ይግባኝ ምክረ ሕግ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Law


📞በስልክዎ ባሉበት ሆነ በማንኛውም ሕግ⚖️ነክ ጉዳዮች ላይ ነፃ🆓️የሕግ ምክር አገልግሎት የሚያገኙበት ገጽ! በነፃ እና በነፃነት ማወቅ፣ መረዳት እና ማብራሪያ በሚፈልጉባቸው ሕግ ተኮር ጉዳዮች ላይ ይግባኝ ይበሉ! በማንኛውም ሕግ ነክ ጉዳዮች ላይ እስኪገባዎት ድረስ ይግባኝ ይበሉ!⚖️

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Law
Statistics
Posts filter




💔🤵💔👰
በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 76 ላይ እንደተመለከተው ጋብቻ ሊፈርስ የሚችለው በሁለት መንገድ ነው፦
1ኛ. በስምምነት ለመፋታት በሚቀርብ የፍቺ አቤቱታ፤
2ኛ. በአንደኛው ተጋቢ በኩል በሚቀርብ የፍቺ አቤቱታ።
⚠️⚠️ከዚህ ውጪ ጋብቻ ሊፈርስ የሚችልበት አግባብ የለም።⚠️⚠️
✍✍ፍቺ በውክልና ይቻላል ወይ?✍✍
በዚህ ረገድ የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ በግልጽ ያስቀመጠው የክልከላም ሆነ የመፍቀድ ድንጋጌ የለውም። ፍቺን በተመለከተ ዳኞች ወይም ተጋቢዎቹን በአካል እንዲቀርቡ ሊያደርጉ የሚችሉት ጋብቻው እንዲቀጥል ለማስማማትና ለማነጋገር በማሰብ ነው፤ ይህ ደግሞ የግዴታ አይደለም። በመሆኑም በሕግ አግባብ ለጠበቃም ሆነ ለቤተሰብ አባል የሚሰጥ ሕጋዊ ውክልና ካለ ፍቺን በውክልና ማድረግን የሚከለክል ሕግ የለም።
⚖⚖ፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት⚖⚖
👉በዚህ ረገድ የፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት በቅጽ 23 በመዝገብ ቁጥር 150408 ላይ በሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 58 እና በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 2199 መሠረት ውክልና ያለው ሰው ፍቺን የሚጠይቀው ተጋቢ በአካል ባይኖርም ፍቺን መጠየቅና ውሳኔን ማሰጠት እንደሚችል አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል።
⚖️ይግባኝ መብት ነው!!!
©️ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
☎️ 09 10 61 69 50
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ


የመስከረም_ወር_2017_ዓም_የሐራጅ_ሽያጭ_ማስታወቂያ.PDF
3.2Mb
⚠️⚠️⚠️💰💰💰⚠️⚠️⚠️
የመስከረም ወር 2017 .ም
የጨረታ ማስታወቂያ
⚠️⚠️⚠️💰💰💰⚠️⚠️⚠️
ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
https://t.me/laws2016
በማናቸውም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች
ጠበቃና የሕግ አማካሪ
09 10 61 69 50


