ማይክ ሐመር በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር በኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው።
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እንዳስታወቀው ልዩ መልዕክተኛው እስከ መጭው ማክሰኞ በኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ጉብኝት ያደርጋሉ።
በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታም ከመንግስት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ጋር በተደረሰው የሰላም ስምምነት አተገባበር ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የሽግግር ፍትህና ተጠያቂነትን የማስፈን ሂደትን እንዲሁም የትጥቅ ማስፈታት እና የመልሶ ማቋቋም ሂደቶችን ጨምሮ በሰላም ስምምነቱ በታዩ መሻሻሎች እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
ውይይቱ ከመንግስት የሥራ ሃላፊዎች እና ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር የሚካሄድ መሆኑም ነው የተገለጸው።
በጅቡቲ ቆይታቸውም በአፍሪካ የአሜሪካ ወታደራዊ ዕዝ እና የምስራቅ አፍሪካ የተቀናጀ የጋራ ግብረ ኃይል በጋራ በሚያስተናግዱት የምስራቅ አፍሪካ የደህንነት ፎረም ላይ ይካፈላሉ ተብሏል።
በተጨማሪም ከጅቡቲ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ ትብብር እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩም ነው የተገለጸው።
ከዚህ ባለፈም ከምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ዋና ፀሃፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ጋር ኢጋድ በሚያከናውናቸው ተግባራት ዙሪያም ይወያያሉ ነው የተባለው።