያ ሪፎርሙን በሚፈለገው ደረጃ በመተግበር ከዘመኑ ጋር አብሮ የሚሄድ አሰሪ የሆነ አደረጃጀት መፍጠር ሲቻል መሆኑን በመግለፅ የማኔጅመንት አባላቱ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ራዕይ ሊያሳካ የሚችልና ወቅቱን ያገናዘበ የስራ መዘርዝር ማዘጋጀት እንዳለባቸውና ከዚህ ቀደም የተዘጋጁትም በጥልቀት መታየት እንዳለባቸው አስታውቀዋል፡፡

የተዘጋጁ የሪፎርም ሠነዶች በባለስልጣኑ የሠው ኃብት ልማት አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ አቶ ሠለሞን አምዴ እና የሪፎርም ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት የቀረበ ሲሆን የማኔጅመንት አባላቱ በቀረበው ሠነድ ላይ ከፍተኛ ውይይት አካሂደዋል፡፡ ጠንካራ ተቆጣጣሪ አካል ለመፍጠር ለሚደረገው ጥረት ሪፎርሙ ትልቅ ጉልበት ይሆናል ተብሎ የሚገመት ሲሆን የስራ ክፍሎች የተዘጋጀው ሠነድ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እየሰራቸው ካሉና ወደፊት ሊሠራቸው ካቀዳቸው ተግባራትና መንግስት በአዋጅ ከሠጠው ስልጣን ጋር በማጣጣም እንዳለበት በበላይ አመራሩ አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡



14 last posts shown.