EthioTube


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።
Follow us on other our social media networks:
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter




ዛሬ ጠዋት በጂማ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ተቃውሞ መነሳቱ ተሰማ።

ተማሪዎቹ ይህንን የተቃውሞው ድምፅ ያሰሙት በህዝባችን ላይ ግድያ ይቁም በሚል ምክንያት ሲሆን ተማሪዎቹ ቁርሳቸውን ሳይበሉ ነው ወደ ተቃውሞ የወጡት።

ተቃውሞው እንዳይባባስ የፀጥታ ሀይሎች ጥረት አድርገዋል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
https://t.me/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L


አያት 49 አንድ የባንክ ጥበቃ ተገደለ

በለሚኩራ ክ/ከተማ አያት 49 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ  40/60 ሳይት 3 አያት 49 ግሎባል ባንክ ዘበኛው ዛሬ ጠዋት በጥይት ተመትቶ መገደሉ ታውቋል።

ግድያው የተፈጸመው ጠዋት አንድ ሰዓት አካባቢ ነው ያሉት ምንጮች ሌላኛው በጥይት የተመታው ጥበቃ ሠራተኛ ጓደኛ እንደቆሰለ አስረድተው፣ ገዳዩና አቁሳዩ በሌላ ብራንች የሚሰራ የጥበቃ ሠራተኛ ሳይሆን እንዳልቀረ ጠቁመዋል።ፓሊስ ምርመራ መጀመሩ ተሰምቷል።

ምንጭ ፦ ዋሱ

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
https://t.me/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L


ከምትሰራበት ቤት ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት እና ገንዘብ ሰርቃ የተሰወረች ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለች

ተጠርጣሪዋ ወንጀሉን የፈጸመችው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አያት ዞን1 ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ/ም ነው፡፡ ተጠርጣሪዋ በደላላ አማካኝነት በቤት ሰራተኝነት ከተቀጠረችበት መኖሪያ ቤት በሶስተኛው ቀን ቆይታዋ የግል ተበዳይ ወደ ስራ በሄዱበት ወቅት አጋጣሚውን በመጠቀም በቤቱ ውስጥ የተቀመጠውን የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች እንዲሁም የተለያዩ የወርቅ ጌጣጌጦችን ሰርቃ በመሰወሯ የግል ተበዳይ የተፈፀመባቸውን የወንጀል ድርጊት ለመሪ ሉቄ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አመልክተዋል፡፡

ተጠርጣሪዋ የወንጀል ድርጊቱን ከፈፀመች በኋላ የግል ተበዳይ ጋር ከመቀጠሯ በፊት በክፍለ ከተማው ወረዳ 14 አባዶ አካባቢ ኮንዶሚኒየም ቤት ለሦስት ወራት ተከራይታ በነበረበት ቤት ተደብቃ በክትትል የፖሊስ አባላት ከሰረቀቻቸው የተለያዩ አልባሳት

* የተለያዩ የሴትና የወንድ ጫማዎች
* 18 ሺህ የአሜሪካ ዶላርና የህንድ ሩፒ
* የተለያዩ የወርቅና ልዩ ልዩ  ጌጣጌጦች ጋር በቁጥጥር ስር መዋሏን ከክ/ከተማው የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

በተጨማሪም በሁለት የተለያዩ ስሞች የነዋሪነት መታወቂያ እንደተገኘባትም ተገልጿል።

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የመሪ ሉቄ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ሰለሞን አበበ እንደገለፁት የግል ተበዳይ ተጠርጣሪዋን ለስራ ሲቀጥሯት ያቀረበችው የተያዥ ፎርም የራሷን ፎቶ በትክክል እንዳይለይ አድርጋ የለጠፈች ሲሆን የግል ተበዳይም ይህንን ሳያረጋግጡ በእምነት የቀጠሯት መሆኑን ገልፀው ህብረተሰቡ የቤት ሰራተኛ በአጋዥነት መቅጠሩ ተገቢ ቢሆንም በህጋዊ መንገድ በቂ ተያዥ በማስቀረብ የተያዣቸውን አድራሻና ማንነት በአግባቡ በማጤን መቅጠር እንደሚገባና ውድ የሆኑ ንብረቶችንና ገንዘቦችን ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ በማስቀመጥ በተገቢው ሊቆጣጠሩና ንብረታቸውን ከስርቆት ወንጀል ሊታደጉ እንደሚገባም ተናግረዋል።

ምንጭ፦ አዲስ አበባ ፖሊስ

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
https://t.me/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L










አቶ ጌታቸው ረዳ ላይ ሊመሰርት ያሰበውን የክስ ሂደት ማቋረጡን የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም የመቀሌ ቅርንጫፍ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም የመቀሌ ቅርንጫፍ ጊዜያዊ እምባ ጠባቂ አቶ ፀሀየ እምባየ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ አልሰጠም ያሉትን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ ላይ ሊመሰረት የታሰበው ክስ ለጊዜው መቋረጡን ለአራዳ ኤፍ ኤም ተናግረዋል

