ጠይም | Teyim 🌹


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter










Video is unavailable for watching
Show in Telegram


ቅዳሜ አይደለሞይ? ደስታ አንፈልግሞይ? 🤨😍

እነሆ የብቻ ሦስተኛ መጽሐፌን በቅርብ ቀን ብያለሁ። "በከንፈርሽ በራ'ፍ"ን እንደ ታናናሾቿ እንደ የ"ብርሃን ልክፍት" እና "የብርሃን ሰበዞች" ፊት ሰጥታችሁ፣ ስማችሁ፣ ተቆጥታችሁ፣ ተንከባክባችሁ እንደምታሳድጉልኝ አምናለሁ። እንግዲህ ከ"እኔ" ወጥታ "የእኛ" መሆኗ ነውና፣ ወሬውን ለወዳጅ ዘመድም አጋሩት።

Spread the word!



አጽንኦት እንዲያገኝ ስለፈለግኹኝ ነው። በነገራችን ላይ ቤተሰቦቼ እንኳን ወዳጅነታችንን አሁን ከእናንተ ጋር ነው የሚያነቡት። ይኽንን አደረግኹኝ ብዬ ልታበይ ወይ ልደነቅበት አይደለም። ወዳጅ ነኝ የሚል ቀርቶ፣ ማንም ሰው ለክብሯ እና ለprivacyዋ ሲል ማድረግ የሚጠበቅበት የኅሊና ግዴታ መሆኑን ግልጽ ለማድረግ ነው።


እኔና ጥቂት ወዳጆቼ ከጎኗ ሳንርቅ፣ በሰው እና በገንዘብ አቅም በሚታለፍ ነገር ሁሉ ለማገዝ ያልሞከርነው ነገር፣ ያልፈነቀልነው ድንጋይ የለም። እኛ እንዲህ የሞከርን የቤተሰቦቿን መገመት ነው። ቢያንስ መኖሪያ አካባቢዋን ለመቀየር ብዙ ጊዜ ታስቦ እና ተሞክሮ በእሷ እምቢታ ነው የተፋረሰው። እንግዲህ ትልቅ ሰው ናት የአገሩም ህግ አይፈቅድምና፣ ካለእሷ ፍቃድ እና ፍላጎት ጣልቃ መግባት አይቻልም።

ሀኪሞችም ጥቂት እንኳን የጤናዋን ሁኔታ trigger የሚያደርግና የሚያባብስ ነገር እንዳይደረግ፣ ሁሉም ነገር በእሷ ፍቃድ እና ፍላጎት ላይ እንዲሆን አበክረው አሳስበዋል። ያንን ማክበር ነው። የሚባለውንም ሁሉ ብታይ እንዳዲስ የመቀስቀስ እና የመረበሽ አቅም አለውና፣ እስከ ጊዜው ድረስ ከዚህ በላይ ማለት አልችልም። ቢያንስ የሰለጠነ አገር እንደሚኖር ሰው ይኽን መረዳትና ራስን ከተጠያቂነት ማራቅ ይገባ ነበር። ግን አስገራሚ ፍጡሮች ነን።

እንግዲህ እንዲህ የቀረጸውን ቪዲዮ ይዞ ነው እለቀዋለሁ ብሎ ማስፈራሪያ አድርጎት ዛሬ የለቀቀው። ትክክለኛ ቀረጻ እንዳልሆነ ያውቀዋል። ያለችበትን ሁኔታ እና የምትፈልገውንም ከለላ ይረዳል። ለዚያም አይደል ማስፈራሪያ አድርጎት የነበረው? ባይሆንና በሰላም የተቀረጸ ቢሆን በወቅቱ ባሰቡት ቻናል ይለቁት ነበር። እኛም ተደስተን በናፍቆት እናየው ነበር። የቀረጿትም አሁን የታየው ያህል ብቻም አይደለም።

በወቅቱ እሷ ህክምናዋን በተሻለ ሁኔታ ላይ ለመከታተል በጣም ጥሩ ሂደቶች ስለነበሩ ላለማበላሸት ላይ ታች ተብሎ ለእርሷ ሰላም እና ደህንነት ሲባል፣ በመሀል በነበሩ በጎ ሰዎች እገዛና ትብብርም እንዳይለቁት ተሞክሮ ቀርቶ ነበር። ይኸው ነገሩን መልሰው ይዘውት መጥተዋል።

