Champion sport ቻምፒዮን ስፖርት


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Sport


ስፖርታዊ መርጃወችን እና የስፖርቱ አለም ድንቅ ትውስታዎች
#በድምፅ እና
#በፅሁፍ

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Sport
Statistics
Posts filter


🔵የብራይተኑ አሰልጥኝ ግርሃም ፖተር ቀጣዩ የቼልሲ አሰልጣኝ ለመሆን ተቃርበዋል።
በርካታ አሰልታኖች ከ ቼልሲ ጋር ስማቸው ቢያያዝም
potter በአዲሱ የቼልሲ ባለሃብት ቶድ ቦሊ ተቀዳሚ ምርጫ እንደሆኑ ተገልጿል።
ምናልባትም በሰአታት ዉስጥ ይፋዊ ኮንትራት ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

🔴ሁዋን ማታ በነጻ ዝውውር ጋላታሳራይን ለመቀላቀል በቃል ደረጃ ተስማማቷል።
በቼልሲ እና ማንቸስተርዩናይትድ የምናስታውሰው ተጫዋች ነው ።


በአፍሪካ ኮንፌደሬሽን ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፈው ፋሲል ከነማ እግርኳስ ክለብ በነገው እለት
9፡00 ሰአት ላይ
ፋሲል ከነማ ከ ቡማማሩ(ብሩንዲ)
በ ባህርዳር ስታዲየም

ተጋታሚው ቡማማሩ በብሩንዲ ሊግ A 10 ነጥብ ይዞ 2ኛ ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው
ከ4 ጨዋታ 3 አሸንፎ በ1ዱ አቻ ወጥቶ።


ቼልሲ አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄልን አሰናብቷል


ዛሬ የሚደረጉ የቻምፒዮንስ ሊግ መርሃግብሮችን ስንመለከት

ዲያናሞ ዛግሬብ ከ ቼልሲ
ምሽት 1:45
በዚህ ጨዋታ የቀድሞው የአርሰናል ተጫዋች ኦበመያንግ በቼልሲ ቤት የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል
ቱሄል፤ ወደ ሙሉ የአካል ብቃቱ መመለስ ስላለበት ዛሬ 90 ደቂቃ እንደማይጫወት ተናግረዋል ። ነገር ግን ተቀይሮ ይገባል ወይም ደግሞ የመጀመሪያወቹን ደቂቃወች ሊጫወት ይችላል በዚህ ጉጋይ የተሻለውን እንወስናለን ብለዋል።

በምሽቱ ጨዋታ ብራዚላዊው የ37 አመት ተከላካይ ቲያጎ ሲሊቫ ከቡድኑ ጋር ወደ ክሮሺያ አልተጓዘም ፤
ቲያጎ በያንዳንዱ ከባድ ጨዋታ ላይ ሲጫወት ነብር ስለዚህም አሁን ከሚኖረው በረራ እና ጨዋታ እረፍት የሚያደርግ ይሆናል ; ብለዋል አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል።

በነገራችን ላይ በቻምፕዮንስ ሊግ ታሪክ ጎል በማስቆጠር 3 ኛው በድሜ ትንሹ ተጫዋች ማቲዮ ኮቫቺቺ ነው ተጫዋቹም ጎሉን ያስቆጠረ ዛሬ ተቃራኒ ሁኖ በሚገጥመው ዳይናሞ ዛግሬብ መለያ ነበር ጨዋታውም ዳይናሞ ዛግረብ ከ ሊዮን ነበር ::


psg vs juventus
ምሽት 4:ሰዓት
ሁለቱ ቡድኖች ባደረጉት የመቸረሻ 5 የርስ በርስ ግንኙነት 5ቱንም ጁቬንቱስ ማሸነፍ ችሏል።
psg በሊግ 1 በ6 ጨዋታ 16 ነጥብ በመያዝ ማርሴን በጎል ክፍያ በልጦ ሊጉን በመምራት ላይ ይገኛል


ጁቬንቱስ ባንፃሩ በሴሪ ኤ በ5 ጨዋታ 2 አሸንፎ በ3ቱ አቻ ወጥቶ 9 ነጥብ ይዞ 7ኛ ደረጃላይ ነው የሚገኘው
በዚህ ጨዋታ ፈረንሳዊ አማካኝ ፖል ፖግባ አይኖርም ተጫዋቹ እና ክለቡ ከተነጋገሩ በኋላ ፖግባ የጉልበት ቀዶ ጥገና ለማድረግ ወስኗል ስለዚህም ለቀጣይ 2 ወራት ከሜዳ የሚርቅ ይሆናል ።