ከስራና ከደሞዝ ታግደው የሚገኙ የክልሉ ፖሊስ አባላት ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ የሚጠይቅ አቤቱታ ምላሽ እንዲሰጥ ለጊዜያዊ አስተዳደሩ ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢቀርብለትም ዝምታን በመምረጡ ነበር ክስ ለመመስረት ታስቦ የነበረው ብለዋል፡፡

በቅርቡ እምባ ጠባቂ ተቋሙ የፖሊስ አባላቱ ወደስራ እንዲመለሱና ሳይከፈል የቆየ ውዝፍ ደሞዝ እንዲከፈላቸው ውሳኔ ማስተላለፉን ተከትሎ የክልሉ ጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ ይህን ውሳኔ ለማስተግበር ለካቤኔቸው ደብዳቤ በማስገባታቸው ውሳኔው እስኪታወቅ ክሱ እንዲቋረጥ ተደርጓል መባሉን አራዳ ሰምቷል፡፡

የትግራይ ክልል የመቀሌ ቅርንጫፍ እምባ ጠባቂ ተቋም ቅሬታ ያቀረቡ የፖሊስ አባላት 450 ናቸው ያለ ሲሆን ነገር ግን ከሌሎች ቅሬታ አቅራቢዎች በተገኘው መረጃ መሰረት በዚህ ችግር ላይ የሚገኙ የፖሊስ አባላት ቁጥር ከ3000 በላይ መሆናቸውን አስታውቋል

በቀጣይ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የካቢኔ ውሳኔ ታይቶ በአቶ ጌታቸው ረዳ ላይ ተቋሙ ሊመሰርት ያሰበው ክስ ሊቀጥልም ላይቀጥልም እንደሚችል አቶ ፀሀየ ተናግረዋል፡፡

በፌደራል መንግስቱና በህውኃት መካከል የተደረገውን ጦርነት ተከትሎ ህውኃት መቀሌን ከተቆጣጠረ ጀምሮ ለፌደራል መንግስቱ ወግናችኋል የተባሉ በርከታ የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አባላት ከስራና ከደሞዝ ታግደው እንደሚገኙ ይታወሳል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
https://t.me/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L


በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እስር ላይ የሚገኙ 270 ናይጄሪያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ትእዛዝ ተሰጠ

የናይጄሪያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአሁኑ ጊዜ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ያሉ ከ270 ያላነሱ ናይጄሪያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ትእዛዝ አስተላልፏል።

ፍርድ ቤቱ ይህንን ትእዛዝ እንዲስፈፅሙ ትእዛዝ የሰጠው ለአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የናይጄሪያ ዲያስፖራ ኮሚሽን እንደሆነ የናይጄሪያ ብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል።

ፍርድ ቤቱ ትእዛዙን ያስተላለፈው ኢትዮጵያ  ለእስረኞቹ የሚሆን ምግብ፣ መድኃኒት እና ሌሎች ግብአቶችን ለመሸፈን የሚያስችል በጀት እንደሌላት በመግለጿ መሆኑ ተነግሯል።

የናይጄሪያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ከዚህ ቀደም በአደገኛ እፅ ዝውውርና ሌሎች ወንጀሎች የተጠረጠሩ ናይጀሪያዊያን በቃሊቲ እስር ቤት  እንደሚገኙ ገልጾ ነበር።

ከ250 በላይ ናይጀሪያዊያን እስረኞች ኢትዮጵያ ውስጥ አግባብ ባለሆነ መንገድ መያዛቸውን የሀገሪቱ የመብት ተከራካሪዎች ገልፀው የነበረ ሲሆን በኢትዮጵያ ያሉ ናይጄራዊያን እስረኞችን ሁኔታ የሚያጣራ ኮሚቴ መዋቀሩም አይዘነጋም።


ምንጭ፦ ቲክቫህ

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
https://t.me/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L








ከንቲባ አዳነች አበቤ መርካቶን በተመለከተ ዛሬ በምክር ቤት ተጠይቀው ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል።

"እንደ ሀገር ያለውን የግብይት ስርዓት በዘላቂነት ለማስተካከል የምናደርገውን ጥረት በጥናት ላይ ተመርኩዘን ክትትል ስናደርግ የቆየን ሲሆን፤ ያገኘነው ግኝት በርካታ ሕገ ወጥ የሆኑ አሰራሮች እንዳሉ ተመልክተናል"

"ግማሹ ግብር እየከፈለ ሌላው የማይከፍልበት አሰራር መኖሩን ከነጋዴዎች ጋር ባደረግነው ውይይት እና ክትትል ተገንዝበናል።ግብር ለማስከፈል እና ደረሰኝ እንዲቆርጡ ለማድረግ በተደረገው ሂደት፤ በሀሰት ውዥንብር በመንዛትና መጋዘኖችን በመዝጋት በምሽት እቃዎች ሲጫኑ ነበር።ይህ ፍፁም ስህተት ነው።"