ነፍሱን ይማረውና የአድማስ ሬድዮው ቴዎድሮስ ከማርክስ ባለቤት ከማያ ኃይሌ ጋር ሄዶ ቀርጾ የነበረው ድምጽ ይታወቃል። ቴዲ ራሱ በወቅቱ ሚዲያ እንደማትፈልግና በድብቅ መቅረጹን እዚያው ሬድዮ ላይ ተናግሮ ነበር። ለምን የማትፈልገውን አደረገ? ለምን በድብቅ? ልክ እንዳልሆነ ለማወቅ ህሊናውን ምን ጋረደበት? ለእሱ የአንድ ቀን ቀረጻ ነበር። እሷ ግን ብዙ ተጎዳችበት። ቀርጾ ከተመለሰ በኋላ አንድም ቀን መልሶ ለመደወል አልሞከረም ነበር። እሷም በድብቅ ቀርጾ ማስተላለፉን ስትሰማ እና ስታውቅ በጣም ተረብሻ አዝናበት ነበር ያለፈው።

ሁኔታዋን እንዳየ ወዳጅ እኔም በጣም አዝኜበት ነበር። በወቅቱ እኔ ጋ ደውላ የተናገረችውን እና የተሰበረችውን እስክሞት አልረሳውም። "ጆንዬ እኔ እኮ እንደ አንተ ሰው ወንድም እየመሰሉኝ ነበር በሬን ሲመቱ ተደስቼ የምከፍተው። ምን አደረግኳቸው ይኽን ያህል? ለምን አይተዉኝም?" ብላ ነበር። ያንን መረበሿን ሳይ ቴዲ ጋ ደውዬ ላወራው ሞክሬ ነበር። እሱ እንኳን ሊጸጸት "እንደውም ብዙ ነገር ቆራርጬ ያወጣሁት። ብዙ የተውኩት ድምጽ አለ።" ብሎ ጭራሽ ምስጋና ፈልጎ ነበር። በሰላም ይረፍ።

ግን ለምን ይኽን ያህል አስፈለገ? ጂጂ ሙዚየም ወይ መደበሪያ አይደለችም። የትልቅ ልጅ እናት ትልቅ ሰው ናት። ያንን መገንዘብ ለምን አቃተን? ሚዲያው አስፈላጊ እና ጠቃሚ ቢሆንላትስ ከልጅነት እስከ እውቀት የማደንቃት እኔ አላደርገውም ነበር? ከዚህ ቀደም ክንፉ አሰፋ ያወራበትን ድፍረት ልክ በደፈናው አንስቼው ነበር። ለአንድ ቀን ለሃያ ደቂቃ አግኝቷት ስንት ስዓት ስንት ነገር አወራ? ብቻ በጣም አሳፋሪ ነው።

የሀኪም ትዕዛዝ ስናከብር፣ ለእሷ የሚያስፈልጋትን ብቻ ለማድረግ ስንሞክር እንጂ፣ እንዲህ አይነት ነገር ከእለት ርካሽ የሶሻል ሚዲያ ጩኸት በቀር፣ ለእሷ ጥቅም ቢኖረው፣ ይኽን ድሮ አናደርገውም ነበር? ጭራሽ እንዲህ ዓይነት ነገር ብዙ ወደ ኃላ ይመልሳታል። ሀኪሞችም በሕይወት ላይ ሁሉ ስለሚመጣ ጉዳትና ህመም ማባባስ ሊደርስ ይችላል ልዩ ጥንቃቄ ትፈልጋለች ብለዋል።

አሜሪካ ውስጥ የስነ ልቡና እና አእምሮ ህመም በጥንቃቄ ነው የሚያዘው። ሰው ካልፈቀደ መታከምም ከቦታ ቦታ መዘዋወርም አይችልም። ወዳጅ ነኝ ያለ ያንን ማክበር፣ ሊያደርግ ከሚችለው በጣም ትንሹ ነገር ነው። ትክክለኛ ምርመራዋንም እንኳን እኔ ወይ ሌላ ሰው፣ ሀኪሞች እንኳን እርስ በርስ እንዳያወሩ የHIPPA ህግ ያስገድዳቸዋል።

