ከሐዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የተሰጠ መግለጫ እና አጠቃላይ የምርመራ ሂደት
የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የከተማው ማህበረሰብ ሰላምና ደሕንነት ማስጠበቅ ቀዳሚ ተልዕኮው እንደሆነ ይታመናል። በዚህም መምሪያው በርካታ ስራዎች እየሰራ ይገኛል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የከተማችን ነዋሪ በሆነችው ወ/ሪት ፀጋ በላቸው ላይ የደረሰባት የጠለፋ ወንጀል ጉዳዩን አስመልክተው ቤተሰቦቿ በእለቱ ለመናኸሪያ ፖሊስ በመቅረብ አቤቱታቸውን አሰምተዋል።
ይህን ተከትሎም መምሪያችን ተፈፀመ ብሎ ባለው ወንጀል መሰረት ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ብርቱ ክትትል እያደረገ ይገኛል።
የችግሩን አሳሳቢነት በመገንዘብ መምሪያችን ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ጭምር አስፈላጊውን ጥረት እያደረገም ነው የሚገኘው።
ይህነን አስመልክቶ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የተበዳይ ቤተሰብ በትዕግሥት እንዲጠብቀው በመጠየቅ ጭምር ነው በዋና አዛዡ ረዳት ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ አማካይነት መግለጫ ሰጥቷል።
ማንም ሰው ከህግ በታች መሆኑን የሚያምነው የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ ይህ ሆኖ ሳለ ግን በአንዳንድ ማህበራዊ የሚዲያ ተቋማት ከሚሰራጩ አሉባልታዎች የተበዳይ ቤተሰብም ሆነ ህዝቡ ሳንደናገር እንዲጠብቅ እና ለፖሊስ መረጃ በመስጠትና ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ያቀርባል።
የምርመራ ሂደት ባጭሩ ለመግለፅ ያህልም
የወንጀሉ ድሪጊት የተፈፀመው በሀዋሳ ከተማ በመናኸሪያ ክ/ከተማ ሲሆን ወ/ሪት ፅጌ በላቸው የተባለች ግለሰብ በቀን 15/9/2015 ዓ.ም ቤተሰቦቿ ተጠልፋ የት እንደደረሰች አናውቅም በማለት ለመነኸሪያ ክ/ከተማ ፖሊስ ባቀረቡት ማመልከቻ መሰረት ምርመራ ሊጀመር ችሏል።
የምርመራው ሂደትም በቀጣይ በከተማዋ ፖሊስ መምሪያ አማካይነት በቅንጅት ሊመራ ችሏል። በኋላም የምርመራው እና ተበዳይን ለማግኘት እና ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከክሉሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በቅንጅት የተመራ ስራ መደረግ ችሏል።
በዚህም ከወ/ሪት ፅጌ በላቸው የጠለፋ ወንጀል ጋር የተጠረጠሩ 6 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ ይገኛል።
ጥቆማው ከተደረገበት እለት ጀምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸውና የፀጥታ አካላትና ፖሊስ ጥብቅ ክትትል በማድረግ ተጠርጣሪው ሣጅን የኋላ መብራቴ እና የተጠለፈችውን ወ/ሪት ፅጌ በላቸው ይዞ ከተሰወረበት ቦታ አድኖ ለመያዝ ጥረትና ክትትል እየተደረገ ይገኛል።
ፖሊስ ይህን ሁሉ ጥረት ሲያደርግ እህታችንን ከነተጠርጣሪው ለመያዝ ህብረተሰቡ የሚችለውን ሁሉ ከስር በተዘረዘሩት ስልክ ቁጥሮች ህብረተሰቡ ጥቆማ እንዲሰጥ የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ይጠይቃል።
09 64 50 46 77
09 69 41 52 72
@fastmereja