"ዓድዋ ኢትዮጵያውያን ውድ ህይወታቸውን መሰዋዕት በማድረግ ያስገኙት ድል ነው"- ኢንጅነር አይሻ መሐመድ
**
(ኢ ፕ ድ)
የአድዋ ድል የፅናትና የአልበገር ባይነት ማሳያ መሆኑን የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሐመድ ገለፁ።
129ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ ''አድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል'' በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ ይገኛል።
በክብረ በዓሉ ተገኝተው መልክት ያስተላለፉ የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሐመድ፤ ዓድዋ የኢትዮጵያውያን ፅናትና አልበገር ባይነት ማሳያ ነው። ዓድዋ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የመላው ጥቁር ህዝቦች ድል መሆኑን ተናግረዋል።
ድሉ ኢትዮጵያውያን ከልጅ እስከ አዋቂ አብረው ያሸነፉበትና ነፃነታቸውን የማይተካ ውድ ህይወታቸውን መሰዋዕት በማድረግ ያስገኙት መሆኑን ጠቅሰዋል።
ዓድዋ የድል ታሪክ ብቻ ሳይሆን ኃላፊነት ነው፤ የአባቶቻችንን ህልም አንድነትና ብልፅግናችንን በማረጋገጥ ማሳካት ይገባል ብለዋል።
የአባቶቻችንን የጀግንነት መንፈስ በመላበስ ፈተናዎች በፅናት ለመሻገር መሥራት ከአሁን ዘመን ይጠበቃል ብለዋል።
በክብረአብ በላቸውና አማን ረሽድ
የካቲት 23 ቀን 2017 ዓም