እንደ ተወዳጅ መዚቀኛ ይቅር፣ ብዙ እንደሰራ ሰው ይቅር፣ እንደ አንድ ሰው፣ እንደ የአገር ልጅ፣ እሷን ያያት እና ያለችበትን ሁኔታ ያየ ሰው ሊያደርግ የሚችለው አንድ ነገር እሷን መጠበቅ እና ከለላ መስጠት ነው። የሚፈልገውን ሳይሆን የሚያስፈልጋትን የሞራል ግዴታ መፈጸም ነው። እንጂ መረሳቱ ትዝ ባለው ቁጥር እንዲህ ዓይነት ግብታዊና ፍጹም ሊጎዳት የሚችል መረጃ ማሰራጫት ተገቢ አይደለም።

አሜሪካ ውስጥ በህግም ቢሆን ራሱን መከላከል የማይችልን ሰው፣ ለራሱ የህግ ከለላ ፍላጎት ወይ በቤተሰብ ፍቃድ (ወላጆች እና ልጅ) እሱንም ታካሚው ቀድሞ ይሁንታ ከሰጣቸው ለህክምና ሂደት ካልሆነ በቀር መቅረጽ ፎቶ ማንሳት በህግ ያስጠይቃል።

ቤተሰቦቿ ለምን ወጥተው አይነግሩንም? የconspiracው ቋሚ ማጀቢያ ነው። ለምን ይነግሩናል? እኛ እንደ አድናቂ ይኽንን ያህል የተጨነቅን እንደ ቤተሰብ እንቅልፍ አግኝተው ይኖራሉ? ሌላው ነገር ቢቀር ቢያንስ ከእኛ አፍ ሰላም ለማግኘትና እፎይ ለማለት ይኽንን ማድረግ ቢችሉ ለምን አይመርጡትም?

ወጥተው ሚዲያው ላይ እንዲህ ነው እንዲያ ብለው መስማት የምንፈልገውን ቢነግሩን፣ እሷ ስትሰማውስ ምን ይሰማታል? ጭራሽ ወደባሰ ሁኔታ እና ድብርት ውስጥ ለመክተት trigger ያደርጋል ተብሎ አይታሰብም?

እናንተ እህታችሁ ወይ ወንድማችሁ ላይ ተመሳሳይ ነገር ቢከሰት እንዲሁ ለወሬ ፍጆታ ታውሉታላችሁ? ብዙ ደስታ ለሰጠችን ሰው ለምን ሰላም እና ከለለ መስጠት ከበደን? የወሬ ፍቅራችን ይህን ያህል ለምን ህሊናችንን አሸነፈው?

አሁንም የተሻለ ህክምናዋን የመከታተል ሁኔታ እና ጥረት ላይ ናት። (ነበረች ባልል ደስ ይለኛል። ግን ይህን ቪዲዮ ካየችው በጣም ትረበሽና የከፋ ሁኔታ ውስጥ መግባቷ አይቀርም። :( ) ብዙ ጊዜ ነገሮች ሊቃኑ ሲሉ ፈተና የሆነው እንደ ቅቤ ሚዲያው ላይ ጠብ የሚደረገው እንዲህ ሆነች፣ በዚህ ገባች ነው። ዋና የምትፈልገው ሰላም እና ከለላ (protection) ነው። Privacyዋን እናክብርላት።

የምትወዷት ከሆነ የምትፈልገውን space እና ነጻነት ስጧት። ፍቅራችንን እና አክብሮታችንን በዚያ እናሳያት። እንርዳት እናሳክማት የሚለው ሀሳብ ከጥሩ ልብ የሚነሳ ቢሆንም፣ ስትፈልግ እና ስትፈቅድ ነው። እስከዚያ የእኛን እርዳታ በግልጽ የጠየቁ ብዙ አርቲስቶች አሉ። እነሱን እናግዝ። በየእምነታችን እንጸልይላት።