የመንግሥት መኖሪያ ቤት ለ3ኛ ወገን ማስተላለፍ
📌መርሕ
#የመንግሥት ቤትን የተከራየ ማንኛውም ሰው በሞት ሲለይ ወይም ከአካባቢው በተለያየ ምክንያት ሲለቅ ቤቱን ለአከራይ እንዲመልስ ይደረጋል።
📌ልዩ
ነገር ግን ሟች በተከራየው ቤት ውስጥ
#የተከራይ ባል ወይም ሚስት ለመሆናቸው ሕጋዊ ማስረጃ ሲቀርብ ወይም የተከራይ ልጆችና በሕጋዊ መንገድ በጉዲፈቻ ያደጉ ልጆች በቤት ውስጥ እየኖሩ መሆናቸው በወረዳው ቤቶች አስተዳደር ሲረጋገጥ፤
#በችግር ምክንያት ከተከራይ ጋር በጥገኝነት የሚኖሩ የባል ወይም የሚስት እናት ወይም አባት ለመሆናቸው በወረዳው ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ሲረጋገጥ፤
እነዚህም ወራሾች ስለመሆናቸው እና በስማቸው ወይም በትዳር አጋራቸው ስም የጋራ መኖሪያ ቤት፣ የግል መኖሪያ ቤት ወይም የቤት መስሪያ ቦታ ወይም ከመንግሥት የተከራዩት ቤት የሌላቸው መሆኑን ወይም ክ1997 ዓ.ም በኋላ በሽያጭ ወይም በሥጦታ ያላስተላለፉ መሆኑ በማስረጃ ሲረጋገጥ በቀድሞው ውል እንዲዋዋሉ ይፈቀድላቸዋል።
📌ጠቅላላ መርሆች
#ቤቱ ወደ ወራሾች ሲተላለፍ ከላይ በተቀመጠው ቅደም ተከተል መሠረት የሚሆን ይሆናል።
#ወራሾች ብዙ የሆኑ እንደሆነ በእነ ስም ውል የሚፈጽሙ ይሆናል።
⚖️ይግባኝ መብት ነው!!!
©️ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
☎️ 09 10 61 69 50
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ




ሙሉ አዋጁን በቴሌግራም ቻናል
https://t.me/etonlinelegal
እና በቴሌግራም ግሩፕ
https://t.me/etonlinelegalchat
ያገኙታል። ለተጨማሪ ሕግ ነክ መረጃዎችና ነፃ የሕግ ምክር አገልግሎት ለማግኘት ቤተሰብ ይሁኑ
#ማንኛውም ሰው የግል፣ የወል ወይም የመንግሥት ይዞታን በሕገወጥ መንገድ የወረረ ከብር 35,000 እስከ ብር 100,000 ወይም ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ወይም በሁለቱም ይቀጣል።
#ማንኛውም ሰው በግል፣ በወል ወይም በመንግሥት ይዞታ ላይ ጉዳት ያደረሰ ከብር 50,000 እስከ 150,000 ወይም ከ3 ዓመት እስከ 7 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ወይም በሁለቱም ይቀጣል።
#ማንኛውም ሰው ባልተፈቀደ ቦታ ላይ ማንኛውንም ግንባታ የሰራ ወይም እንዲሰራ የፈቀደ ከብር 25,000 እስከ ብር 50,000 ወይም ከ1 ዓመት እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት ወይም በሁለቱም ይቀጣል።
#ማንኛውም ሰው ከመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ውጪ ይዞታውን ጥቅም ላይ ካዋለ ከብር 20,000 እስከ ብር 50,000 ወይም ከ1 ዓመት እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት ወይም በሁለቱም ይቀጣል።
#ሀሰተኛ የመሬት ይዞታ ማስረጃ ያቀረበ ባለይዞታ ማስረጃ የሰወረ ወይም የተሳሳተ ማስረጃ የሰጠ ባለሙያ ከብር 10,000 እስከ ብር 25,000 ወይም ከ1 ዓመት እስከ 3 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ወይም በሁለቱም ይቀጣል።
#ማንኛውም ሰው መሬት የሸጠ ወይም የገዛ እንደሆነ ከብር 100,000 እስከ ብር 200,000 ወይም ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ወይም በሁለቱም ይቀጣል።
አዋጅ ቁጥር 1324/2016 ዓ.ም የኢፌዲሪ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ አንቀጽ 62
⚖️ይግባኝ መብት ነው!!!
©️ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
☎️ 09 10 61 69 50
ጠበቃና የሕግ አማካሪ


3. ከይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሚጠይቁትን ዳኝነት ግልጽ ያድርጉ
ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 348 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት በቀረበለት ይግባኝ ላይ የሥር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ለማጽናት ወይም ለመለወጥ ወይም ለመሻር የሚችል በመሆኑ እርስዎ ከእነዚህ ሦስቱ የቱን እንደሚፈልጉ ግልጽ ያድርጉ።
4. ይግባኞትን በጊዜ ያቅርቡ
በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 323 ንዑስ አንቀጽ 2 ላይ በግልጽ እንደተመልልከተው ይግባኝ የሚጠየቀው ይግባኝ የሚባልበት ጉዳይ በተፈረደ በ60 ቀናት ውስጥ ነው። በመሆኑም በተሰጠው ውሳኔ ላይ ቅሬታ ያለዎት እንደሆነ በጊዜ የውሳኔ ግልባጭዎን ወጪ በማድረግ ይግባኝ ይጠይቁ።
⚖️ይግባኝ መብት ነው!!!
©️ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
☎️ 09 10 61 69 50
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ


በሥር ፍርድ ቤቶች በሚሰጡ ውሳኔዎች ላይ ስህተት አለው ብለው ሚያምኑ እንደሆነ የተሰጠውን ውሳኔ ለማሳረም ሁለት ዕድሎች ይኖርዎታል።
የመጀመሪያው ይግባኝ ሲሆን ሁለተኛው ጉዳዩን ውሳኔ በሰጠው ፍርድ ቤት በድጋሜ እንዲታይ ማስደረግ ነው። ለዛሬ ስለይግባኝ እንነጋገራለን።
ይግባኝ በሥር ፍርድ ቤቶች ላይ የተፈጸሙ ሦስት ስህተቶችን ማለትም የክርክር አመራር ሂደት፣ የማስረጃ ምዘና እና የሕግ አተረጓጎም ነጥቦችን መነሻ በማድረግ የሚቀርብ አቤቱታ ነው።
ይግባኝ በሚጠይቁበት ወቅት እነዚህን ነጥቦች ልብ ይበሉ!
1. በሥር ፍርድ ቤት ያላነሱትን ክርክር አያንሱ
ይግባኝ የሚጠየቀው በሥር ፍርድ ቤት እንዲህ እና እንደዛ ብዬ በጽሑፍ፣ በቃልና በምስክሮች ተከራክሬና አስረድቼ እያለ በዝምታ ወይም ያለአግባብ መታለፉ ስህተት ነውና ይታረምልኝ የሚሉበት እንጂ አዲስ ነጥብ ሚያቀርቡበት ባለመሆኑ ጥንቃቄ ያድርጉ።
2. የሥር ፍርድ ቤት የፈጸመውን ስህተት በግልጽ ያስቀምጡ
ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ላይ ያሉ ዳኞች እርስዎ ያቀረቡህን የይግባኝ አቤቱታ፣ የሥር ፍርድ ቤትን መዝገብ እና የእርስዎን ክርክር በማየት ብቻ በጉዳዩ ላይ ያስቀርባል ወይም አያስቀርብም የሚሉ በመሆናቸው አቤቱታዎት ግልጽ በሆነ መልኩ መቅረብ አለበት።


