FastMereja.com


Channel's geo and language: Ethiopia, AmharicChannel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ሃላፊዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ሃላፊዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በሙስናና በሃብት ምዝበራ ተጠርጥረው ነው። በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ሀብታሙ አበበ (ዶ/ር) እና ምክትል ፕሬዚዳንቱ ታምራት ታገሰ (ዶ/ር) ይገኙበታል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በዩኒቨርሲቲው የሀብት ምዝበራ ላይ ያተኮረ የምርመራ ዘጋቢ ፊልም ማቅረቡ ይታወሳል።


ሙሴቬኒ ወጣቶቹን በእሳት አትጫወቱ አሉ
#FastMereja
በኡጋንዳ የተቃውሞ ሰልፍ የጠሩ ወጣቶች "በእሳት አትጫወቱ" የሚል ማሳሰቢያ ከፕሬዝዳንቱ ደረሳቸው። የኡጋንዳ ወጣቶች በመንግሥት ደረጃ የሚስተዋለውን ሙስና ለማስቆም በማኅበራዊ ሚዲያዎች የሰልፍ ጥሪ ሲያስተባብሩ ታይተዋል።

ፕሬዝዳንቱ በቴሌቪዥን በተላለፈ መልዕክታቸው የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ያሰቡ ሰዎችን እንደማይታገሱ ተናግረዋል። ከማስጠንቀቂያቸው በተጨማሪም የተቃውሞ ሰልፍ አዘጋጆች “ከውጭ ኃይሎች ጋር እየሠሩ” ኡጋንዳን ሊበጠብጡ ነው ሲሉ ኮንነዋል።

ይሁንና ሙሴቬኒ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል ሲል ቢቢሲ በዘገባው ጠቅሷል ሲል አራዳ ሬዲዮ ነው ያስነበበው።
በኮድ 2 ተሽከርካሪ ራይድ መጀመሩን ዛይ ራይድ አስታወቀ
#FastMereja
ዛይ ራይድ የኮድ 2 መኪኖች ወደ ስራ የማስገባት ፕሮፖዛል በመንግስት ተቀባይነት ማግኘቱን ዛሬ ሐምሌ 13/2016 ዓ.ም የዛይ ራይድ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሐብታሙ ታደሰ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።

በአዲስ አበባ የሚታየውን የትራንስፖርት እጥረት ለመቅረፍ ዛይ ራይድ እንደ መፍትሄ የኮድ 2 የቤት መኪኖች በተመጣጣኝ ዋጋ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ እንደሆነ ከአራት ወር በፊት ፕሮፖዛላቸውን ለሚዲያ አቅርበው ነበር። አሁን ፕሮፖዛሉ ተቀባይነት አግኝቶ የኮድ 2 ተሽከርካሪዎችን መመዝገብ መጀመራቸውን ገልጿል።

የኮድ 2 ትራንስፖርት አገልግሎት እስከ 75% ለህብረተሰቡ ቅናሽ ያለው፣ ለአሽከርካሪ ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኝ፣ ለመንግስት እስከ 6 ቢሊዮን ብር ገቢ እንደሚያስገኝ አቶ ሀብታሙ ታደሰ ተናግሯል።

40ሺ መኪኖችን ለመመዝገብ እቅድ እንዳላቸው፣ ምዝገባ መጀመሩን ተገልጿል።

የኮድ 2 ባለንብረቶች በምን መልኩ ተመዝግበው ወደ ስራ መግባት እንደሚችሉ፣ ምን ማሟላት እንደሚገባ ተጨማሪ የቪዲዮ ማብራሪያ ተመልከቱ
👇👇
https://youtu.be/GJX84hJ1ihg?si=DSaAxxWc3GHvTTRv


ጀግናው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ አፍሪካዊ ስፖርተኛ ተባለ::