ይኽ በእንዲህ እንዳለ በተለቀቀው ቪዲዮ የተነሳ በጤናዋም ሆነ በህይወቷ ላይ ሊደርስ ስለሚችለው ነገር የENT TV ሰዎች እና ጋዜጠኛ ወድንወሰን ከበደ ሙሉ ኃላፊነቱን ይወስዳሉ። ሌሎቻችን ፍቅራችንን እና አድናቆታችንን በመተው፣ ሰላሟን ባለመንሳት እናሳያት። አገር አለኝ ወገን አለኝ ትበል።

P.S. ይኽን ፎቶ የተነሳነው ከአንድ ዓመት በፊት ከእንጅባራ ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክትሬት በተሰጣት ጊዜ፣ የሰማችሁትን የምስጋና ድምጽ በቀረጽኳት እና በወቅቱ ያያችሁትን ፎቶ ባነሳዃት ጊዜ፣ ለማስታወሻ እንነሳ አብረህ ላክላቸውና ይውጣ ብላኝ ያስቀረነው ነበር። በወቅቱም ከዚያም በኋላ በጭራሽ ፎቶውን የማጋራት ፍሎጎት አድሮብኝ አያውቅም ነበር። እንደ ቅርብ ወዳጇም ላደርግ ከምችላቸው ነገሮች መካከል በጣም ተራው ነው። አሁንም የማጋራው በእሷ ፍቃድ፣ በሀኪም ምክረ ሀሳብ መልእክቱ


ጂጂን የሚወዳት የሚቆረቆርላት ሁሉ ማወቅ ያለበት!
«ሰው እየመሰሉኝ ነው በሬን ሲመቱ ተደስቼ የምከፍተው።»

ይኸው ደግሞ የእጅጋየሁ ሽባባውን ነጻነት እና ሰላም ማወክ ዞሮ መጥቷል። ያው መነሻው አብሮ የመታየት፣ ስሜ ከስሟ ጋር ይነሳ የማለት ፍላጎት ነው። እኔ እንኳን የማውቀውን ሁሉ ብናገር፣ ብዙ ነውረኞችን ማጋለጥ ይቻል ነበር። በእሷ ገንዘብ እንሠራለን፣ ዝና እናገኛለን በሚል ፍላጎት እና ተስፋ፣ እንደ investment ገንዘብ መድቦ ለማውጣት፣ ከቦታ ቦታ ይዞ ለመሄድ እስከ መሞከር ድረስ (kidnapping በሉት)፣ ግጥምና ዜማ አስጠንቶ ለዩቲዩብ ንግድ እስከማሰብ ብዙ አሳፋሪ እና ህገወጥ ሙከራ ያደረጉ አሉ። ነገር ግን ዝርዝሩ እሷን ላለመረበሽ እና ደህንነቷን ለመጠበቅ ሲባል ተከድኖ ይብሰል።

አሁን የሚንሸራሸረው ፎቶ እና ዛሬ የተለቀቀው ቪዲዮ፣ ከሁለት ዓመት በፊት ኦክቶበር 23/30, 2022 የተቀረጸ ነው። ጋዜጠኛው አሁን ይኽንን ማድረግ ለምን እንደፈለገ ራሱ ያውቃል። (የሙያ ethics አላየሁበትምና ስቅቅ እያለኝ ነው ጋዜጠኛው የምለው) በወቅቱ ጋዜጠኛም ነውና ከENT (Ethiopian Network TV) ነው የመጣነው ብለው ካሜራ ወድረው ቃለ መጠይቅ አድርጎ ቀርጿትም ነበር። ከቀረጿት ጥቂቱን ነው የለቀቀው።

እጅጋየሁ በጣም ልዩ የሆነ ትኩረት፣ የራስ ምርጫ ነጻነት እና ህክምና የሚፈልግ ሁኔታ ውስጥ እንዳለች ብዙ ሰው ይረዳል ብዬ አስባለሁ። በእሷ የጤንነት ሁኔታ ላይ ያለን ሰው ለቃለ መጠይቅ ማሰብ ትንሽ ህሊና ቢስነት ይጠይቃል። የሚለውም ሁሉም ነገር በቁም ነገር ያለመወሰድ እድሉ ስፋት ለመረዳትም ብዙ ምርምር አይጠይቅም። በተለይ ሀኪሞች አስጠንቅቀው እንዳሉት የሚዲያ ሰው ናትና፣ ከሚዲያ ጋር የተያያዘ ትኩረት ሙሉ ለሙሉ፣ በጭራሽ አያስፈልጋትም።