በጁቬንቱስ ዉስጥ ለፔኤስጂ የተጫወቱ አራት ተጫዋቾች አሉ ዲማሪያ፤ሞይስኪን፤አ.ራቢዮ እና ፓራዴዝ ። ምንም እንኳን ዲማሪያ በዛሬው ጨዋታ ላይ የማይኖር ቢሆንም ::

የጁቬንቱሱ አሰልጣኝ ማሲሚላኖ አሌግሪ ፤ ከምድባችን ለማለፍ 10 ነጥብ ያስፈልገናል ሲሉ ተናግረዋል ፡ አሰልጣኙ አክለውም በኔ አስተያየት የዘንድሮውን ቻምፒዮንስ ሊግ ለማንሳት ቅድሚያ ግምቱን የሚወስደው ፒኤስጂ ነው ብለዋል።

ኪልያን ምባፔ በሰጠው አስተያየት
"ወደ ሜዳ ስገባ አላማዬ ቡድኔ እንዲያሸንፍ የምችለውን ሁሉ ማድረግ ነው። ያለ ሲሆን ምባፒ ሲቀጥልም ሻምፒዮንስ ሊግ በጣም ከባድ ውድድር መሆኑን ገልፆ በበዚህ ክረምት ምርጥ የአውሮፓ ቡድኖች ሁሉም ተጠናክረዋል፤ ስለዚህ እኛ መታገል አለብን. እንደ ፓሪስ ያለ ክለብ እንደ ጁቬንቱስ ያሉ የአውሮፓን ታላቅ ቡድኖችን ማሸነፍ አስፈላጊ ነው፣ የውድድሩ ጅምራችንንም ጥሩ ማድረግ እንፈልጋለን ብሏል።


የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የግማሽ ሳምንት ፕሮግራም


ዝውውር

ሊቨርፑል ብራዚላዊውን አርቱር ሜሎን ከዩቨንቱስ በውሰት አስፈርሟል በውሉ ላይም የግጅ አማራጭ አልተካተተም ::

ማንቸስተር ሲቲ የ27 አመቱን የመሃል ተከላካይ ማኑኤል አካንጂን ከዶርትሙንድ አስፈርሟል €17.5ም


ፔር ኤምሪክ ኦባመያንግ ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተመልሷል : ተጫዋቹንም በቸልሲ ቤት የምንመለከተው ይሆናል : ቸልሲ በዝውውሩ €14M እና ማርኮስ አሎንሶን ለባርሳ የሚሰጥ ይሆናል ::

ኦበመያንግ 2 ዓመት ኮንትራት ከአንድ ዓመት የማራዘም አማራጭ ከቸልሲ ጋር ይፈራረማል ::


ሌንደን ዶንደንከር ወደ አስቶንቪላ ለመዘዋወር ተስማምቷል ለተጫዋቹም £13M ወጭ የሚደረግበት ይሆናል ::


በ አርሰናል ቤት የምናውቀው ሄክቶር ቤለሪን ባርሳን ተቀላቅሏል ባርሳም ከተጫዋቹ ጋር የ አንድ ዓመት ኮንትራት ነው ለመፈራረም የተስማሙት.... ተጫዋቹ በ ዋትፎርድ እና ሪያል ቤቲስ በውሰት አሳልፏል ::


ፉልሃም ዳኒ ጀምስን ከሊድስ ለማስፈረም ከጫፍ ደርሷል : ሊድስ እሱን ለመተካት ሴኔጋላዊውን ባምባ ዲንግን ከ ኦሎምፒክ ማርሴ ለማስፈረም እየሰራ ነው ::

ማርቲን ብራዝዋይት ከባርሳ ጋር ያለውን ኮንትራት አቁአርቷል : ቀጣይ ማረፊያውም ኤስፓኞል ይሆንል ተብሎ ይጠበቃል ::

የዝውውር መስኮቱ ዛሬ ምሽት ሌሊት 7 ሰዓት የሚዘጋ ይሆናል ::


ተጠናቀቀ ⏱

ሳውዝ አምፕተን 0-1ማን, ዩናይትድ
ብ, ፈርናዴዝ ⚽️55








የዛሬ የዝውውር መረጃወች

ኤመርሰን ፓልሜሪ ለ ዌስትሃም ፈረመ
የ28 አመቱ ጣሊያናዊ የግራ መስመር ተከላካይ ለዝውውሩ 13M£ ከተጨማሪ 2M£ ጋር ወጭ ተደርጎበታል
ተጫዋቹ ያለፈውን የውድድር አመት ቼልሲ በውሰት ሰጥቶት በ ፈረንሳዩ ክለብ ሊዮን ማሳለፉ ይታወሳል።