ኢኤስፒኤን (ESPN) የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ 10 ታላላቅ አፍሪካውያን ስፖርተኞችን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ኢትዮጵያ እና ኬኒያ ሁለት አትሌቶችን በማስመረጥ ቀዳሚውን ደረጃ ይዘዋል።

ኢትዮጵያዊው የረጅም ርቀት ሯጭ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ቀዳሚውን ደርጃ ሲይዝ ኬንያዊው የረጅም ርቀት ሯጭ ኤሉድ ኪፕቾጌ ሁለተኛ ደረጃን ይዘዋል።

በሴቶች የዚምቧብዌዋ የዋና ስፖርት ተወዳዳሪ ክርስቲ ኮቨንትሪ ቀዳሚውን ደረጃ ስትይዝ ኢትዮጵያዊቷ የረጅም ርቀት ሯጭ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በሴቶች ሁለተኛ በሁለቱም ጾታ ደግሞ አምስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችላለች።


“እንደ ተገለጸ መጽሐፍ የሚያነበኝ ይህ መነኩሴ ማነው?”

በሰሜን ምስራቅ ግብጽ በአባይ ወንዝ አቅራቢያ ባለው ዛራቢ አል-ሙራቅ የተባለ ስፍራ በ1899 ዓ.ም የተወለዱት አባ ዮስጦስ በቤተ ክጋርስቲያኒቱ ዝምተኛው መነኩሴ በመባል ይታወቃሉ፡፡ ጸሎታቸውም፣ ኑሯቸውም ዝምታ ይበዛበታል፡፡ በቅዱስ እንጦንስ ገዳም ሲኖሩም አዳፋ ልብሳቸው ብዙዎች ስለእርሳቸው የተሳሳተ ግምት እንዲኖራቸው አድርጓል፡፡ እርሳቸው ግን የተሰውረውን ሁሉ የሚያውቁ ታላቅ ጻድቅ ነበሩ፡፡

የቅዱስ እንጦንስ ገዳምን በረከት ለማግኘትና ለመሳለም የሚሔዱ ምዕመናን ለገዳሙ የተለያዩ ስጦታዎችን ይወስዱ ነበር፡፡ ሰው ምንም ያህል ቢሰጥ የነፍሱን ያሕል አይሆንምና ለገዳማውያኑ ጥቂት ነገር ሰጥቶ ስጋዊና መንፈሳዊ በረከት ያገኝ ነበር፡፡

ታዲያ በዚህ ገዳም ሁለት በልዩነት የሚታወቁባቸው አባባሎች አሏቸው፡፡ በክርስትናው ደከም ያለውንና ለስጋው ብቻ የሚያስበውን የሚያነቁበት “አሁን ስንት ሰዓት ነው?” እና በክፉም በደጉም መታመናቸውን የሚያሳዩበት “እግዚአብሔርን አመስግኑ” የሚሉ፡፡

አንድ ቀን አንድ ሞልቶ የተረፋቸው ሐብታም ነጋዴ ለገዳማውያኑ ይሆናሉ ያሏቸውን በርካታ ስጦታዎች ይዘው ወደ ቅዱስ እንጦንስ ገዳም ይሔዳሉ፡፡ ድንገት ከዚያ በፊት የትም አይተዋቸው የማያውቁት አንድ አዳፋ ልብስ የለበሱ ቀጭን መነኩሴ መጥተው ሀብታሙን ሰው እየጎተቱ ወስደው በገንዘብ ሽፋን የሚሰሩትን ኃጢአት ዘክዝከው በመንገር ንስሐ እንዲገቡ ነገሯቸው፡፡