🌼💛








ደስታ ላካፍላችሁማ! 😍

የዛሬ 6 ዓመት 98 ሺ ዶላር ለህክምና በእኔ አስተባባሪነት የሰበሰብንለት ዮናስ ጋሻቅ፣ ሁለቱንም ክራንቾቹን ትቶ ቆሞ መሄድ፣ ወጥቶ መግባት፣ ሰርቶ ቤተሰብ ማስተዳደር ጀምሮ እናንተን ለማመስገን ቆሟል። እግዚአብሔር የፈቀደው በለጠና፣ ልጅም ወልዷል። እግዚአብሔር ይመስገን።

እናመሰግናለን ብለው ከባለቤቱ ጋር የእምዬ ማርያምን ምስል ስጦታ ሰጥተውኛል። ❤️ ማመስገን። ወክዬ ተቀብያለሁ።

በወቅቱ ከአምስት ብር ጀምሮ ያዋጣችሁ፣ መልእክቱን በማጋራት ያገዛችሁ ሁሉ ምስጋናው ይድረሳችሁ። ደስታውም ለተጨነቁት፣ ከማዋጣት አንስቶ በሀሳብና በጸሎት ላሰቡት ሁሉ አድርሱት።

ሙሉውን ዝግጅት ከምንጊዜም ሚዲያ የዩቲዩብ ቻናል ላይ እዩትማ። link: https://youtu.be/ixnGiL2cox4?feature=shared

አስተዋጽኦ ላደረጉት ሁሉ ምስጋናው እንዲደርስ እባካችሁ ሼር በማድረግ አግዙ። እኔን እንኳን ደስ አለህ ማለት ከፈለጋችሁ ደግሞ ሜዳውም ይኸው ፈረሱም ይኸው፣

“አንድ ስኒ ቡና ለአመሌ በቂ ነው
ሱሰኛ ነህ ካልሽኝ መደጋገሜ ነው” እንዲል ዘፋኙ፣ የልደት ቀኔን ቡና ጋብዙኝ።

ለ"እማሆይ ፓኬጅ" 💛💛💛

ዓላማው በተለያዩ ገዳማት ውስጥ የሚኖሩ መነኮሳይያት (ሴቶች መናንያን) የንጽህና መጠበቂያ ፓድ ራሳቸው ማምረት እንዲችሉ የተጀመረውን እገዛ በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ጃን ሉቃስ በኩል ለመደገፍ ነው።

አገር ውስጥ ያላችሁ እነዚህን አካውንቶች ተጠቀሙ፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
አካውንት ቁጥር 1000524918629 ወይም 8261
አቢሲኒያ ባንክ
አካውንት ቁጥር 8261

የምታዋጡ screenshot ላኩልኝ።

የጎፈንድሚ ሊንክ https://gofund.me/bb7a4f51

SHARE! Spread the word!

❤️


It’s that time of year again—my birthday! 🎉😍 This year, I’m excited to support a meaningful cause: the “Emahoy Project,” which helps Christian mothers (nuns) produce sanitary pads. This initiative operates under the Ethiopian Jandereba Generation and aims to empower mothers in monasteries by providing them with the resources to produce menstrual pads for their own use and for other nuns.

The fund will be used to purchase raw materials, and potentially, establishing a supply chain from other monastery textile productions, and acquire production tools. The nuns will receive essential assistance and training, enabling them to produce sanitary pads and support their community.

As always, consider this like buying me a birthday coffee, or cake. Your contribution will go to the nuns through me, through the Ethiopian Jandereba Generation, Emahoy Project.
Let’s make this another successful year together!

To support the project through local banks:
Commercial Bank of Ethiopia 8261
Abissinia Bank 8261

Please send me a screenshot of your transfer if using local banks.

Thank you!

Spread the word and support if you can!

https://www.gofundme.com/f/wish-me-in-action-support-emahoy-project?utm_campaign=fp_ss_icons_ai&utm_content=amp1v4&utm_medium=customer&utm_source=copy_link











20 last posts shown.