"በቀጣይ ሕጋዊ ስርዓት በመዘርጋት እና ለእያንዳንዱ ግብይት ደረሰኝ እንዲቆርጡ በማድረግ ግብርን በአግባቡ መሰብሰባችንን አጠናክረን እንቀጥላለን" ብለዋል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
https://t.me/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L




ፍቅር እስከ መቃብር ተከታታይ ድራማ ሊጀምር ነው


" ተኩስ ተከፍቶብኝ መኪናዬ ላይ ጉዳት ደርሷል " - አቶ ሰለሙን መዓሾ

" መረጃው ከእውነት የራቀ ነው። የተኮሰበት ሰው የለም " - አቶ ገብረ ተክለሃይማኖት

" ፓለቲከኞች የልዩነታችሁ ጣጣችሁን እዛው ጨርሱት ወደ ሰራዊቱ አታጋቡት " - ጀነራል ህንፃ ወ/ጊዮርጊስ

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመራር ከተቃጣባቸው የግድያ ሙከራ ማምለጣቸውን ተሰምቷል።

የጊዚያዊ አስተዳደሩ የማእከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሰለሙን መዓሾ ባለፈው እሁድ ህዳር 8/2017 ዓ.ም ከስራ ባለደርቦቻቸው ጋር ከአክሱም ወደ መቐለ ሰጓዙ የግድያ ሙከራ እንደ ተቃጣባቸውና ከግድያ ሙከራው እንደተረፉ ተናግረዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ከአክሱም ወደ መቐለ ሲመለሱ ማይቅነጣል ፈላፍል በተባለ ቦታ ሲደርሱ መኪናቸው ላይ ተኩስ እንደተከፍተባቸው ገልጸዋል።

ለጊዜው እነማን እንደተኮሱባቸው ማንነታቸውን / የታጣቂዎችን ማንነት ማወቅ እንዳልቻሉ ገልጸው በተተኮሰባቸው ጥይቶች መኪናቸው ላይ ጉዳት መድረሱን አስረድተዋል።

በጥይት የተመታው መኪናቸውን የሚያሳይ ፎቶም ይፋ አድርገዋል።

በመኪናው ውስጥ ከእሳቸው በተጨማሪ ጥበቃቸው እና የመኪናው ሹፌር ነበሩ።

ዋና አስተዳዳሪው የደረሰባቸው አካላዊ ጉዳት እንደሌለ አረጋግጠዋል።

እሁድ ህዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም በዋና አስተዳዳሪ ሰለሙን መዓሾ የመግደል ሙከራ መደረጉ በማህበራዊ የትስስር ገፆች ላይ በስፋት ከተሰራጨ በኃላ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ወደ ማይቅነጣል ወረዳ ስልክ ቢደውልም ጉዳዩ የሚያረጋግጥ አካል አልተገኘም ነበር።

የዞኑ መቀመጫ ወደሆነችው አክሱም የሚገኝ ፓሊስ ማዘዣ ስልክ ቢደወልም የተጣራ መረጃ ማግኘት አልተቻለም።

ይህ በእንዲህ እያለ የመግደል መከራ ተቃጥቶበታል የተባለው ቦታ የሚያስተዳድረው የማይ ቅነጣል ወረዳ " ጉዳዩ አልተፈፀመም " የሚል መግለጫ አውጥቷል።

የማይቅነጣል ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ገብረ ተክለሃይማኖት ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ደግሞ ፣ ጉዳዩን ከወረዳው የጸጥታና ፖሊስ አባላት ማጣራታቸውን ገልፀው፣ " መረጃው ከእውነት የራቀ ነው። የተኮሰበት ሰው የለም " ብለዋል።

ከዚህ ባለፈ " በአከባቢው አለ ጉዳዩ ፈፅሞታል " ተብሎ በማህበራዊ የትስስር ገፅ ተጠቃሚዎች ተደጋግሞ የተጠቀሰው የትግራይ ሰራዊት አርሚ 60 አዛዥ ጀነራል ህንፃ ወ/ጊዮርጊስ እሳቸው የሚያዙት በፀሃፊዎቹ የተገለፀው ሰራዊት በአከባቢው እንደሌለ በመግለፅ " ፓለቲከኞች የልዩነታችሁ ጣጣችሁን እዛው ጨርሱት ወደ ሰራዊቱ አታጋቡት " ሲሉ ተጠምደዋል።

ከአሁን በፊት በተለያዩ ጊዚያት መሰል የግደያ ሙከራዎች በጊዜያዊ አስተዳደሩ ከፍተኛ ሹማመንት በየነ መኩሩ ፣ ነጋ ኣሰፋ ፣ ሰሎሙን ትኩእ እንዲሁም በአክሱም ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራር መደረጋቸው የተነገረ ቢሆንም እስካሁን የድርጊቱ ፈፃሚዎች ተጣርተው የተወሰደ እርምጃ የለም።

Via VOATigrigna

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
https://t.me/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L







20 last posts shown.