#በአንድ የወንጀል ድርጊት በፍርድ ቤት ክስ የተመሰረተበት ሰው የወንጀል ክስ አቤቱታው እንደደረሰው ከተረጋገጠ በኋላ የወንጀል ድርጊት መፈጸም ወይም አለመፈጸሙን በማመን ወይም በመካድ ቃሉን ይሰጣል። ይህም በፍርድ ቤቱ ይመዘገባል።
#በተጠረጠረበት ወንጀል ጥፋተኛ ስለመሆኑ አምኖ ቃሉን የሰጠ ሰው ላይ ዳኞች በልዩ ሁኔታ ነገሩን ለማጥራትና ከጥርጣሬ ነፃ ለመሆን በማሰብ ካልሆነ በስተቀር የከሳሽን ምስክር መስማት ሳያስፈልጋቸው በወንጀለና መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 134 መሠረት የጥፋተኝነት ውሳኔ ይሰጣሉ።
#የጥፋተኝነት ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ ቀጣዩ ሂደት ለጥፋቱ በሕግ የተቀመጠውን የቅጣት ውሳኔ መስጠት በመሆኑ የቅጣት ማክበጃና ማቅለያ ምክንያቶችን ከከሳሽና ከተጠርጣሪው በመቀበል በሕጉ የተቀመጠውን የጥፋት መጠን ልክ ቅጣት ይወስናሉ።
ይግባኝ መጠየቅ የማይቻለው በምን ላይ ነው?
#በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 185 ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ በግልጽ እንደተመለከተው ጥፋተኝነቱን አምኖ ቃሉን የሰጠ ሰው በተጠረጠረበት ወንጀል ጥፋተኛ አይደለውኝም በማለት ይግባኝ ለመጠየቅ መብት የለውም።
ለምሳሌ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 555 መሠረት አስቦ በሌላ ሰው ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ያደረሰ ግለሰብ ጥፋቱን ስላመነ ፍርድ ቤቱ በሕጉ ከተመለከተው ቅጣት በ10 ዓመት ጽኑ እስራት ቢፈርድበት ባደረሰው የአካል ጉዳት ጥፋተኛ መባሉን መነሻ በማድረግ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ ያለኝ ያለአግባብ ነው በማለት ይግባኝ መጠየቅ አይችልም። ነገር ግን በተወሰነበት የ10 ዓመት ጽኑ እስራት ተገቢ አለመሆን ላይ ይግባኝ መጠየቅ ይችላል።
#ነገር ግን በቅጣቱ ልክ ወይም ቅጣቱ ሕጋዊ ስላለመሆኑ በመከራከር ይግባኝ የመጠየቅ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ይግባኝ መብት ነው!




#የፍርድ ቤት ክርክር ያለባቸው ንብረቶችን በሐራጅ መግዛት ጠቀሜታዎቹ፦
1. ስለሚገዙት ንብረት ሕጋዊነት እርግጠኛ መሆን መቻልዎ፤
2. አቅምዎትን ከግምት ውስጥ ባስገባ ደረጃ ለሚፈልጉት ንብረት ፍትሐዊ በሆነ የውድድር መድረክ ንብረቶቹን ለመግዛት መቻልዎ፤
3. የሚገዙትን ንብረት በቦታው ተገኝተው የንብረቱን ደረጃ፣ ዓይነትና ጥራት ማወቅ መቻልዎ፤
4. ስም ለማዘዋወር የሚፈጠሩ እክሎች በብዙ መቀነሳቸው
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የነሐሴ ወር የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ ሙሉውን ሰነድ በማውረድ ይጠቀሙ።


#በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 ዓ.ም አንቀጽ 38 ንዑስ አንቀይ 2 ላይ በግልጽ እንደተመለከተው የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በየዓመቱ ከነሐሴ 1 ቀን እስከ መስከረም 30 ድረስ ዝግ ይሆናሉ።
#በርካቶቻችን ግን የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዝግ ይሆናሉ ሲባል ክርችም ተደርጎ እንደሚዘጋ ተቋም አድርገን በስህተት እንረዳለን፤ ለዛም ነው ትላንት በችሎት ገጠመኝ በርካታ ባለጉዳዮች ፍርድ ቤት ሊዘጋ ነውና ኧረ በፍጥነት ዕግድ ስጡን! ፋይል ክፈቱልን! የውሳኔ ግልባጭ ካልተሰጠን... እያሉ ሲጋፉ የተስተዋለው።
በዚህ የዕረፍት ወቅት የሚሰሩ ሥራዎች፦
#የዋስትና
#የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች
#አካል ነፃ የማውጣት ክሶች
#በመንግሥትና በሕዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ጉዳዮች
#የቀለብ ጉዳዮች እና ሌሎች በበቂ ምክንያት በአስቸኳይ ሊታዩ የሚገባቸው ጉዳዮች በተረኛ ችሎት በመደበኛነት ይስተናገዳሉ።
ሌሎች ጉዳዮችስ?
#ትልቁ አለመረዳት እዚህ ጋር ነው፤ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ በሚሆኑባቸው ወቅቶች ፋይል መክፈትንና ዕግድ መጠየቅን ሚከለክል ድንጋጌ አልተቀመጠም።
#ያለዎት ጉዳይ ቀጣይ ዓመት ጥቅምት ወር ፋይል ቢከፈት ሚፈጠርብዎት የመብት ጥሰት ከሌለ ፋይል ሳይከፍቱ መቆየት ይችላሉ፤ ነገር ግን የለም ፋይል ከፍቼ ቀጠሮው ለቀጣይ ዓመት ይሻገርልኝ ካሉም መብትዎ ነውና የተሳሳተውን አረዳድ ያርሙ።
#በስተመጨረሻ በአዲስ አበባ ደረጃ የከተማው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች እና ማኅበራዊ ፍርድ ቤቶች መደበኛ ሥራቸውን እንደሚያከናውኑ አይርሱ።
⚖️ይግባኝ መብት ነው!!!
©️ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
☎️ 09 10 61 69 50
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ


⚖️በቸልተኛነት ሰውን መግደል
⚠️የኢፌዴሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 543
#ጥፋተኛው የሌላን ሰው ሕይወትና ደኅንነት የመጠበቅ ግዴታ ሳይኖርበት በቸልተኝነት ሰውን የገደለ እንደሆነ ከስድስት ወይም እስከ ሦስት ዓመት ሊደርስ በሚችል ቀላል እሥራት ወይም ከሁለት ሺ እስከ አራት ሺ ብር ሊደርስ በሚችል መቀጮ ይቀጣል፤
#ነገር ግን ጥፋተኛው የሌላን ሰው ደኅንነት የመጠበቅ የሙያ ግዴታ ያለበት እንደሕኪም ወይም አሽከርካሪ ያለ እንደሆነ ቅጣቱ ከአንድ ዓመት እስከ አምስት ዓመት ሊደርስ የሚችል ቀላል እሥራት እና ከሦስት ሺ እስከ ስድስት ሺ ብር ሊቀርስ የሚችል መቀጮ የሚያስቀጣ ይሆናል።
#ጥፋተኛው ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎችን የገደለ እንደሆነ ወይም ግልጽ የሆነ ደንብ በመጣስ የፈጸመው እንደሆነ ወይም አደንዛዥ ዕፅ በመጠቀም እንደሆነ ቅጣቱ ከአምስት ዓመት እስከ አሥራ አምስት ዓመት ለመድረስ በሚችል ጽኑ እሥራት እና ከብር አሥር ሺ እስከ አሥራ አምስት ሺ የሚደርስ መቀጮ ይሆናል።
⚖️ይግባኝ መብት ነው!!!
©️ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
☎️ 09 10 61 69 50
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ


⚖️ከባድ የሰው ግድያ
⚠️የኢፌዴሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 539
#ጥፋተኛው ሟችን ለመግደል አስቀድሞ የነበረው ሃሳብ፣ የተጠቀመበት መሳሪያ፣ ግድያው የተፈፀመበት መንገድ ሁኔታው ጨካኝ፣ ነውረኛ እና አደገኛ መሆኑ፤ እንዲሁም በተደራጀ የወንበዴ ቡድን አባል በመሆን ወይም ሌላ ወንጀልን ለመፈጸም ወይም ወንጀሉ እንዳይታወቅ ለማድረግ የተፈፀመ መሆኑን መነሻ በማድረግ ሲሆን፤ ቅጣቱም በዕድሜ ልክ ፅኑ እሥራት ወይም በሞት ያስቀጣል። ነገር ግን ጥፋተኛው በዚሁ ድንጋጌ መሠረት ጥፋተኛ ተብሎ በእሥራት ላይ እያለ ይህንኑ ወንጀል ፈጽሞት እንደሆነ በሞት ይቀጣል።
⚖️ተራ የሰው ግድያ
⚠️የኢፌዴሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 540
#በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 539ም ሆነ በአንቀጽ 541 ከተመለከቱት ውጪ ባለ መንገድ የተፈጸሙ እና የሚፈጸሙ የግድያ ወንጀሎች በዚህ ድንጋጌ ሥር የሚያርፉ ይሆናሉ፤ ቅጣቱም ከአምስት ዓመት እስከ ሃያ ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት የሚያስቀጣ ይሆናል።
⚖️ቀላል የሰው ግድያ
⚠️የኢፌዴሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 541
#ጥፋተኛ የተባለው ሰው ወንጀሉን የፈጸመው አስገዳጅ ሁኔታን ወሰንን በመተላለፍ ወይም ሕጋዊ መከላከልን ከመጠን በማሳለፍ ሲሆን፤ ወይም ድርጊቱን የፈጸመው ከፍ ባለ ደም በሚያፈላ ስሜት ውስጥ በመግባት ወይም ሕሊናውን ሊያውክ በሚችል ድንገተኛ ምክንያት በከፍተኛ ስሜት ውስጥ እና መሰል በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ሆኖ የፈጸመው ሲሆን፤ ቅጣቱም ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ቀላል እሥራት የሚያስቀጣ ይሆናል።


#ከሰሞኑ እየበዛ ያለው ጥያቄ 'ልጄን ወይም የልጅ ልጄን ትምህርት ቤት ለማስመዝገብ የልደት ካርድ አቅርቢ ተባልኩኝ እሱን ለማውጣት ደግሞ ሌላኛው ወላጅ ከሌለ ወይም የሞግዚትነት ውሳኔ ከሌለሽ አይቻልም ተባልኩኝ' ምን ይሻለኛል? የሚል ነው። እነሆ ምላሹ!
#ልጅዎን ወይም የልጅ ልጅዎን ለብቻዎ እያሳደጉ ከሆነ በሚኖሩበት ክፍለ ከተማ ሥር በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመቅረብ ልጅዎትን ወይም የልጅ ልጅዎን ለብቻዎ እያሳደጉ መሆኑንና ለልጅዎ ወይም ለልጅ ልጅዎ ሞግዚትና አሳዳሪ ተደርገው ለመሾም ያመልክቱ።
#ሲያመለክቱ እንደማስረጃነት የክትባት ወረቀት፣ የሀኪም ቤት የተወለደበት ማስረጃ እና የእምነት ተቋም ማስረጃዎችን ማያያዝዎትን አይርሱ።
#በማመልከቻው ላይ በምን ምክንያት ልጅዎን ወይም የልጅ ልጅዎን ለብቻዎ እያሳደጉ እንዳለ ሚያቀርቡት ምክንያት ማስረጃ ካለው እሱን ይጥቀሱ፤
ለምሳሌ ባለቤቴ ሞቷል ካሉ የሞት ሠርተፍኬት ወይም የፍርድ ቤት ውሳኔ፣ በሕጋዊ መልኩ ተለያይተው ከሆነ የፍቺ ውሳኔ፣ ወላጆቹ በሕይወት  ወይም በሥራ ምክንያት በአካባቢው ከሌሉ ምክንያቶችን ይጥቀሱ።
#ፍርድ ቤቱ ያለዎትን ማስረጃ እና ምስክሮች ከመረመረ በኋላ ለልጅዎ ሞግዚትና አሳዳሪ እንደሆኑ አረጋግጥዎ ማስረጃውን ይሰጥዎታል።
#ይህን ውሳኔ ይዘው በሚኖሩበት ወረዳ ለልጅዎ የልደት ሠርተፍኬት በማውጣት ለሚፈልጉት አገልግሎት ሊጠቀሙበት ይችላሉ።
የሞግዚትነት ሥልጣን ቅደም ተከተል
1. የልጁ ወላጅ አባትና እናት
2. የልጁ ወደላይ ሚቆጠሩ ወላጆች (አያቶች)
3. አካለ መጠን የደረሱ የልጁ ወንድሞች እና እህቶች
4. የአጎት ወይም የአክስት ልጆች
#አቤቱታውን ለማጻፍ አቅም ከሌለዎት በቴሌግራም በኩል ያናግሩኝ።
⚖️ይግባኝ መብት ነው!!!
©️ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
☎️ 09 10 61 69 50


