የአባቶች ስቃይ
#ከራሱ ቆዳ የተሰራውን ስልቻ አሸዋ ሞልተው አሸከሙት
ከ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ ቅዱስ ቶማስ በተጣራራሪነቱ ይታወቃል፡፡
በቀዳሚ ስሙ ‘ዲዲሞስ’ ወይም ጨለማ ሲባል የነበረ ቢሆንም በኋላ ግን ቶማስ ወይም ፀሐይ ተብሏል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላ በ8ኛው ቀን እሁድ ነው ያየው፡፡
እናም በጦር የተወጋ ጐኑን ዳስሶ ማረጋገጥ በመፈለጉ ዳሶ ሲያውቅ ግን ጌታዬ አምላኬ ያለ ነው፡፡ እመቤታችን ስታርግም ከሁሉም ቀድሞ ያየው ነው፡፡
ወደ ሀገረ ስብከቱ ሕንድ የገባው እንደ ባሪያ በ30 ብር ተሽጦ ነበር፡፡ የገባበት አካባቢ አስተዳዳሪ ሉክዮስ አሳዳሪው ሆኖ በቤቱ ሲያገለግል ምን መሥራት እንደሚችል ሲጠይቀው ሕንፃ ማነጽ ሐውልት መቅረጽ እንደሚችል ስለነገረው ብዙ ወርቅና ብር ሰጥቶ ሰርቶ እንዲጠብቀው ነግሮት የተለየ ጥበብኛ ሰው አገኘሁ ለማለት ወደ ንጉሥ ሄደ፡፡
ቅዱስ ቶማስ ግን ገንዘቡን ለነዳያን መጸወተው በርካቶችንም አስተምሮ አሳምኗቸዋል፡፡ የሉክዮስ ሚስትና ልጆቿ ቤቱ ካሉ አገልጋዮች ጋር ሁሉ አምነው ተጠምቀዋል፡፡
ሉክዮስ ከሄደበት ተመልሶ ሕንጻውንና ሐውልቶቹን ለማየት ቢፈልግም ሐዋርያው በወርቅና በብርህ ያነጽኳቸው ሕንጻዎች እኒህ ናቸው ብሎ ያመኑትን አገልጋዮች አሳየው፡፡ ይህ ክፉ ባሪያ ተጫወተብኝ ብሎ እጅ እግሩን አሥሮ ቆዳውን አስገፍፎ ስልቻ አስፍቶ በአሸዋ መልቶ አሸክሞ በገበያው ሲያዞረው ሚስቱ አርሶንዋ አይታ በድንጋጤ ወድቃ ሞተች፡፡
መስፍኑም ደንግጦ ሚስቴን ካዳንካት እኔም በአምላክህ አምናለሁ አለው፡፡ ጌታ ቁስሉን እንደ ውኃ አቀዝቅዞለት ካለችበት ሄዶ ስልቻውን ቢያስነካት ተነሥታለች በዚህም ሉክዮስ አምኖ ተጠምቋል፡፡
ከዚህም በኋላ ስልቻውን ተሸክሞ ከቦታ ወደ ቦታ እየተዘዋወረ ሙት እያነሣ ድውይ እየፈወሰ አሕዛብን አሳምኖ አጠመቀ፡፡
በቀንጦፍያ የተገደሉ የአንድ ሽማግሌ ሰባት ልጆች ስልቻውን እያስነካ አስነሥቶለታል፡፡ በኢናስም የቃሉን ትምህርት የእጁን ተአምራት አይተው ከንጉሱ ሚስት ጀምሮ እስከ ተራ ገባር ድረስ ያሉት ሁሉ አምነው ተጠመቁ፡፡ በኋላም የጣኦት ካህናተ በተንኮል ከንጉሥና መኳንንቱ ጋር አጣልተው በሰይፍ አስመትተውታል፡፡
ዛሬም ድረስ ሕንድ ውስጥ በመንበሩ ላይ የጌታችንን የተወጋ ጎኑን የዳሰሰች የቅዱስ ቶማስ ቀኝ ቅድስት እጅ በሕይወት እንዳለች ሆና ትታያለች፡፡ በሕንድ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ፓትርያርክ ሲሾሙም የቅዱስ ቶማስን ቀኝ እጅ በሚሾመው ፓትርያርክ ላይ ጭነው ነው፡፡
ገዳማውያን እናቶችና አባቶች በብዙ ስጋዊ መከራ ውስጥ እንኳን አልፈው በእምነታቸው ጸንተው የክርስቶስን ወንጌል በሕይወታቸው ሰብከው፣ ወንጌልን ኖረው ነው የሚያልፉት፡፡ ታዲያ ገዳማቸውን ስንደግፍ፣ በዓታቸውን ስናጸና የእነርሱን በረከት እንታደላለን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444