ሰውየውም “እንደ ተገለጸ መጽሐፍ የሚያነበኝ ይህ መነኩሴ ማነው?” አሉ፡፡ ዝምተኛው መነኩሴ አባ ዮስጦስ መሆናቸውንም ተረዱ፡፡ ይዘው በሔዱት ስጋዊ ሀብት የዘለዓለም ድህነት የሚያገኙበት የንስሐ ጥሪ ሰሙ፡፡
ገዳማውያንን ስንረዳ ሔደን ስንጎበኝ ዓለም የማትሰጠንን የነፍስ መዳን እናገኛለን፡፡ ልክ እንደ አባ ዮስጦስ “አሁን ስንት ሰዓት ነው?” የሚሉን ገዳማውያን አባቶች በችግር እንዳይበተኑ፣ ጸሎታቸው እንዲጠብቀን እጃችንን እንዘርጋ፡፡ የገዳማውያኑ በረከትና ጸሎት አይለየን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ :-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አድነት  ገዳም

                ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
                 1000442598391

                        ወይም

                   አቢሲኒያ ባንክ
                   141029444


ለተጨማሪ መረጃ:- 
   የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957     
                         ወይም 0938644444
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ የሆነውን የሰው ልጅ በእናትነት እቅፏ ታቅፋ ዘወትር ስለልጆቿ ለምትማፀነው ፣ የህይወት ውሀ ምንጭ  የሆነው ወንጌልን የሚወዱ ፍለጋ ሳይሰደዱ ፣ እናት ቤተክርስቲያን ለዘመናት የጠበቀቻቸውን ልጆቿን ሳታጣ  ከአስራታችን ፣ ከዕለት ቁርሳችን በመስጠት የሐዋርያት መሰብሰቢያ የጻድቃን ከተማ የሆነችውን ቅድስት ቤተክርስቲያንን እንታደግ።

ድጋፍ ለማድረግ :-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አድነት  ገዳም

                        ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
                        1000442598391

                               ወይም

                        አቢሲኒያ ባንክ
                        141029444


ለተጨማሪ መረጃ:- 
   የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957     
                         ወይም 0938644444


“የሰው ልጅ ሆይ ወደ ደቡብ አቅና” በሚል መሪ ሐሳብ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ
#FastMereja
የደቡብ ኦሞና የአሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት “የሰው ልጅ ሆይ ወደ ደቡብ አቅና” በሚል መሪ ሐሳብ ከሐምሌ 15 እስከ ነሐሴ 30 ድረስ የሚቆይ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮጀክት ቀርጾ ወደ ተግባር መግባቱን ዛሬ ሐምሌ 12/2016 ዓም በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።

አካባቢው ጠረፋማ ከመሆኑ የተነሳ ትኩረት የሚሻ አካባቢ ከመሆነም በላይ ከሌሎች የአገራችን ክፍሎች አንጻር ከስልጣኔ እና ከእድገት ወደኋላ የቀረ ቢሆንም በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሥራዎች ለም የሆነ መሬት እና መልካም አጋጣሚዎች ያሉ በመሆኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረስብከት ሐዋርያዊ አገልግሎትን ከማስፋት በተጨማሪ ምዕመኑን ተጠቃሚ የሚያደርግና የዞኖቹን የልማት ሥራዎች የሚደግፍ ፕሮጀክቶች ቀርፆ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ ተነግሯል።

ይህንን ሥራ በይበልጥ ለማከናወን በሀገረ ስብከቱ ከፍተኛ አቅም ያላችው ሁለት ገዳማትንና እነዚህ ገዳማትን ጨምሮ በሌሎች አብያተ ቤተ ክርስትያናት ላይ ለአካባቢው ህብረተሰብ የሚጠቅሙ መንፈሳዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ የልማት ሥራዎች ለማጠናከር የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ማከናወን አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱ ተገልጿል።

በገቢ ማሰባሰቢያው ፕሮጀክት ከተካተቱት መካከል

• የ100 ብር፣ 250 ብር፣ 500 እና 1,000 ብር ዋጋ ያላቸው አንድ መቶ ሺ ትኬቶችን በአዲስ አበባ በሚገኙ ገዳማት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት፣ ማህበራትና የንግድ ተቋማት በኩል በማሰራጨት ምዕመናን እንደ አቅማቸው ተሳታፊ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡

• የክፍያ መተግበሪያ አማራጮችን በመጠቀም የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎችንና የአሐዱ ባንክ የድጋፍ መለገሻ መተግበሪያን (Donation App) ጭምር በመጠቀም በርካቶች ባሉበት ሆነው E-ticket በመግዛት ድጋፍ የሚያደርጉባቸው የበይነ መረብ የገቢ ማሰባሰቢያ ከሐምሌ 15 ጀምሮ ክፍት የሚሆን ሲሆን በበይነ መረብ ማሰባሰቢያ መንገድ ተደራሽ መሆናል።

• ሐምሌ 27 እና 28/2016 ዓ.ም በቦሌ ደብረ ሰላም መድኃኔአለም ቤተክርስቲያን የሀገረ ስብከቱን ታሪክ፣ የስብከተ ወንጌልና የልማት ስራዎችን የሚያስቃኝና የልማት ውጤቶችንና ሥራዎች ለገበያ የሚቀርቡበት አውደ ርዕይ የሚካሄድ ሲሆን ሐምሌ 28 ማታ ብጹዓን አባቶች፣ ሰባክያነ ወንጌሎችና ዘማሪያን የሚሳተፉበት ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በቤተክርስቲያኑ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

• ከዚህም ባሻገር በነሐሴ ወር መጨረሻ ብጽዐን አባቶች፣ የሀገረ ስብከት ኃላፊዎች፣ የገዳማትና የአድባራት ደብር አስተዳዳሪዎች፣ ባለሀብቶች፣ የንግድ ተቋማት የሚሳተፉበት የእራት መርሃ ግብር የሚካሄድ ይሆናል፡፡

በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናት አባቶችና ማኅበረ ምዕመናን ለዚህ በርካቶች የሚያሳትፍ በጎ ተግባር በኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ልማት ለሚያሳድግ ታላቅ መንፈሳዊ አገልግሎት መሳካት ከላይ የተጠቀሱትን የገቢ ማሰባሰቢያ መንገዶችን በመጠቀም ከቤተክርሰቲያን ጎን እንድትቆሙ በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም ጥሪ ቀርቧል።

የደቡብ ኦሞና የአሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና ከአዲስ አበባ 735 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኝ በጅንካ ከተማ ላይ ይገኛል፡፡

ጋዜጣዊ መግለጫውን ያስተባባረው ሎዛ ኦርቶዶክሳዊ ኹነቶች አዘጋጅ ነው።

📷 FastMereja / ጥላሁን ደሳለኝ
የተሽከርካሪ ቀረጥና ታክስ አወሳሰን

ተሽከርካሪ ወደ ሀገር ሲገባ ቀረጥና ታክስ የሚታሰበው ተሽከርካሪው ዓይነት (የቤት አውቶሞቢል፣ የህዝብ ማመላለሻ ወይም የዕቃ ማመላለሻ፣ ልዩ ልዩ) የተሸከርካሪውን የመጫን አቅም (የሰው ብዛት፣ የጭነት ኪሎ መጠን)፣ ጉልበት (ለቤት አውቶሞቢሎች) መሰረት በማድረግ እንዲሁም CIF (የተገዛበት ዋጋ + የትራንስፖርት ወጪ + የኢንሹራንስ ወጪ እና ሌሎች ወጪዎችን ጨምሮ) በሚገኘው ጠቅላላ ወጪ ነው፡፡

ተገጣጥመው ወደ ሀገር የሚገቡ አዲስ የቤት አውቶሞቢል ተሽከርካሪዎች ጉልበታቸው እስከ 1300 ከሆነ 75.67%ሲሆን ጉልበታቸው ከ1301 እስከ 1800 ደግሞ 116.79% እንዲሁም ከ1800 በላይ ጉልበት ያላቸው ከሆኑ ደግሞ 231.9% አጠቃላይ የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ምጣኔ ተጥሎባቸዋል፡፡

