Risk Management በፎሬክስ ትሬዲንግ ውስጥ ለረጅም ጊዜ በስኬት ለመቆት Risk management ቁልፍ ነገር ነው። ምርጥ ስትራቴጂዎችን ብንጠቀም እንኳን ተገቢ የሆነ Risk management ከሌለን ሊከሽፉ ይችላሉ።
1.
Never Risk More Than 1-2% Per Trade
በአንድ ትሬድ ከ1-2% በላይ በጭራሽ Risk እንዳታረጉ!📌 በአንድ ትሬድ ላይ ከትሬዲንግ ካፒታላቹህ ትንሽ ፐርሰንት ብቻ ነው Risk ማድረግ ያለባቹህ።
#ለምሳሌ 1,000$ አካውንት ካላቹህ፣ 1% Risk ብታረጉ በእያንዳንዱ ትሬድ ከፍተኛ ኪሳራቹህ የሚሆነው $10 ማለት ነው።
ይህም ለምን ይጠቅማል ካላቹህ ተከታታይ ኪሳራዎች ካጋጠሙን ካፒታላችንን ለመጠበቅ ይረዳል።
2.
Use stop loss and take profit
ትርፍና ኪሳራህን ግታ
📌
Stop loss (SL) ትሬድ ስታረጉ በዚህ ትሬድ ከዚህ በላይ አልከስርም ብላቹህ የምታስቀምጡበት ቦታ ነው።
Example 1% ኪሳራ ከፈቀዳቹህ ማርኬቱን ኪሳራቹህ 1% ሲደርስ limit ታረጉለታላቹህ።
📌
Take profit (TP) ትርፍ መውሰጃ ማርኬቱ ትርፍ እናመጣበታለን ወዳልንበት አቅጣጫ ሲሔድና ያቀድነውን ሲነካልን Take profit እንለዋለን። ሁልጊዜም ቢሆን መርሳት የሌለብን ኪሳራችንን እንደምንገድበው ሁሉ ትርፋችንም የተገደበ መሆን አለበት።
3.
Risk Reward ratio(RRR)
የትርፍና ኪሳራ ምጥጥን ሲሆን ከላይ እንደለፅኩላቹህ 1% risk ካደረግን 2% profit አድርገን መግባት እንችላለን። 1:2 ይህ ratio አንድ ፎሬክስን የተማረና በበቂ ሁኔታ የተለማመደና ማርኬቱን የተረዳ ሰው በቀላሉ የሚያገኘው ሲሆን እንዳስፈላጊነቱ Reward and risk የምናደርገውንም መለዋወጥ ይቻላል።
#ምሳሌ፡ 1:2 ብንገባ እና 1000$ አካውንት ቢኖረን $10 Risk አደረግን ማለት ነው። ስለዚህ ኪሳራ ቢመጣ 10$ እናጣለን ማለት ነው። በተቃራኒው ደግሞ $20 ትርፍ እናገኛለን ማለት ነው።
1:3 ብንገባ ኪሳራ 👉 10$
ትርፍ 👉 30$
✍️ አደራቹህን እንዳትስገበገቡ ትልቅ ደረጃ እስከምትደርሱ ድረስ 1:2 RRR በቂ ነው። በተለይ ጀማሪዎች ማርኬቱ ላይ ለመቆየት ነው ጥረት ማድረግ ያለባቹህ በመስገብገብ ካፒታላቹህን 0 እንዳታረጉት።
4.
ስሜታቹህን ተቆጣጠሩ የበቀል ንግድን አስወግዱኪሳራ በሚገጥማቹህ ጊዜ ስሜታዊ ሁናቹህ ኪሳራቹህን ለመመለስ በችኮላ ትሬድ አታድርጉ። ለምን ኪሳራ እንዳጋጠማቹህ የገባቹህትን ትሬድ በደንብ አጥኑት፣ ከስህተታቹህ በመማር ለሌላ ጊዜ ማስተካከል አለባቹህ።
መርሳት የሌባቹህ ነገር በፎሬክስ ትሬዲንግ አለም ኪሳራ ግዴታ ነው። በተከታታይ መቁጠር እስከሚሠለቻቹህ ድረስ ልትከስሩ ትችላላቹህ። ይህ የፎሬክስ እውነታ ነው ከእናንተ የሚጠበቀው ከስህተታቹህ በመማርና ማርኬቱን በማጥናት በበቂ ሁኔታ ልምምድ ማድረግ ነው።
✅ ስግብግብነት ያገኛቹህትን ያሳጣቹሃል። ሁልጊዜ ቢሆን መጀመሪያ ታርጌት ያደረጋቹህበት ቦታ Take profit ሲነካ ውጡ። እናንተ ተስገብግባቹህ ወደ Take profit ሲጠጋ እናንተም የምታስጠጉ ከሆነ እመኑኝ ያገኛቹህትን ታጣላቹህ። በቃ የመጀመሪያ እቅዳቹህ ከተሳካ እሱ በቂ ነው!
በቀጣይ ስለ Risk management ተጨማሪ ነገር ይኖረናል። ለዛሬ እዚህ ጋር አበቃሁ።
ያልገባቹህ ነገር ካለ comment 👇Share for your friends
@fast_forex1 @fast_forex1@fast_forex1 @fast_forex1