በፍትሐ ብሔር ክርክር ሂደት ውስጥ ማንኛውም ሰው ከዚህ ቀጥሎ በተመለከቱት መንገዶች መብቱን ለማስከበር ፍርድ ቤትን ሊጠይቅ ይችላል።
1️⃣ከሳሽ በመሆን
#በግልጽ እንደሚታወቀው በፍርድ ሊወሰን የሚችልን ጉዳይ ሥልጣን ባለው የዳኝነት ሰጪ አካል በጽሑፍ ካሉ የሰነድ ማስረጃዎች እና የሰው ምስክሮች ዝርዝር ጋር በማድረግ በከሳሽነት ክስ በማቅረብ መብትን ማስከበር ይቻላል።
2️⃣ጣልቃ ገብ በመሆን
#በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 41 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ላይ በግልጽ እንደሰፈረው በጉዳዩ ላይ ከሳሽ ወይም ተከሳሽ ያልነበረ ነገር ግን የሚደረገው ክርክር መብትና ጥቅሙን የሚነካበት ማንኛውም ሰው እየተደረገ ባለው ክርክር ጣልቃ እንድገባ ይፈቀድልኝ ብሎ በመጠየቅ ክርክር እየተደረገበት ያለው ነገር የእርሱ ብቻ ወይም ክርክር እየተደረገበት ካለው ነገር ላይ ድርሻ ያለው መሆኑን በማስረዳት መብቱን ማስከበር ይችላል። ይህ መብት ማስከበሪያ የሚሰራው ፍርድ ከመሰጠቱ በፊት ከቀረበ ብቻ ነው።
3️⃣በሌለውበት የተሰጠው ፍርድ ይነሳልኝ በማለት
የፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 358
#ይህ መብት ማስከበሪያ መንገድ ክርክር እየተደረገበት በነበረው ጉዳይ ላይ ጣልቃ በመግባት መብቱን ለማስከበር ይችል የነበረ ነገር ግን ክርክሩ ስለመደረጉ እውቅና የሌለው እና ስለጉዳዩ ያወቀው ፍርድ ከተሰጠ በኋላና ከመፈጸሙ በፊህ የሆነ ሰው የሚጠቀመው መብት ማስከበሪያ ነው። ይህ መንገድ የተሰጠው ፍርድ ከመፈጸሙ በፊት የሚቀርብ መሆን አለበት።
4️⃣በተያዘ ንብረት ላይ መብትን ማስከበር
የፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 418
#ይህ መብት ማስከበሪያ መንገድ በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት ንብረት እንዳይያዝ በመቃወም የሚቀርብ ክርክር ነው። ይህ ዓይነቱ የመብት ማስከበሪያ መንገድ ለፍርድ አፈጻጸም ተብሎ በተያዘው ንብረት ላይ ተቀዳሚ መብት አለን የሚሉ እንደሆነ የሚቀርብ መብት ማስከበሪያ መንገድ ነው።
⚖️ይግባኝ መብት ነው!!!
©️ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
☎️ 09 10 61 69 50
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ




#በተጠረጠሩበት የወንጀል ጉዳይ በየትኛውም ፍርድ ቤት በዋስትና እንዲወጡ መወሰን ማለት መደበኛው ክስ በሚቀርብብዎት ጊዜ እቀርባለውኝ በማለት የሚሰጡት ማስተማመኛ እንጂ ክሱ ተዘግቷል ማለት አይደለም።
#የተጠረጠሩበት የወንጀል ድርጊት መታረቅንና መካስን የማይከለክል እንደዛም ማድረጉም ጥቅም የሚያሰጥዎ እንደሆነ በዋስትና እንደወጡ መደበኛው ክስ ሳይመሰረትብዎ ከተበዳይ ጋር ይታረቁ። ቅጣትዎን ለማስገደብ ወሳኝ ሚና አለውና።
#ልዩ ሁኔታ ካልገጠምዎ በስተቀር በወንጀል ጉዳይ የፍርድ ቤትን ቀጠሮ አይቅሩ! ቀጠሮ በቀሩና ከፍትሕ በሸሹ ቁጥር እራስዎት ላይ ቅጣትዎን ያከብዳሉ።
#በዋስትና ከወጡ በኋላ ከዓቃቤ ሕግ የወንጀል ክስ ቻርጅ (አቤቱታ) እንደደረስዎት ፍርድ ቤት ከመቅረብዎት በፊት ተገቢውን የሕግ ባለሙያ ሳያማክሩ ችሎት አይቀረቡ። የክስ ቻርጁ የደረስዎት ለማማከር በቂ ጊዜ በሌለበት እንደሆነ ጊዜ ይሰጠኝ ብለው ይጠይቁ።
#ከወንጀል እንዲሸሹ ወይም እንዳይቀጡ በማሰብ ሳይሆን ሕጋዊ መብትዎ እንዲጠበቅ በማሰብ ምን ምክንያቶች የወንጀል ቅጣትን እንደሚያስገድቡ ለማወቅ like, follow and share ያድርጉ!
⚖️ይግባኝ መብት ነው!!!
©️ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
☎️ 09 10 61 69 50
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ


#በእጅዎት የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪነት መታወቂያ የዕድሳት ጊዜው ያላለፈበት ቢሆንም እንኳን ወደ ወረዳዎት በመሄድ በዲጂታል መታወቂያ ይለውጡት!
#ዛሬ ነገ ሳይሉ የብሔራዊ መታወቂያ ወይም ፋይዳ መታወቂያ ያውጡ! አሁን አሁን ላይ ለግለሰብም ሆነ ለጠበቃ ውክልና ለመስጠት ቅድሚያ ፋይዳ መታወቂያ ግድ እየሆነ ነው። በወቅቱ ከመደናገር ቀድሞ መዘጋጀቱ አይመስልዎትም?
#የትኛውንም ዓይነት ውል በመገደድ ወይም በመታለል ወይም ሸማስፈራራት ፈርመው እንደሆነ ይህ መገደድ ወይም መታለል ወይም ማስፈራራቱ እንደቀረልዎ ውሉ እንዲፈርስልኝ በማለት በፍርድ ቤት ለመጠየቅ መብት እንዳለዎት አይርሱ። ይህን መሰል ጉዳይ ከገጠመዎ መልዕክትዎንና ጥያቄዎትን ይላኩ።
ይግባኝ መብት ነው!!!
#በወንጀል ጉዳይ ላይ በጊዜ ቀጠሮ ወይም በዋስትና አልያም በመደበኛ ክስ ሲቀርብብዎ ቢያንስ ቢያንስ ጠበቃ ለማቆም አቅም ቢያንስዎት ሕጋዊ ጉዳዩን ምክር እንዲጠየቅልዎ የቅርብ ሚሉትን ቤተሰብ ያናግሩ። ምክር ለማግኘት ደግሞ በየትኛውም ማኅበራዊ ሚዲያችን በነፃነት መጠየቅ መብትዎ ነው።
#እየተጠቀሙበትና እየሰሩበት ባለበት ንብረት ላይ ከሳሽም ተከሳሽም ባልሆኑበት የዕግድ አቤቱታ ከደረስዎ በክርክሩ ውስጥ ጣልቃ በመግባት መብትዎን ማስከበር ስለሚገባዎ ወዲያውኑ ባለሙያዊ ምክር ይጠይቁ እንጂ አልተከሰስኩኝ ምን አገባኝ!? ብለው ችላ ብለው አይቀመጡ።
⚖️ይግባኝ መብት ነው!!!
©️ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
☎️ 09 10 61 69 50
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ



20 last posts shown.