ሹፌሩን ጨምሮ እስከ 16 የመቀመጫ አቅም ያላቸው የሰው ማጓጓዣዎች እና እስከ 1.5 ቶን እቃ የመጫን አቅም ያላቸው የእቃ ማጓጓዣዎች አጠቃላይ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ 52.5% ሲሆን ከ16 ሰው በላይ የሚጭኑ የህዝብ ማመላለሻዎች እና ከ1.5 ቶን በላይ እቃ የሚጭኑ ተሽከራካሪዎች ደግሞ 29.5% አጠቃላይ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ ተጥሎባቸዋል፡፡

በሌላ በኩል ሀገር ውስጥ ለመገጣጠም በአምራች ድርጅቶች ወደ ሀገር የሚገቡ ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የተበተኑ (CKD/SKD) የሆኑ ተሽከራካሪዎች በተመለከተ በአዲስ ይዞታ ተገጣጥመው ወደ ሀገር ከሚገቡ ተሽከራካሪዎች በተለየ በዝቅተኛ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ የሚስተናገዱ ሲሆን በተቃራኒው ያገለገሉ(USED) ተሽከራካሪዎች ደግሞ ከፍተኛ የኤክሳይዝ ታክስ ስለተጣለባቸው በአዲስ ይዞታ ከሚገቡ ተሸከራካሪዎች በአንፃራዊነት በጣም ከፍተኛ አጠቃላይ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ አላቸው፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር


የደብረ ብረሃን ዩኒቨርስቲ የባህል፣ የታሪክና የቋንቋ ማዕከል እንደገና ሊያደራጅ ነው።
#FastMereja
ዩኒቨርሲቲው የሚገኝበት የሰሜን ሸዋ አካባቢ የቱባ ባህል ባለቤት፣ የኢትዮጵያ የረዥም ጊዜ ታሪክና ፖለቲካ ማዕከል እንዲሁም የአማርኛ ቋንቋና ስነፅሁፍ መፈጠሪያ እንደመሆኑ መጠን እነዚህን የማህበረሰብ ህልውና መሰረቶች የዩኒቨርሲቲው ዋነኛ ተግባራት መሆን እንዳለባቸው ከማህበረሰቡ በተደጋጋሚ ጥያቄዎች ሲነሱ አስተያየቶችም ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡ በመሆኑም፡-

1. ካለን ተሞክሮ በመነሳት ከዚህ በፊት የነበረዉን የባህል ማዕከል የበለጠ ለማጠናከርና ለማስፋት ታሪክንና የአማርኛ ቋንቋን በማካተት አንድ ማዕከል ማቋቋም አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት የባህል፣ የታሪክና የቋንቋ ልማት ማዕከል ሆኖ እንደገና እንዲቋቋም ተወስኗል።

2. የሚቋቋመው ማዕከል ተልዕኮ የአካባቢውን ባህል፣ ታሪክና እና የአማርኛ ቋንቋ ስነፅሁፍ ማስተማርና ማጥናት ላይ ያተኩራል።

3. የአማርኛና የታሪክ ትምህርት ፕሮግራሞች ለተማሪ ምርጫ ቀርበዉ ዩኒቨርሲቲዉን ሌጅስሌሽን (Legislation) ላይ የተቀመጡን ዝቅተኛ የተማሪ ቁጥር ማሟላት የሚችሉ ከሆነ በመጀመሪያ፣ ሁለተኛና ሦስተኛ ድግሪ እንዲማሩ ይደረጋል፡፡

4. ከላይ በተራ ቁጥር 3 በተጠቀሱት ትምህርት ክፍሎች ዉስጥ ያሉ መምህራን ከማስተማር ስራቸዉ ጎን ለጎን የማዕከሉ ተመራማሪ በመሆን ያገለግላሉ፡፡