ኤሪክ ባይሊ ወደ ፈረንሳዩ ክለብ ኦሎምፒ ማርሴ አቅንቷል
አይቬሪኮሳትዊው የመሃል ተከላካይ በአዲሱ የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ስር ከማይፈለጉ ተጫዋቾች መካከል መሆኑን ተከትሎ በዉሰት ዉል የፈረንሳዩን ኦለምፒክ ማርሴን ተቀላቅሏል። በሁለቱ ክለቦች ስምምነት ላይም ኦሎምፒክ ማርሴ በቀጣዩ አመት ለቻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ የሚበቃ ከሆነ ተጫዋቹን በቋሚነት የማስፈረም ግዴታ ተካቶበታል::
ተጫዋቹም ዛሬ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ የልምምድ ማዕከል ካርሪንግቶን አምርቶ የቡድን ጓደኞቹን ይሰናበታል ከዛም በ24 ሰዓት ዉስጥ ወደ ፈረንሳይ ማርሴ በረራውን የሚያደርግ ይሆናል:: እንዴ ፋብሪዝዮ ሮማኞ ዘገባ


ቼልሲና ኦበመያንግ በግል ጥቅማጥቅም ጉዳዮች ተስማምተዋል
ነገርግን አሁንም ዝውውሩ ከመፈፀም ያገደው ነገር የባርሴሎና ከተጫዋቹ ዝውውር 30M£ መፈለጉ ነው :: ቼልሲዎች ባንፃሩ 15M£ ተግቢው ክፍያ ነው ብለው ያምናሉ ::
ፒየር ኤምሪክ ኦበመያንግ ባሁኖ የቼልሲ አሰልጣኝ ስር 79 ግቦችን በዶርትሙንድ እያለ ማስቆጠሩ ይታወሳል ::


የቀድሞው የፒኤስቪ, ማንቸስተር ዩናይትድ, እንድሁም የሊዮን ተጫዋች ሜምፊስ ደፓይ ከባርሴሎና ጋር ያውለውን ኮንትራት ለማቁአረጥ ዝግጁ መሆኑ ተገለፀ :: አሁን የሚጠበቀው የጁቬንቱስ ተጫዋቹን የማስፈረም ግልፅ የሆነ ፍላጎት ነው :: ጁቬንቱሶች ለተጫዋቹ የ 2 ዓመት ኮንትራት ያቀርቡለታል ተብሎ የሚጠበቅ ቢሆንም ባንፃሩ ጁቬንቱስ አርካዴዝ ሚሊክን የማስፈረም አማራጭ መያዛቸው ጉዳዩን በእንጥልጥል እንዲቆይ አድርጎታል ::


ቸልሲ የኤቨርተኑን አጥቂ አንቶኒ ጎርዶንን ለማስፈረም እንደተዛጋጄ ስካይ ስፖርት አስነብቧል ለተጫዋቹም 60M£ከተጨማሪ ክፍያ ጋር ሊያቀርብ መዘጋጀቱ ነው የተገለፀው::
አንቶንይ ማይክል ጎርዶን 1.82cm የሚረዝም የ 21 ዓመት እንግሊዛዊ ወጣት ተጫዋች ነው ::


ከበርካታ ጊዜያት ጀምሮ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ስሙ የተያያዘው የpsv አጥቂ ኮዲ ጋክፖን በተመለከተ የpsv አሰልጣኝ ሩድ ቫን ንስትሮይ ተከታዩን አስተያየት ሰጥቷል ::

እሱን በተመለከተ ለረጅም ጊዜ ብዙ መረጃወች ወጥተዋል:: እነዚህ ወሬዎች ከተሰሙ በኋላም አንድም ቀን በልምምድ ላይ የተለየ ባህሪ አሳይቶ አያውቅም:: ይህ ደግሞ ለወጣት ተጫዋቾች እጅግ በጣም ጥሩ ነገር ነው ሲል የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋች እና ያሁኑ የpsv አሰልጣኝ ሩድ ቫንስትሮይ ተናግሯል ::


