ባለፈው ሳምንት ከተሰጠው ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ የ Comprehensive Nursing ተፈታኝ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አቅርበዋል፡፡
ፈተናው ከBlue Print ውጪ መዘጋጀቱን እንዲሁም የጥያቄ መደጋገም መኖሩን የገለፁት ተፈታኞቹ፤ ትምህርት ሚኒስትር ቅሬታቸውን በማየት በአፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡
ከነርሲንግ ተማሪዎች ጋር ተያይዞ የትምህርት ሚኒስቴር እስካሁን ያለው ነገር የለም፡፡ ቲክቫህ ጥያቄውን ለሚኒስቴሩ ከፍተኛ አመራር ያቀረበ ሲሆን፤ የሚሰጡንን ምላሽ የምናቀርብ ይሆናል፡፡
በሌላ በኩል "ፈተናዎቹ ዘግይተው መሰጠት በመጀመራቸው የሰዓት ዕጥረት እንዲፈጠር ማድረጉ" እንዲሁም "የኔትወርክ እና የመብራት መቆራራጥ ችግሮች" ሌሎች በፈተናው ወቅት የታዩ ችግሮች እንደነበሩ ተፈታኝ ተማሪዎቹ ለቲክቫህ ገልፀዋል፡፡
እንደ ተንቀሳቃሽ ስልክ ያሉ የተከለከሉ ነገሮችን ወደ ፈተና ጣቢያ ይዞ ለመገባት መሞከር በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ማጋጠሙን መግለፃችን ይታወሳል፡፡
ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሞባይል ስልክ ሲጠቀሙ የተያዙ እና በመፈተኛ ክፍሎች ሞባይል ስልኮችን ይዘው የተገኙ 128 ተማሪዎችን ከፈተና ማዕከሉ እንዲሰናበቱ ማድረጉንና ውጤታቸው እንዲሰረዝ ማድረጉን አሳውቋል፡፡
የሀገር አቀፍ መውጫ ፈተና ውጤት ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ጥቂት ቀናት ይፋ እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡
ምስል፦ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ
📄
@Exitnewss