5. ማዕከሉ በዳሬክቶሬት ደረጃ የሚቋቋም ሆኖ አንድ ዳይሬክተር እና በስሩ የአማረኛ ቋንቋና የታሪክ ዘርፍ አስተባባሪዎች ይኖሩታል፡፡


አፋር እና ሶማሌ ክልሎች በአዋሳኝ አካባቢዎች የሚከሰቱ ግጭቶችን በዘላቂነት ለመፍታት መስማማታቸውን አስታወቁ
#FastMereja
በአፋር እና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶችን በውይይት በዘላቂነት ለመፍታት ከስምምነት መደረሱን የየክልሎቹ ርዕሳነ መስተዳድሮች ገለጹ።

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ “አልፎ አልፎ እየተነሳ ያለውን ችግር ከስር መሰረቱ ለመፍታትና ተመልሶ እንዳይነሱና የሰው ሕይወት መጥፋት ስለሌለበት ስምምነት መደረጉን” አረጋግጠዋል።

በሰኔ ወር በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ በተቀሰቀሰ ግጭት በርካታ ሰዎች መሞታቸውን እንዲሁም መፈናቀላቸውን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል።
መካኒኩ የጋራጅ ሰራተኛ የ7ሚሊዮን ብር ዕድለኛ ሆነ!
#FastMereja
የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሰለሞን ደበበ በልዩ-2 ሎተሪ በ1ኛ ዕጣ የ7 ሚሊየን ብር ቼካቸውን ተረክበዋል ፡፡ አቶ ሰሎሞን በጋራጅ ውስጥ የመካኒክ ባለሙያ ሲሆኑ በደረሳቸውም ገንዘብ ሥራቸውን ለማስፋፋት ማቀዳቸውን ገልፀዋል።
***
ትክክለኛው የቴሌግራም ገጻችን ይህ ነው 👇
https://t.me/fastmereja
https://t.me/fastmereja


የቢሾፍቱ ከተማ መስተዳደር የኢትዮጵያ ወንገል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካዉንስልን አስጠነቀቀ
#FastMereja

በሀይማኖት ሽፋን በሚዲያ አጀብ በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ላይ እየተካሄደ ያለዉን የስም ማጥፋት ዘመቻ ለማስቆም የተሰጠ አጭር ማሳሰቢያ ብሎ ባወጣው መግለጫ

በሕገ-ወጥ መንገድ ረዘም ላለ ጊዜ ሳይለማ የቆየ 280,000 ካሬ ሜትር ለልማት እንዲውል ማድረግ ሕገ- መንግስትን ማስከበር እና ማክበር እንጂ የሚያስወቅስ ጉዳይ አይደለም ብሏል መስተዳደሩ በመግለጫው።

ከዚህ ውጪ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ሕግ እና ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን ማስከበር የአንድ የመንግስት ኣካል ሃላፊነት ሆኖ እያለ ለ40 ዓመታት ያለ ልማት ያለ ህዝብ ጥቅም) የቆየ 280,000 ካሬ ሜትር ስኩዌር የህዝብ እና የቀጣይ ትውልድ ውስን ሐብትን በሕገ -ወጥ መንገድ በየትኛውም መንገድ በሚዲያ ጫናም ሆነ በጉልበት ይዞ መገኘት ወንጀል ነው ብሏል አስተዳደሩ።

በቢሾፍቱ ከተማ ኩርፍቱ ሃይቅ ዙርያ የሆነው እንደሱ ነው። ይህንን መነሻ በማድረግ የከተማ መስተዳድሩ የመንግስት እና የህዝብ ዉስን ሃብትን የመጠበቅ ፥የማስተዳደር እና ለልማት እንዲዉል የማድረግ ህዝባዊ፧ መንግስታዊ ግደታ እና ተጠያቂነት አለበት ። በመሆኑም ተደጋግሞ የሚደረግብን የሚዲያ ጥላቻ እና ዘመቻ የህዝብን ጥቅም ከማረጋጋጥ ጉዞዋችን ቅንጣት የማይገታን መሆኑን ልናሳውቅ እንወዳለን።