ምሽቱን በተደረገው የ ሶሥተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ
ቆንጆ እና ሳቢ ጨዋታ ተመልክተናል በላንክ ሻየር ደርቢ ማንቸስተር ዩናይትድንና ሊቨርፑልን ያገናኝው ጨዋታ በማን, ዩናይትድ አሸናፊነት ተደምድሟል
ማንቸስተር ዩናይትድ በሊጉ ሁለት ተከታታይ ሽንፈቶችን አስተናግዶ ባንጸሩ ሊቨርፑል ሁለት ተከታታይ የአቻ ውጤቶችን ይዞ የተገናኑበት ጨዋታ ነው
ዩናይትድ በተካላካይ ክፍሉ ላይ ወትሮ ከስህተት ርቆ ማያውቀውን የስህተት ስፔሻሊስቱን ሃሪ ማጕየርን በተቀያሪ ቦታ አስቀምጦ የገባ ሲሆን በጨዋታውም የተመለከትነው መቀመጡ ተገቢነት አለው ብለናል ለምሽቱ ድል አርጀንቲናዊው 🇦🇷🇦🇷ማርቲኔዝ ያሳየው አልሸነፍ ባይነት ያስደንቃል 💪💪 የ ጃደን ሳንቾ የአይምሮ ብስለት 👏👏👏የማርከስ ራሽፎርድ በምሽቱ ጨዋታ ጎል ጨራሽነት 👌ጣፋጭ ድል አጊንተዋል
በተቃራኒው በሊቨርፑል በኩል ሁልጊዜም አንድ ለ አንድ መታለፉ እንጂ ክለቡ ላይ ጎል መቆጠሩ ማያስጨንቀው ሚመስለው ግዙፍ ኔዘርላንዳዊ 🇳🇱🇳🇱ቨርዥል ቫንዳይክ የሰራው ስህተት በጉዳት እና በተለያዩ ምክኒያቶች የሳሳው የማህል ክፍሉ የትሬንት መውረድ በቶሎ በክሎፕ ማይታረም ከሆነ የቁልቁለት እና የኅልዮሽ ጉዞ ይቀጥላል


🔥 የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ🔥🔥🔥

የሙሉ ሰዓት ዉጤት

🔴 ማን ዩናይትድ 2 -1 ሊቨርፑል 🛑
ጄ.ሳንቾ 16'                       ሞ.ሳላህ 81'
ማ.ራሽፎርድ 53'


ዛሬ ነሀሴ 16, 12, 2014
ምሽት 04:00
በ 3ተኛ ሳምንት የእንግሊዝ🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿 ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ

ኦልድ ትራፎርድ ስታዲየም 🏟74140 ተመልካች

ማን, ዩናይትድ Vs ሊቨርፑል
ከዚ በፊት 206ጊዜ ተገናኝተው
ማንቸስተር ዩናይትድ 82 አሽነፈ
ሊቨርፑል 68 አሽነፈ
56 አቻ ተለያዩ

ያለፉትን አምስት የመጨረሻ ግንኝነታቸው
ሊቨርፑል 3 አሸነፈ 16 ግቦችን አስቆጠሩ
ማን, ዩናይትድ 2 ጊዜ ሲረቱ 9 ግቦችን አስቆጥረዋል

ዛሬ በሊጉ ሲገናኑ

ሊቨርፑል 2 ነጥብ ይዞ 15ተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ

ማን, ዩናይትድ በ 0 ነጥብ በ 5 የግብ እዳ 19ጠኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል

በማንቸስተር ዩናይትድ በኩል የማይሰለፉ ተጭዋቾች
አንቶኒ ማርሻል
ቪክቶር ሊንደሎፍ
ብሬንዳን ዊሊያምስ
ሜሰን ግሪን ውድ በወንጀል በመጠርጠር 👮‍♂

በሊቨርፑል በኩል
ኢብራሂማ ኮናቴ
ከርትስ ጆንስ
ዴጎ ጆታ
ኦክስሌድ ቻምበርሌን
ጆይል ማቲፕ
ቲያጎ አልካንታራ
ፋቢኒሆ
ዳርዊን ኑንየዝ በቅጣት የማይሰለፉ ተጨዋቾች ናቸው