ይሀ እንዳለ ሆኖ የከ/መስተዳድሩ ይህንን መሬት ለልማት ኢንዳያዉል በሃይማኖት ሽፋን ሕገ- ወጥ ሁከት እና ዘመቻ እያደረጋችሁ ያላችሁ አካላት በሙሉ ከድርጊታቸሁ እንድትታቀቡ ኢያሳሰብን ከዚህ ውጪ በሚደረገዉ በማንኛውም እንቅስቃሴ ላይ የሕግ-የበላይነት ለማስከበር የምንገደድ መሆኑን እናሰምርበታለን።

የኢትዮጵያ ወንገል ኣማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካዉንስል ይሀንን ተረድተዉ የተጀመረውን ሃገራዊ እና የሕዝቦችን ተጠቃሚነት ጉዞ የሚያደናቅፍ የሚዲያ ዘመቻውን እንድያቆምልን እንጠይቃለን ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
በአዲስ አበባ በስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓት፤ የኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ ሊደረግ ነው፡፡

በከተማዋ ጠዋትና ማታ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ የኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲቀሳቀሱ ሊደረግ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ለሸገር ተናግሯል፡፡

ጎዶሎ ቁጥር እና ሙሉ ቁጥር የኮድ 2 ተሽከርካሪዎችን በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ የሚያደርግ የህግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቷል ያሉት በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የትራፊክ ቁጥጥርና ሁነት አስተዳደር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አያሌው እቴሳ ናቸው፡፡

እቅዱ በ2 እና በ3 ወር ጊዜ ውስጥ፤ በከተማው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኮድ 2 ተሽከርካራች በፈረቃ አንዲንቀሳቀሱ ይደረጋል ተብሏል፡፡

የኦሮሚያንና የፌዴራልን ታርጋ ሳይጨምር የአዲስ አበባ ታርጋ ብቻ ያላቸው ተሽከርካሪዎች ከ755,000 በላይ ናቸው ያሉት አቶ አያሌው ከእነዚህ ውስጥ የበዙት ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በመሆናቸው ነው ጠዋትና ማታ በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ የሚደረገው ሲሉም ለሸገር ተናግረዋል፡፡


በዘንድሮ መልካም ወጣት 30ሺ ወጣቶችን ለማሰልጠን ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለፀ
#FastMereja
የኢትዮጲያ አዲስ ኪዳን ካህናት ቤተ-ክርስቲያን "በመልካም ወጣት" በሰባት አመት 180ሺ ወጣቶችን ማሰልጠን እንደተቻለ ፓስተር ዮናታን አክሊሉ ዛሬ ሐምሌ 09/2016 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል በሰጠው መግለጫ ተገልጿል።

ቤተ ክርስቲያኗ በየአመቱ የምታካሂደው የመልካም ወጣት መርሃ ግብር ዘንድሮም "መልካም ወጣት ወደ ብርታት" በሚል መሪ ሃሳብ በዚህ አመትም 30ሺ ወጣቶችን በሐዋሳ ለማሰልጠን እንደተዘጋጁ ፓስተር ዮናታን ገልጿል።

በሐዋሳ ከተማ ከ1.2 ቢሊዮን ብር እየተገነባ የሚገኘው የመልካም ወጣት ማዕከል ግንባታ 70 በመቶ መድረሱን ፓስተር ዮናታን ተናግሯል፣ ቀሪው በሁለት አመት ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ብሏል።

በተጨማሪም በወላይታ ሶዶ የኢትዮጵያ አዲስ ኪዳን ካህናት ቤተ ክርስቲያን በ100ሺህ ካሬ ላይ ያረፈ በ500 ሚሊዮን ብር ጥራቱን የጠበቀ በሱስ የተጠቁ ወጣቶች የማገገሚያ ተቋም የሚሆን እና ለመቶ ሺዎች ተደራሽ መሆን የሚችል የሆስፒታል ግንባታ እንደተጀመረ በመግለጫው ላይ ተነግሯል።

በዘንድሮ መልካም ወጣት ምዝገባ ለአንድ ሰው 1,500 ብር መሆኑ ተገልጿል።

📷 FastMereja / ጥላሁን ደሳለኝ

የመግለጫው ቪዲዮ
👉 https://youtu.be/ob8vVIFyh6U?si=M3ZGFbEuEwfH3BpE

የመግለጫው ቪዲዮ
👉 https://youtu.be/ob8vVIFyh6U?si=M3ZGFbEuEwfH3BpE


"ባካሄድነው ጥናት 90 በመቶ ተማሪ ኮራጅ መሆኑን ደርሰንበታል"- አለማየሁ ተ/ማሪያም (ዶ/ር)
#FastMereja
በኢትዮጵያ የኩረጃ ደረጃ ምን ያህል ነው? ሀገርንስ ምን ያህል ይጎዳል? በሚል በ2004 በተደረገ ጥናት 90 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ኮራጅ መሆናቸው ተረጋግጧል ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአካቶ ትምህርት ክፍል ተመራማሪ የሆኑት አለማየሁ ተ/ማሪያም (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡

ተመራማሪው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዳጉ ፕሮግራም በነበራቸው ቆይታ፤ በቀደመው የትምህርት ሥርዓት የመመዘኛ ፈተናዎች የሚሰጡበት ሂደት ለኩረጃ ምቹ እንደነበሩ ተናገረዋል፡፡

ተማሪዎች በፈተና ወቅት የማያውቁትን ጥያቄ መልስ ከሌሎች ለመቅዳት ድሮም ይሞክሩ እንደነበር ገልጸው፤ አሁን ላይ ሥር ሰዶ በዘመቻ መል የሚካሄድ ሆኗል ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡

ተማሪዎች ከትምህርቱ በበለጠ የኩረጃ መንገዶችን ያጠናሉ የሚሉት ተመራማሪው፤ በጥናቱ 27 የሚሆኑ የኩረጃ ዘዴዎች እንዳሉ ደርሰንበታል ብለዋል፡፡

በዚህ ሂደት ውስጥ ተማሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ወላጆች ልጆቻቸው እንዲያልፉ ከመፈለግ አንፃር እንዲሁም መምህራን፣ ርዕሰ መምህራን፣ የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጭምር ለኩረጃው እገዛ እንደሚያደርጉ ይናገራሉ፡፡

ይህም ፈተናውን አልፈው ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ተማሪዎች የሥብዕና ጉድለት እንደሚታይባቸው እዲሁም መሰረታዊ የሆነው መፃፍ እና ማንበብ ሲቸግራቸው እንመለከታለን ይላሉ፡፡

ተመራማሪው፤ ከፈተና አሰጣጥ በተጨማሪ ለግምት አጋላጭ የሆኑ የፈተና ዓይነቶችን ለማስተካከል መስራት እንደሚገባ አዲሱ የፈተና ሥርዓት ያመላከተ መሆኑንም ይናገራሉ፡፡

በተለይም የተጀመረው የበይነ በረብ (ኦን ላይን) ፈተና አሰጣጥ ሲጠናከር የተንሰራፋውን የኩረጃ መጠን በመቀነስ እና ተማሪዎችን በማብቃት ረገድ ላቅ ያለ ሚና ይኖረዋል ነው ያሉት፡፡

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ከ700 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች ከሐምሌ 3 ጀምሮ እስከ ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡

ዘገባው የኢቢሲ ነው።

20 last posts shown.