ሌላው ቼልሲና ሊድስ ዩናትድን ያገናኝው ጨዋታ
አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል እና ቼልሲ በሚገባ ምን እንደጎደላቸው የተመለከቱበት ጨዋታ ሆኖ አልፏል
አሜሪካዊ 🇺🇸🇺🇸የሊድስ አሰልጣኝ ሄሴ ማርሽ በክረምቱ ወሳኝ ተጭዋቾቹን ክላቫን ፊሊፕስን እና ራፊናን ቢያጡም ቆንጆ ተፎካካሪ ቡድን ሰርተዋል 💪💪
ጃክ ሀሪሰን, ሮድሪጎ ይችላሉ 👌👌👏👏
ቼልሲ በዝውውሩ በርካታ ተጭዋቾቹን አቷል, ሩዲገር, ክሪስቴንሰን, ሉካኩ, ወርነርን ለቆ
ስተርሊንግን, ኩሊባሊን እና ኩኩሬላን አምጥቶ ሊጉን ቢጀምርም ተቸግሯል
በትናቱ ጨዋታ ኒጎሎ ካንቴን እና ማቲዮ ኮቫሲችን በጉዳት ይዘው ያልገቡት ሰሟያወቹ አማካኝ ክፍሉ ፍጹም ተሰብሮ ነው የተመለከትነው
የዚ ውጤት ግዙፉን ተከላካይ ካሊዱ ኩሊባሊን የቀይ ካርድ 🟥ሰለባ አርጎታል, ኤድዋርድ ሜንዲ ባልተለመደ መልኩ ስህተት ሰርቶ ጎል ተቆጥሮበታል
ከሮማን አብራሀሞቪች ቼልሲን የተረከቡት ቶድ ቦሆሊ ምን ይወስኑ ይሆን 🤔🤔


ትናት በተደረጉ የእግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታወች ትንሽ ሙያዊ አስተያየት


ኒውካስትል ዩናይትድ እና ማን, ሲቲ ያደረጉት ጨዋታ በጣም ድንቅ ሚባል ነው 👏👏👌👌 የሴንት ጀምስ ፓርኩ ክለብ በበሳል አመራሮቹ ቆንጆ ቡድን እየገነቡ መሆኑን በሚገባ እያስመለከቱን ነው 👌👌ሚያዘዋውሯቸው ተጭዋቾች ሱፐር ስታር ሳይሆኑ ወደ ፊት ሱፐር ስታር የሚሆኑ ናቸው ለአሰልጣኝ ኢዲሀው ምስጋና ይግባውና 💪💪💪ከዚም በላይ ይሰራሉና, ክለቡ ልዩነት ፈጣሪ የሆኑ ድንቅ ኮከቦች አሉት አለን ሴንት ማክሲመን, ብሩኖ ጉማሬሽ,
የፔፕ ሰራዊትም ከመመራት ተነስቶ አቻ መሆን ችሏል ኬቪ አስደናቂነቱን ቀጥሎበታል 🤔🤔
ሁሌም አስገራሚ ነው, ግዙፉ ኖርዊዥን ኤርሊንግ ሆላድ ቆንጆ 9 ቁጥር ነው ከወዲው 3ጎሎች 1 አሲስት በማድረግ ቆንጆ ጅማሬ ነው
ፕሪምየር ሊጉ 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿የሴንት ጀምስ ፓርኩን ጨዋታ ለማስታወቂያ ቢጠቀምበት በጣም መልካም ነው


ኒውካስትል ዩናይትድ 3-3 ማን, ሲቲ

አልሚሮን 28⚽️ ጉንዶሀን 5⚽️

ሀላንድ 61⚽️

በርናርዶ, ሲልቫ 63⚽️

ዊልሰን 40

ትሪፔር 54


ተጠናቀቀ

ሊድስ ዩናይትድ3 Vs 0 ቼልሲ

አሮንሰን 33⚽️

ሮድሪጎ 37⚽️

ጃክ ሀሪሰን 66⚽️

ወስታሀም ዩናይትድ 0 Vs 2 ብራይተን ሆቭ & አልቢዮን
ማክአሊስተር 22⚽️
ትሮሳርድ 69⚽️


ኒውካስትል ዩናይትድ Vs ማን, ሲቲ

ሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም 52305ተመልካች

ኒውካስትል ዩናይትድ 74 አሸነፈ

ማንቸስተር ሲቲ 70አሸነፈ

39አቻ
ያለፉትን 5ጨዋታወች ርስበርስ ግንኝነታቸው
ኒውካስትል ዩናይትድ 0,

3 ግቦችን አስቆጠረ
ማንቸስተር ሲቲ 5 አሸነፈ 20 ግቦችን አስቆጠረ


ዛሬ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሚደረጉ ጨዋታወች

20 last posts shown.

373

subscribers
Channel statistics